loading
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለማስጀመር መዘጋጀቱን ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2013 ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለማስጀመር መዘጋጀቱን ገለፀ:: ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ታሳቢ ባደረግ መልኩ ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት ማድረጉ ገልጿል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሉኡካን በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ቅበላን በማስመልከት የመስክ ምልከታ አካሂዷል። በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ዶክተር ኤባ ሜጀና በወቅቱ እንደተናገሩት  ፤ዩኒቨርሲቲው ወረርሽኙን ለመከላከል ያከናወነው ተግባር የሚበረታታ ነው። […]

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራሮች የምርጫ ቦርድን የምርጫ ዝግጅት ጎበኙ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራሮች የምርጫ ቦርድን የምርጫ ዝግጅት ጎበኙ::የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎና የምክር ቤት አመራሮች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቅድመ ዝግጅትን እየጎበኙ ነው። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የመከላከያ መንገዶችን በመተግበር እንዲካሄድ ከጤና ሚኒስቴር የቀረበለትን ምክረ ሃሳብ በተጨባጭ በማጤን […]

13ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን ተከበረ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 13ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን ተከበረ::13ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለሰላማችን፣ ለአብሮነታችንና ለሃገራዊ ብልጽግናችን!” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡የሰንደቅ ዓላማ ቀኑ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ አርበኞች እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ነው የተከበረዉ፡፡ ቀኑ በየዓመቱ የተለያየ መሪ ቃል እየተቀረፀለት በፌደራል፣ በክልልና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በዋናነት ስለሰንደቅ […]

ጠ/ሚ ዐቢይ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በጅማ ዞን ጉብኝት አደረጉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 ጠ/ሚ ዐቢይ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በጅማ ዞን ጉብኝት አደረጉ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የስራ እንቅስቃሴን ጎበብኝተዋል መሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው የሚያካሂዳቸውን የምርምርና የግንባታ እንቅስቃሴዎች መጎብኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።በተያያዘም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ ቡናን ወደ ውጭ በመላክ ስኬታማ የሆነ […]

በከተማ ልማት ዕቅድ ላይ የሚመክረው ጉባኤ ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ይጀምራል::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 በከተማ ልማት ዕቅድ ላይ የሚመክረው ጉባኤ ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ይጀምራል::”የብልፅግና ማዕከላት ከተሞች እና ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን እንዱስትሪን ለመገንባት በጋራ እንሰራልን”!! በሚል መሪ ሀሳብ ከጥቅምት 05 -07 2013 ዓ.ም ድረስ በአዳማ ከተማ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሴክተር የቀጣይ 10 ዓመታት መሪ ዕቅድ ትግበራ ማስጀመሪያ ጉባኤ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡ የጉባኤው ዋና […]

በአንድ ወር ውስጥ ከ10 ሺህ በላይ ህግ እና ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች ተቀጡ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 በአንድ ወር ውስጥ ከ10 ሺህ በላይ ህግ እና ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች ተቀጡ:: ባሳለፍነው መስከረም ወር ብቻ ከ10 ሺህ በላይ የትራፊክ ህግ እና ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎችን መቅጣቱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋከል፡፡ ኤጀንሲው በመስከረም ወር ብቻ የትራፊክ ህግ እና ደንብን ለማስከበር ባደረኩት የቁጥጥር 10 ሺህ 711 አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንብ ሲተላላፉ […]

የመቀሌ ዩኒቨርስቲ በአትሌቲክስና በብስክሌት ስፖርቶች በዓለም አቀፍ ውድድር ተሳትፈው አንፀባራቂ ድል ላስመዘገቡ ሁለት ሴት ስፖርተኞች የማበረታቻ ሽልማት ትናንት አበረከተ ።

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 የመቀሌ ዩኒቨርስቲ በአትሌቲክስና በብስክሌት ስፖርቶች በዓለም አቀፍ ውድድር ተሳትፈው አንፀባራቂ ድል ላስመዘገቡ ሁለት ሴት ስፖርተኞች የማበረታቻ ሽልማት ትናንት አበረከተ ።ዩኒቨርሲቲው ለሴት ስፖርተኞቹ የእውቅና ምስክር ወረቀትና የአንገት ሀብል ሽልማት አበርክቶላቸዋል። ዩኒቨርሲቲው ሽልማት ካበረከተላቸው ሴት ስፖርተኞች መካከል በቅርቡ በስፔን ቫለንሽያ ከተማ በተካሔደው የአትሌቲክስ ውድድር በ5 ሺህ ሜትር ሩጫ የአለም ክብረ ወሰን የሰበረችው […]

ዶክተር አረጋዊ በርሄ የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆኑ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013 ዶክተር አረጋዊ በርሄ የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆኑ::ዶክተር አረጋዊ በርሄ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆኑ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ዶክተር አረጋዊ በርሔን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር […]

የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ ከህብረተሰቡ በተደረገ ድጋፍ 14 ቢሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻሉ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ ከህብረተሰቡ በተደረገ ድጋፍ 14 ቢሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻሉ ተገለፀ:: የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ይህን አስተዋፅዖ ላደረጉት ሁሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡ ለተሰበሰበው ገንዘብ በሀገር ውስጥ ከሚኖሩ ኢትያጵዊያን በተጨማሪ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያን እና ትውለደ ኢትዮጵያን ተሳትፎም የጎላ ነበር ተብሏል፡፡ የድጋፍ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ […]

በከተሞች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 በከተሞች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ::በከተሞች ለሰላም እጦት መንስኤ የሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አስታወቁ፡፡ ፕሬዝዳንቷ ይህን ያስታወቁት በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ባለው የከተሞች የሰላም ፎረም ላይ ነው፡፡”የፍትህና ተጠያቂነት መጓደል፣ የኑሮ ደረጃ ልዩነቶች፣ እንዲሁም ስራ አጥነት በከተሞች የሚስተዋሉ […]