loading
የዲግሪ ተመራቂው ወጣት ቅድሚያ ለሀገር ህልውና ብሎ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገባ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣2013 በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ትምህርት በዲግሪ የተመረቀው ወጣት ስራ ቢያገኝም ቅድሚያ ለሀገር ብሎ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገባ፡፡ ከአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ወታደራዊ ስልጠናውን የተቀላቀለው ወጣት በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ የትምህርት ዘርፍ የድግሪ ምሩቅ ሲሆን ስራ ቢያገኝም ቅድሚያ ለሀገሬ ህልውና ብሎ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገብቶ እየሰለጠነ ይገኛል፡፡ የዲግሪ ተመራቂው ነጋ ምህረት ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ […]

በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 1ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የኮቪድ-19 ክትባት ለመከተብ ዘመቻ ተጀመረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣2013  በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 1ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችን ለመከተብ ዘመቻ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ አስታወቁ፡፡ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ የሚገኘውን የኮቪድ -19 ስርጭት በርብርብ መግታት ካልተቻለ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ዶክተር ዮሐንስ እንደገለጹት ባለፉት አራት ሳምንታት በኮቪድ -19 የመያዝ ምጣኔው፣ በጽኑ የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እና […]

ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የሚያሳይ ምልክት መታየቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣2013 ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የሚያሳይ ምልክት መታየቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ። ዶክተር ሊያ ጉዳዩን አስመልክተው ዛሬ በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 5 ሺህ 547 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡ በአንድ ቀን ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች መያዛቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ የወረርሽኙ መጠን ከዚህ በፊት ካለው በእጅጉ መጨመሩን […]

ህገወጥ ነጋዴዎችን በአከባቢያችሁ ለሚገኝ ፖሊስ ጠቁሙ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣2013  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ለንግድ ማህበረሰቡ ማሳሰቢያ ሰጠ፡፡ ቢሮው አንዳንድ ስግብግብ ነጋዴዎች ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ በአቋራጭ ለመክበር እና ሆን ብሎ ህገ-ወጥ የዋጋ ጭምሪ እና ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ለመፍጠር ጥረት ማድረግ ላይ መሆናቸውን ድርሼበታለሁ ብሏል፡፡ ስለሆነም በማንኛውም ንግድ ስራ ላይ ተሰማርታችሁ የምትገኙ ነጋዴዎች ለሽያጭ በሚቀርቡ ማለትም በተለይ ከውጪ ሃገር […]

የኢትዮጵያ ሽልማት በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣2013  በዓለም ፀሐይ ወዳጆ የጥበብ መድረክ አዘጋጅነት ከዚህ በፊት በአሜሪካ ለሶስት ዙር የተካሄደው የኢትዮጵያ ሽልማት ለአራተኛ ግዜ በኢትዮጵያ ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ፡፡ በጥር 2011 ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ ኮሎራዶ የተቋቋመው ዓለም ፀሐይ ወዳጆ የጥበብ መድረክ ለመጀመርያ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ሄልተን ነሀሴ 29፣ 2013 ዓ.ም በዕለተ ቅዳሜ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ታዉቋል፡፡ […]

ለተዝካር ማውጫ የተዘጋጀ 100 ሺህ ብር ለህዳሴ ግድብ የለገሱ ኢትዮጵያዊ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣2013 ኢትዮጵያዊቷ ለወላጅ አባታቸው ተዝካር ማውጫ የተዘጋጀ 100 ሺህ ብር ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድጋፍ አደረጉ። በጀርመን ሀገር የሚኖሩት ኢትዮጵያዊቷ ወይዘሮ ሌንሳ ተሾመ ለወላጅ አባታቸው ተዝካር ማውጫ የተዘጋጀ 100 ሺህ ብር ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲውል በማድረጋቸው ከግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። ወይዘሮ […]

ሉሲ (ድንቅነሽ) በዱባይ በሚካሄደዉ ኤክስፖ ለጉብኝት ልትቀርብ መሆኑ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣2013 ሉሲ (ድንቅነሽ) በዱባይ በሚካሄደዉ ኤክስፖ ለጉብኝት ልትቀርብ መሆኑ:: ሉሲ (ድንቅነሽ) በዱባይ በሚካሄደዉ ኤክስፖ 2020 ላይ ለጎብኚዎች ልትቀርብ መሆኑ ተገለፀ፡፡ በፈረንጆቹ ከጥቅምት 1 እስከ መጋቢት 31 ቀን 2022 በዱባይ ኤክስፖ 2020 ይካሄዳል፡፡ በኤክስፖውም ላይ ሉሲ (ድንቅነሽ) ለጎብኚዎች እንደምትቀርብ የተገለፀ ሲሆን÷ ለዚህም ትናንት የሉሲ ቅሬተ አካል ዱባይ መግባቱን ከንገድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ […]

በዋሽንግተን ሲካሄድ በቆየው የህዳሴ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከ1 ሚሊዮን 1 መቶ ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣2013 በዋሽንግተን ሲካሄድ በቆየው የህዳሴ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከ1 ሚሊዮን 1 መቶ ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ:: በዋሽንግተን የኢፌዲሪ ኤምባሲ ከበድር ኢትዮጵያ እና ከኡስታዝ ጀማል በሽር (የአባይ ንጉሶች መስራች) ጋር በመሆን በGoFundMe ሲያካሂድ የቆየው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የማጠናቀቂያና የምስጋና ምሽት በዋሽንግተን ዲ.ሲ. የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከናውኗል:: በወቅቱም አምባሳደር ፍጹም […]

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 2 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣2013 በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 2 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት 2 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ10 ሺህ 804 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 2 ሺህ 95 ሰዎች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል።13 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሲሆን፤ 532 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ህክምና […]

ትምህርት ቢሮ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚፈጽሙ ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣2013 ትምህርት ቢሮ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚፈጽሙ ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ:: የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚፈጽሙ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ እወስዳለሁ አለ ፡በከተማዋ አስተዳደር የሚገኙ የግል ትምህርት ተቋማት በትምህርቱ መስክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና ለከተማው ነዋሪ የስራ እድል ከመፍጠር እረገድ ሚናቸዉ ላቅ ያለ […]