loading
የኮሮና ቫይረስ  በ164 ሰዎች ላይ ሲገኝባቸው፤ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012  የኮሮና ቫይረስ  በ164 ሰዎች ላይ ሲገኝባቸው፤ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 630 የላብራቶሪ ምርመራ 190 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 670 መድረሱንም የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ባወጡት ሪፖርት አመላክተዋል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአረንጓዴ ልማት እንዲነሳ ጥሪ አስተላለፉ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአረንጓዴ ልማት እንዲነሳ ጥሪ አስተላለፉ:: የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ አሻራችንን በማኖር ለኢትዮጵያ አረንጓዴ ምንጣፍ እንዘርጋ በማለት ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ ልማት ጥቅም በመረዳት መሥራት ያስፈልጋል። አረንጓዴ ዐሻራ ከሥነ ውበት በላይ ነው። የምንተነፍሰው አየር ነው። የምንጠቀመው እንጨት […]

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 16 ሚሊየን ከፍ አለ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 16 ሚሊየን ከፍ አለ::በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 16 ነጥብ 5 ሚሊየን ከፍ ማለቱን በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፅህፈት ቤት አስታወቀ።  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር የ2020 የሰብዓዊት እርዳታ ፍላጎቶች ላይ ክለሳ […]

በአራተኛ ዙር 274 ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው መሸኘታቸዉን በኩዌት የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2012 በአራተኛ ዙር 274 ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው መሸኘታቸዉን በኩዌት የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ የኩዌት መንግሥት ያወጣውን የምህረት አዋጅ በመጠቀም ከኩዌት ወደ አገራቸው ለመመለስ ሲጠባበቁ የነበሩ 274 ዜጎች በአራተኛው ዙር ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።ዜጎቻችን በኩዌት ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በአምባሳደር አብዱልፈታህ አብዱላሂ፣ ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች እንዲሁም በኮሚኒቲ አመራሮች ሽኝት […]

ከ90 ዓመታት በኃላ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ሙሉ እድሳት የተደረገለት የነቀምቴ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተሻለ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 ከ90 ዓመታት በኃላ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ሙሉ እድሳት የተደረገለት የነቀምቴ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተሻለ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ::የምስራቅ ወለጋ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ለአርትስ በላከዉ መግለጫ የነቀምቴ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለበርካታ ዓመታት እድሳት ሳይደረግለት የቆየና ለአመታት በብልሹ አሰራርና ለታካሚዎች አመቺ ባለመሆኑ ከህብረተሰቡ በርካታ ቅሬታዎችና ወቀሳዎችን ሲያስተናግድ እንደቆየ ገልጿል፡፡ሆስፒታሉ እድሳት የተደረገለት […]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 176 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸዉ 75 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸዉ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 በኢትዮጵያ ተጨማሪ 176 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸዉ 75 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸዉ ተገለጸ፡፡ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ዉ 5 ሺ 6 መቶ 36 የላብራቶሪ ምርመራ አንድመቶ ሰባስድስት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸዉ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ አስታዉቀዋል፡፡በአጠቃላይም በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 5 መቶ 21 ደርሷል፡፡ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ ሰዎች […]

ከ1ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የላብራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012  ከ1ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የላብራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ:: የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ ሬይ አስመጪ እና ላኪ ኃ/ተ/ግ/ድርጅት በዛሬ ዕለት ለኮሮና መከላከያ የሚውሉ የላብራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያዎች ለ ሚኒስቴሩ አስረክበዋል ፡፡ በርክክቡም ወቅት የጤና ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ያዕቆብ ሰማን እንደተናገሩት የተደረገው ድጋፍ ለኮሮና በሽታ ለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከሎች አገልግሎት […]

የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር በይፋ ተጀመረ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር በይፋ ተጀመረ::ኢ/ር ታከለ ኡማ በሚኖሩበት አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ቀነኒ ሁንዴ መኖሪያ ቤት በመገኘት የቤት እድሳት መርሀግብሩን አስጀምረዋል :: በየአካባቢው የሚገኙ ለኑሮ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ አቅመደካማች መኖሪያ ቤታቸው የሚታደስ ይሆናል :: በመኖሪያ ቤት እድሳቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶችና […]

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ግምት የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012  የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ግምት የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች፡፡ ቤተክርስትያንዋ ላደረገችዉ ድጋፍ በአማራ እና አፋር ክልል በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ሳቢያ ለችግር ለተጋለጡ 10 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የሚሰራጭ ነዉ፡፡ ለደቡብ ወሎ ዞን የተደረገውን 800 ሺህ ብር በሚጠጋ ወጪ የሙቀት መለኪያ፣የምግብ ዘይት፣ዱቄትና የተለያዩ የንፅህና […]

 በፌደሬሽን ም/ቤት ፤በህግ ትርጉም ሽፋን የተላለፈዉን የፖለቲካ ዉሳኔ እንደሚቃወም ባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ገለጸ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 በፌደሬሽን ም/ቤት ፤በህግ ትርጉም ሽፋን የተላለፈዉን የፖለቲካ ዉሳኔ እንደሚቃወም ባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ገለጸ::ፓርቲዉ ለአርትስ ባለከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ፤የፌደሬሽን ምክርቤት በሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ/ም ባደረገዉ ስብሰባ ፤6ኛዉ አገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ በዉል ላልታወቀ ዘመን እንዲራዘም እና እድሜያቸዉ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ/ም የሚያበቃላቸዉ ሁሉም ም/ቤቶች በስልጣናቸዉ እንዲቀጥሉ መወሰኑ አግባብንት […]