loading
የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ መቀመጫዉን አስመራ ካደረገዉ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ (አዲኃን) ጋር ይወያያሉ፡፡

አዲኃን ባለፉት ስምንት ዓመታት መቀመጫውን ኤርትራ አድርጎ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስርዓት በመቃወም የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የነበረ የፖለቲካ ፓርቲ ነዉ፡፡ የአማራ መገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቀዉ አዲኃን ከመንግስት ጋር የሚያደርገዉ ድርድር ምን ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር አስካሁን አልታወቀም፡፡ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ትላንት አስመራ መግባታቸዉ ይታወሳል፡፡

ዓለም አቀፍ የሴቶች እና ወጣቶች የሰላም ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ ተካሄደ

የሰላም ኮንፍረንሱ የተካሄደው በአዲስ አበባ የኢሲኤ አዳራሽ ነው፡፡ አለም አቀፍ የሴቶችና ወጣቶች የሰላም ኮንፈረንስ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ስለሰላም የሚያወሳ አጫጭር ጹሁፎችን አቅርበዋል። ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሴቶች እና ወጣቶች ለሰላም መረጋገጥ […]

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገር ቤት ሊገባ ነዉ፡፡

ቪኦኤ እንደዘገበዉ አትሌት ፈይሳ በቅርቡ ቤተሰቡን ይዞ ወደ ሀገር ቤትለመመለስ ወስኗል፡፡ ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በጋራ ባወጡት መግለጫ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ወደ ሀገሩ እንዲመለስ መጋበዛቸዉ ይታወሳል፡፡በወቅቱም ለአትሌቱ የጀግና አቀባባል እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

የአማራ ክልል ልዑክ በአስመራ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ጋር ምክክር ጀመረ፡፡

አዴኃንና የአማራ ክልል መንግስት የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የዉይይታቸዉ ሀሳብ ነዉ፡፡ አዴኃን ወደ ሀገሩ ገብቶ በሰላም እንዲንቀሳቀስና ጥሩ አጋር ሆኖ እንዲሰራ የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግለትም ገልጧል ልዑኩ፡፡ የልኡኩ አባል የአማራ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን የኤርትራ መንግስት ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ያሳየውን አጋርነት ማድነቃቸዉን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡ የኤርትራ ውጭ […]

ሳልቫ ኪር ኤርትራን ሊጎበኙ ነው፡፡

ሳልቫ ኪር ኤርትራን ሊጎበኙ ነው፡፡ የኤርትራ ፕሬስ እንደዘገበው የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር አስመራን የመጎብኘት እቅድ ይዘዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ደቡብ ሱዳን ራሷን ችላ ሀገር መሆኗን በይፋ ስታውጅ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጁባ በተገኙበት ወቅት ነበር፡፡

የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን በ80 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ።

የኖቤል ተሸላሚ የነበሩት አናን እአአ በ1938 በጎልድ ኮስት ጋና ነበር የተወለዱት። ኮፊ አታ አናን ሙሉ ስማቸው ሲሆን አካን በሚባል ቋንቋ የመጀመሪያ ስማቸው ‘‘በዕለተ አርብ የተወለደ’’ ማለት ሲሆን አታ ማለት ደግሞ ‘‘መንትያ’’ ማለት ነው። በጋና እና አሜሪካ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ሲሆን የመጀመሪያ ስራቸውን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመጀመር ለአርባ ዓመታት አገልግለዋል። የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ ለመሆንም በቅተዋል።

የቀድሞው የጃኮቭ ዙማ አስተዳደር ምርመራ ሊደረግበት ነው፡፡

ደቡብ አፍሪካ በፕሬዝዳንት ጃኮቭ ዙማ ዘመነ መንግስት የተፈጸመውን የሙስና ወንጀል ለማጣራት አዲስ ምርመራ ልትጀምር ነው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የሀገሪቱ የፍትህ ተቋም በወቅቱ በመንግስት ተቋማት ላይ የተፈጸሙትን የሙስናና የማጭበርበር ወንጀሎች ለማጣራትና በድርጊቱ የተሳተፉትን ለፍርድ ለማቅረብ የሚደረገውን ስራ ዛሬ በይፋ ይጀምራል፡፡ ፕሬዝዳንት ጃኮቭ ዙማ ከአሁን ቀደም በስልጣናቸው እያሉ በሙስና ቅሌት ተጠርጥረው ተደጋጋሚ ክስ ይቀርብባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ቦኮሃራም በናይጄሪያ 19 ሰዎችን ገደለ።

ፕሬስ ቴሌቭዥን እንደዘገው ታጣቂው ቡድን ቦኮሃራም በሰሜን ምዕራብ የሃገሪቱ ክፍል በምትገኘው ማይላሪ ዘልቆ በመግባት በተሽከርካሪ የታገዘ የሮኬት ጥቃት ፈፅሟል። ማንነታቸው ያልተገለፀ የእርዳታ ሰጭ ድርጅት ሰራተኞች የሟቾችን ቁጥር 63 አድርሰውታል። የአካባቢው ነዋሪዎች ፖሊስ ጥቃቱ ሲፈጸም ህዝቡን ለመከላከል ምንም ዓይነት ሙከራ ባለማድረጉ ማዘናቸውን ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ ቦኮሃራም ከፈረንጆቹ 2009 ጀምሮ እስካሁን ከ20 ሺህ በላይ ናይጄሪያውያንን ሲገድል፥ […]

የማሊ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት የኬታን አሸናፊነት ይፋ አድርጓል፡፡

በማሊ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ለሁለተኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወዳዳሪዎች የኬታን ማሸነፍ አንቀበልም በማለታቸው ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶ ነበር፡፡ እጩ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት ሱሜይላ ሲሴ ውጤቱ ይፋ በተደረገ ማግስት ይህ የማሊያዊያንን ደምጽ የሚወክል ውጤት አይደለም አንቀበለወም ነበር ያሉት፡፡ የኋላ ኋላ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዲታይ ተደርጎ ኬታ 67.2 በሆነ […]

ጋዜጠኞችን የደበደቡ የዩጋንዳ ወታደሮች የእስር ትእዛዝ ወጣባቸው፡፡

የሀገሪቱ ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ዴቪድ ሙሁዚ ጸጥታ የማስከበር ስራን ሽፋን አድርገው ጋዜጠኞችን በጭካኔ የደበደቡ ወታደሮች ላይ ከባድ ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ጠበቅ ያለ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ የኬንያው ደይሊ ኔሽን ጋዜጣ እንደዘገበው ጋዜጠኞቹ ባለፈው ሰኞ በዩጋንዳ ፖለቲከኞች ይፈቱ የሚል አመጽ ባሰነሱ ሰልፈኞች ላይ የጸጥታ ሀይሎች የሚወስዱትን ርምጃ ሲዘግቡ ነው ድብደባው የደረሰባቸው፡፡ የዩጋንዳ መከላከያ ተቋም ይህን ትእዛዝ ያስተላለፈው በሀገር ውስጥና […]