loading
የመካነ ቅርሶች ጉብኝት በኢትዮጵያ ቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን መስሪያ ቤት አስተባባሪነት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ።

አዲስ አበባ፣የካቲት 5፣ 2013 የመካነ ቅርሶች ጉብኝት በኢትዮጵያ ቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን መስሪያ ቤት አስተባባሪነት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ።የኢትዮጵያ ቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን መስሪያ ቤት በደቡብ እና ምእራብ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለመገናኛ ብዙሀን ያዘጋጀው ለሳምንት የሚዘልቅ ጉብኝት በመካሄድ ላይ ይገኛል። በጉብኝቱ የቅርስና ጥበቃ ባለሙያዎች ፣ የጥናት ባለሙያዎች እንዲሁም የመገናኛ ብዙሀን ሙያተኞች እየተሳተፉ ይገኛል። ይህ የኢትዮጵያን የአገር ውስጥ ቱሪዝም ለማበረታት […]

አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ በአራት ክልሎች የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል::

አዲስ አበባ፣የካቲት 8፣ 2013 አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ በአራት ክልሎች የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል:: አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ እና ሐረሪ ክልሎች የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል። ምዝገባው የሚከናወነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዕጩዎች ምዝገባ ባወጣው ከየካቲት 08 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ነው። የምርጫ […]

በዋግኽምራ ዞን 150 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 8፣ 2013 በዋግኽምራ ዞን 150 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ፡፡ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ድሃና ወረዳ 150 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመርቋል። በምርቃቱ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰም ማሞና የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮን ጨምሮ የክልልና የብሔረሰብ አስተዳደሩ ከፍተኛ […]

ኢዜማ መንግስት የፓረቲያቸዉን አባል ሕይወት የቀጠፉትን ወንጀለኞች አድኖ ሕግ ፉት ባስቸኳይ እንዲያቀርብ ጠየቀ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣ 2013 ኢዜማ መንግስት የፓረቲያቸዉን አባል ሕይወት የቀጠፉትን ወንጀለኞች አድኖ ሕግ ፉት ባስቸኳይ እንዲያቀርብ ጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ የፓርቲዉ አባል አቶ ግርማ ግድያን ተከትሎ በሰጠዉ መግለጫ ፤ ከዚህ በፊት በቢሾፍቱ ከተማ የምናደርገዉ እንቅስቃሴ ላይ የተለያዩ ችግሮች ሲያጋጥሙ እና አባላቶቻችን ላይ ማዋከብ ሲያገጥመን የቆየ ነዉ ብሏል፡፡ የምርጫ ወረዳ መዋቅራችን የሚጠቀምበት ጽ/ቤት ለመክፍት […]

የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ የፈፀመበት 84ኛው የሠማዕታት ቀን ታስቦ ዋለ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ የፈፀመበት 84ኛው የሠማዕታት ቀን ታስቦ ዋለ:: በአድዋ ሽንፈትን የተከናነበው የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር የዛሬ 84 ዓመት ዳግም ኢትዮጵያን ሲወር በአራቱም አቅጣጫ ይፋለሙት በነበሩ ኢትዮጵያዊያ ላይ ግፍና በደል ፈጽሟል። ግፍና በደሉን አንቀበልም ያሉት አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ግራዚያኒን በቦምብ ለመግደል ያደረጉትን ያልተሳካ ሙከራ ተከትሎም የግራዚያኒ […]

በ5 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳደሮች ኤች አይ ቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 በ5 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳደሮች ኤች አይ ቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ:: በ5 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳድሮች ኤች አይ ቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌዴራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ። እንደ ሀገር የስርጭት መጠኑ በወረርሽኝ ደረጃ ባይሆንም በጋምቤላ፣ አማራ፣ ሀረሪ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች፣ እንዲሁም በአዲስ […]

ጂ አይ ዜድ እና ኦሬንጅ የኦሬንጅ በይነ መረብ ማዕከልን በኢትዮጵያ ከፈቱ፡፡

ጂ አይ ዜድ እና ኦሬንጅ የኦሬንጅ በይነ መረብ ማዕከልን በኢትዮጵያ ከፈቱ፡፡ ማዕከሉ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቃዊ አፍሪካ ሶስተኛውና ወጣቶችን በበይነ መረብ ቴክኖሎጂ ለማሠልጠንና የተሻለ የሥራ ዕድል እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡ ከዚህ ባለፈም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር የዲጂታል ክህሎትን የሚያጎለብትና ለልዩ ልዩ ፈጠራዎች የሚያነሳሳ የኦሬንጅ ዲጂታል ማዕከል […]

ስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ፓርቲዎች ገለጹ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 25፣ 2013 ስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ፓርቲዎች ገለጹ:: በጋምቤላ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች  ምርጫው ያለንዳች እንከን እንዲሳካ ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ፉክክር  ለማድረግ እየተዘጋጁ መሆናቸውን አመራሮቹ  ተናግረዋል። የብልጽግና ፓርቲ ጋምቤላ ክልል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ላክድር ላክባክ እንዳሉት ፤ ብልጽግና በክልሉ ከሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ካለፈው ዓመት ጀምሮ በትብብር እየሰራ […]

ለሴቶች ከፍ ያለ ደረጃ መድረስ ከትምህርት ሌላ ምንም መሰላል እንደሌለ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣ 2013 ለሴቶች ከፍ ያለ ደረጃ መድረስ ከትምህርት ሌላ ምንም መሰላል እንደሌለ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ ፡፡ ሴቶች በትምህርታቸው ውጤታማ በመሆን ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎችን በብቃት መምራት እንደሚችሉ አምነው እንዲማሩ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መክረዋል።ፕሬዚዳንቷ  ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ የቱሉ ዲምቱ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ከትምህርት ቤቱ የስርዓተ ጾታ ክበብ አባላት ጋር […]

በሀገራችን ያለውን የአይን ህክምና ዘርፍ ከፍ የሚያረግ እና የተሻለ ህክምና የሚገኝበት ላቪስታ የአይን ህክምና ክሊኒክ ተመርቆ ስራ ጀመረ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2013 በሀገራችን ያለውን የአይን ህክምና ዘርፍ ከፍ የሚያረግ እና የተሻለ ህክምና የሚገኝበት ላቪስታ የአይን ህክምና ክሊኒክ ተመርቆ ስራ ጀመረ:: ላቪስታ የአይን ህክምና በሀገራችን ያለውን የአይን ህክምና ዘርፍ ለማገዝና በተሻለ ለመስራት መቋቋሙ ተነግሯል፡፡ እንዲሁም በአዳዲስ የአይን ህክምና መሳሪያዎች በመታገዝ ታካሚዎች የተሻሉ የተባሉ መሳሪያዎች ለማግኘት ወደ ውጪ ሀገር ሄደው ለመታከም የሚገደዱበትን […]