loading
ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት ተከትበዋል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት ተከትበዋል ተባለ:: የጤና ሚኒስቴር በየ24 ሰዓቱ በሚያወጣው የኮቪድ 19 ወቅታዊ መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት መከተባቸውን ገልጿል፡፡ በተጨማሪም 2 መቶ22 ሺ 5 መቶ 60 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ሪፖርቱ አትቷል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ […]

የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ወደ ግል ለማዞር የተደረገ ምክክር::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013  ጠ/ሚ ዐቢይ የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ወደ ግል ለማዞር ከተቋቋመው አማካሪ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሁለት የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ፈቃድ ለመስጠት እየተሰራ ባለው ስራ ዙሪያ ከአማካሪ ምክር ቤት አባላት ጋር መከሩ።ውይይቱ አዲስ የቴሌኮም ፈቃድ በመስጠት ሂደቱ ዙሪያ የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ወደ ግል ለማዞር ከተቋቋመው […]

የህዳሴው ግድብ የሰላም ፕሮጀክት ነው” ደቡብ-ሱዳን

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2013  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለሶስትዮሽ ድርድሩ ህብረቱ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተስፋ አለን አሉ፡፡ አቶ ደመቀ “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” መርህ መሰረት የሶስትዮሽ ድርድሩ ውጤታማ እንዲሆን የአፍሪካ ህብረት ሚናው አጠናክሮ እደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።አቶ ደመቀ የግድቡ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሊት በተያዘለት ጊዜ እንደኪካሄድም አብራርተዋል፡፡ አቶ ደመቀ […]

ኢትዮጵያውያን የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም በያሉበት ሆነው ድምጻቸውን የሚያሰሙበት መርሃ ግብር ዛሬ ይካሄዳል::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2013 ኢትዮጵያውያን የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም በያሉበት ሆነው ድምጻቸውን የሚያሰሙበት መርሃ ግብር ዛሬ ይካሄዳል:: በፕሮግራሙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ አገራትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ" በሚል መሪ ሐሳብ በያሉበት ሆነው ለአንድ ሰዓት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ፡፡ ከመልእክት ከማስተላለፊያ መንገዶች አንዱ ጣልቃ ገብነቱን የሚቃወም የዲጂታል ፊርማ ማሰባሰብ መሆኑም ታውቋል፡፡ መርሃ-ግብሩ ብሔራዊ […]

ኢትዮ ቴሌኮም የኢንፎርሜሽን ቴከኖሎጂ እና የኔትወርክ መሰረተ ልማትን የሚያፋጥን ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማእከል ስራ አስጀመረ።

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2013 ኢትዮ ቴሌኮም የኢንፎርሜሽን ቴከኖሎጂ እና የኔትወርክ መሰረተ ልማትን የሚያፋጥን ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማእከል ስራ አስጀመረ። ይህ ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማእከል በከፍተኛ ደረጃ የሃይል ፍጆታን የሚቀንስ፣ በቀላሉ ፍላጎትን ተከትሎ ሊስፋፋ የሚችል እና ፈጣን የሲስተም ተከላ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ […]

ከግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ የክረምት ዝናብ በተወሰኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተፅዕኖ እንደሚኖረው ተገለጸ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2013  ከግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ የክረምት ዝናብ በተወሰኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተፅዕኖ እንደሚኖረው ተገለጸ:: የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አህመዲን አብዱልከሪም ከግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ የክረምቱ ዝናብ ተፅዕኖ ሊበረታ ስለሚችል በአርሶና አርብቶ አደር አካባቢዎች ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብለዋል። ከግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ የክረምት ዝናብ ተፅዕኖው ሊጀምር እንደሚችል የጠቆሙት አቶ […]

መንግሰት ስለ ኬሚካል ጦር መሳሪያዉ የሰጠዉ ምላሽ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2013 የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅሟል የሚለውን ዘገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባበለ፡፡የውጭ ጉዳይ  ሚኒስቴር ሁኔታውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በቴሌግራፍ መፅሄት ላይ ታትሞ የወጣውን በትግራይ ክልል ከጦር ወንጀል የማይተናነስ ድርጊት መፈፀሙን የሚያመላክት ሪፖርት አጥብቆ እንደሚቃወም ገልጿል፡፡ በመፅሄቱ የአፍሪካ ዘጋቢ  የሆነው ዊል ብራውን መቀመጫውን ናይሮቢ ላደረገው የቴሌግራፍ መፅሄት ባጠናቀረው […]

ኮሚሽኑ የፀረ ሙስና ትግሉን ላገዙ ግለሰቦችና ተቋማት እውቅና ሰጠ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2013  የፌዴራል ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የፀረ ሙስና ትግሉን አግዘዋል ላላቸው ለ10 ተቋማት፣ ለ286 ግለሰቦች እና ለ229 ተማሪዎች እውቅና ሰጠ። እውቅና የተሰጣቸው ተማሪዎችም በሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ላይ በተዘጋጁ ጥያቄዎች አሽናፊ ለሆኑ ለዘጠነኛ እና አስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ነው። “ኮሚሽኑ ትኩረት ለትውልድ ሥነ ምግባር ግንባታ” በሚል መሪ […]

የመጪው ክረምት ዝናብ ለሕዳሴው ግድብ በረከት::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2013 የመጪው ክረምት ዝናብ ለሕዳሴው ግድብ በረከት የመጪው ክረምት ዝናብ ለሕዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ተባለ:: ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ያለፈውን በልግና የመጪውን ክረምት የአየር ሁኔታ ግምገማና ትንበያ ይፋ አድርጓል። በመጪው ክረምት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያው የአገሪቱ የምዕራብ አጋማሽ አብዛኞቹ ቦታዎች ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙና በጥቂት ቦታዎችም መደበኛ ዝናብ […]

እነ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ በመጪው ጥር አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ አስታወቁ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17፣ 2013 እነ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ በመጪው ጥር አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ አስታወቁ:: አምስት ኩባንያዎች እና ተቋማትን ያካተተው “ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ” የተሰኘው ጥምረት የሚያቋቁመው ኩባንያ፤ በኢትዮጵያ የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት የማቅረብ ስራውን ከሰባት ወራት ገደማ በኋላ በጥር 2014 ዓ.ም ለመጀመር እንዳቀደ አስታወቀ። አዲሱ ኩባንያ አሁን በሀገሪቱ በብቸኝነት የቴሌኮም አገልግሎት እየሰጠ ያለውን ኢትዮ ቴሌኮምን የሚገዳደር […]