loading
የአገር መከላከያ ሠራዊቱ ከፖለቲካው ጋር የሚወድቅ የሚነሳ ሳይሆን ከአገርና ከሕዝብ ጋር የሚዘልቅ ነው ሲሉ ሜጀር ጀኔራል ሹማ አብደታ ገለፁ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013የአገር መከላከያ ሠራዊቱ ከፖለቲካው ጋር የሚወድቅ የሚነሳ ሳይሆን ከአገርና ከሕዝብ ጋር የሚዘልቅ ነው ሲሉ ሜጀር ጀኔራል ሹማ አብደታ ገለፁ:: እየተገነባ ያለው የአገር መከላከያ ሠራዊት ከፖለቲካው ጋር የሚወድቅ የሚነሳ ሳይሆን ከአገርና ከሕዝብ ጋር ዘላቂነት ያለው ነው” ሲሉ በሠራዊቱ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ሹማ አብደታ ተናገሩ።ሜጄር ጄኔራሉ ሠራዊቱ በሰው ኃይል […]

ለትግራይ ወረዳ፣ ከተማና ቀበሌ የድጎማ በጀት የሚተላለፍበት አሰራር ዝግጅት ማጠናቀቁን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 ለትግራይ ወረዳ፣ ከተማና ቀበሌ የድጎማ በጀት የሚተላለፍበት አሰራር ዝግጅት ማጠናቀቁን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃጂ ኢብሳ እንደተናገሩት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ሚኒስቴሩ ለክልሉ ወረዳዎች ፣ ከተሞችና ቀበሌዎች የድጎማ በጀቱን የሚያስተላልፍበትን የአሰራር ዝግጅት አጠናቋል፡፡በሚኒስቴሩ የተዘጋጀው የበጀት ድጎማ አሰራር በሚቀጥለው ሳምንት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ […]

የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመሰረተ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመሰረተ::የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ምስረታ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ ተደረገ። በማህበሩ ምስረታ ላይም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ […]

የጤናውን ዘርፍ ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ የግሉ ዘርፍ እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 የጤናውን ዘርፍ ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ የግሉ ዘርፍ እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ::የጤና ጥበቃ ሚንስተር ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለጤናው ዘርፍ መንግስት ከሰጠው ትኩረት ጎን ለጎን የግሉ ዘርፍ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። ዶክተር እመቤት ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ አሁን ላይ በአለማችን የጥርስ ህክምና የመጨረሻ ቴክኖሎጂ የሆነውን ካድ ካም […]

የፈረንሳይ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ያለዉን የመገናኛ ብዙሃን አቅምን ለማሳደግ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክርቤት ጋር ድጋፍ ለማድረግና በጋራ ለመስራት ተስማሙ ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013 የፈረንሳይ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ያለዉን የመገናኛ ብዙሃን አቅምን ለማሳደግ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክርቤት ጋር ድጋፍ ለማድረግና በጋራ ለመስራት ተስማሙ ፡፡ ድጋፉ በተለይም የሚዲያ ነፃነት የሙያዉን ስነምግባር ባከበረ መልኩ እንዲሆንና በዘርፉ ላይ ባለሙያዎችን እንዲሁም የሚዲያ ተቋማትን ለማሰልጠን እንደሚዉልና አይነተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረዉ ተገልጿል፡፡የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በዋናነት የሚዲያ ነፃነት ላይ በኢትዮጵያ ያሉ […]

ከግንቦት መጨረሻ እስከ ሰኔ ወር መጀመሪያ ባለው ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ ዕቅድ ተይዟል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 ከግንቦት መጨረሻ እስከ ሰኔ ወር መጀመሪያ ባለው ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ ዕቅድ ተይዟል ተባለ:: ይህ የተባለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ በሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ከሲቪክ እና ከመገናኛ ብዙሃን አባላት በመከረበት ወቅት ነው፡፡ በውይይቱ ወቅት እንደተባለው ከታህሳስ እስከ ጥር ባሉት ጊዜያት የመራጮች ምዝገባ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት […]

በአንበጣ መንጋ ጉዳት የደረሰባቸውን አርሦ-አደሮች በዘላቂነት ለማቋቋም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ገልጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 በአንበጣ መንጋ ጉዳት የደረሰባቸውን አርሦ-አደሮች በዘላቂነት ለማቋቋም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ገልጹ፡፡ የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ በቅርቡ በአካባቢዉ በተከሰተዉ የአንበጣ መንጋ ምክንያት በ35 የ1ኛ ደረጃ እና በአንድ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት-ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በኢኮኖሚና በሰነልቦና ተጎጂ መሆናቸውም ነው በጥናቱ የተመላከተው፡፡ 9ሽህ 388 ህፃናት እና 2 […]

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2013 የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ::የኢፌዴሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ፡፡የኢፌዴሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ባደረገው 21ኛ አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ መንግሥት የሀገርን ሰላምና ሕልውና፣ የሕዝብንና የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ እና ሀገሪቷን ወደ ሁከትና ብጥብጥ የሚወስዱ ማናቸውንም ድርጊቶችን የመከላከል ሕገ […]

በአዲስ አበባ አዋሬ ገበያ በደረሰ የእሣት አደጋ አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2013 በአዲስ አበባ አዋሬ ገበያ በደረሰ የእሣት አደጋ አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ ::በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ አዋሬ ገበያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የእሣት አደጋ አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።የከተማ አስተዳደሩ የእሣትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ የእሣት አደጋው […]

የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ከ8ኛና 12ኛ ክፍል ዉጪ በተቀሩ ክፍሎች ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በኮቪድ19 የቀዉስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂ እቅድ ላይ የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ሟሟላት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነዉ ፡፡ ከጥቅምት 30 ጀምሮ ይጀመራል የተባለዉ ትምህርት አስፈላጊ […]