loading
ጄምኮርፕ ኩባንያ የብሔራዊ የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን አደጋን ለመቀነስ ለሚያደርገዉ ዝግጅት ድጋፍ እያደረኩኝ ነዉ አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ጄምኮርፕ ኩባንያ የብሔራዊ የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን አደጋን ለመቀነስ ለሚያደርገዉ ዝግጅት ድጋፍ እያደረኩኝ ነዉ አለ፡፡ ኩባንያዉ የብሔራዊ የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን 200,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለመግዛት ላወጣው ጨረታ ተወዳዳሪ ሆኖ በመገኘት በድጋሚ ማሸነፉን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ አስታዉቋልጄምኮርፕ ኢኮኖሚውን በንግድ ሥራ ለመደገፍ እና ኢንቨስት ለማድረግ የኢትዮጵያን ገበያ የተቀላቀለው በ2010ዓ.ም. […]

ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆነ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆነ:: በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆኗል።በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የለይቶ ሕክምና ማእከል ውስጥ ክትትል እየተደረገላት ከምትገኝ የ34 ዓመት እናት ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም የተወለደው ሕፃን 3.1 ኪ.ግ. ክብደት ያለው ወንድ ልጅ መሆኑም ታውቋል።ከሕፃኑ በተወሰደው ናሙና ላይ በተካሔደው […]

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀቺው ተጠርጣሪ ተያዘች::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀቺው ተጠርጣሪ ተያዘች:: የአማራ ፖሊስ ከሚሽን እንዳስታወቀዉ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ የሁለት ዓመት ዕድሜ ያለው ህፃን ይዛ በመሰወር የማስለቀቂያ 600 ሺህ ብር የጠየቀችው ተጠርጣሪ መያዟን የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ግለሰቧ በሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት መኖሪያ ቤት ከግብረአበሯ ጋር በመሆን ህፃኑን ይዛ በመሰወር ለህፃኑ […]

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ምክንያት በማድረግ በትግራይ ክልል እየተፈፀመ ያለዉ ግፍ እንዲቆም ህጋዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልገዉ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ለአርትስ ቲቪ ገለፀ ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ምክንያት በማድረግ በትግራይ ክልል እየተፈፀመ ያለዉ ግፍ እንዲቆም ህጋዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልገዉ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ለአርትስ ቲቪ ገለፀ ፡፡በክልሉ አሁን ድረስ ቀደም ሲል የነበረዉ የአፈናና የእኔ አዉቅልሀለሁ አገዛዝ አሁንም እንደቀጠለ የተናገሩት የፓርቲዉ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት በተለይ የትግራይ ህዝብን ከመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የሚደረገዉ ጥረት ተቀባይነት እንደሌለዉ ተናግረዋል፡፡በመሆኑም በክልሉ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ለአፍሪካ ቀን” የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ለአፍሪካ ቀን” የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸው አፍሪካ ባለ ብዙ ፀጋ ባለቤት ናት በመሆኑም የአፍሪካ ቀንን ስናከብር የምንፈልጋትን የአፍሪካን እዉን እንድትሆን አንድነታችንን እናጠናክር ብለዋል::የአፍሪካ ቀን “የአፍሪካ ነፃነት ቀን” እየተባለም የሚከበር ሲሆን እ.ኤ.አ ግንቦት 25 ቀን 1963 በ32 ነፃነታቸውን በተቀናጁ የአፍሪካ […]

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኳታር መንግስት ለኢትዮጵያ የሕክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረጉ አመሰገኑ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኳታር መንግስት ለኢትዮጵያ የሕክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረጉ አመሰገኑ:: “የኳታር መንግሥት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች፣ የሕክምና ጓንቶች፣ ፊትን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍኑ እና ሰውነትን ከንክኪ የሚከላከሉ ልብሶች እንዲሁም ሌሎች ኮቪድ-19ን የመከላከያ ግብአቶች መላካችሁ  ወረርሽኙን ለመግታት የምናደርገውን ጥረት ይደግፋል ነዉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ድጋፉ 470 ሺ ማስክ ፣ 70 […]

ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር ሉዓላዊነት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባቸው ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ግንቦት 18፣2012 ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር ሉዓላዊነት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባቸው ተገለጸ:: “የኢትዮጵያ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች ሚና ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግደብ ግንባታ ሁለንተናዊ ድጋፍ እና ተሳትፎ” በሚል መሪ ቃል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዳራሽ ውይይት ተደርጓልበውይይቱ ወቅት በሀገሪቱ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች በሀገር ሉዓላዊነት እና አንድነት ጉዳይ እንደማይደራደሩ ተናግረዋል። በተለያዩ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ልዩነት ቢኖርም […]

አቶ ገዱ የዓለም ምግብ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012 የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የዓለም ምግብ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን ዴቪድ ቢስሊይን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ሁለቱ  ወገኖች የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት፣ የበረሃ አንበጣ እና የጎርፍ አደጋ በቀጠናው ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።በተጨማሪም የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከተ መረጃ […]

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 100 ሰዎች ሲገኙ የ1 ሰው ህይወት አለፈ ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 100 ሰዎች ሲገኙ የ1 ሰው ህይወት አለፈ :: ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4950 የላቦራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 100 ሰዎች ተገኝተዋል፡፡አዲስ የተገኙትን ጨምሮ ባጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 831 ደርሷል፡፡ ትናንት ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰቦች የእድሜ ክልላቸው ከ 3 እስከ 70 ዓመት ሲሆን 53 […]

29ኛው የግንቦት 20 በዓል በዛሬው እለት በመላው ሀገሪቱ በመከበር ላይ ይገኛል ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 29ኛው የግንቦት 20 በዓል በዛሬው እለት በመላው ሀገሪቱ በመከበር ላይ ይገኛል :: የግንቦት 20 የድል መታሰቢያ በዓልን በማስመልከትም በዛሬው እለት በአዲስ አበባ መድፍ ተተኩሷልጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም 29ኛው የግንቦት 20 በዓልን በማስመልከት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ግንቦት 20 የዘመናዊት ኢትዮጵያን ታሪክ ከቀየሩ ዕለታት […]