loading
የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በባለ ስልጣናት ግድያ በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የመከላከያ ምስክሮችን መስማት ጀመረ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013   የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በባለ ስልጣናት ግድያ በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የመከላከያ ምስክሮችን መስማት ጀመረ፡፡ ፍርድ ቤቱ በሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ እጃቸው አለበት በተባሉት በእነሻምበል መማር ጌትነት መዝገብ የተከሰሱ 32 ተከሳሾችን የመከላከያ ምስክሮች ነው ማዳመጥ የጀመረው፡፡ በዚሁ የክስ መዝገብ ጉዳያቸው ሲታይ ከነበሩት 55 ተከሳሾች […]

ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት ከነገ ጀምሮ በጤና ተቋማት ይሰጣል-ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013 ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት ከነገ ጀምሮ በጤና ተቋማት ይሰጣል-ጤና ሚኒስቴር በአዲስ አበባ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ባሉ የጤና ተቋማት ለኮሮና ቫይስ ተጋለጭ የሆኑ የህበረተሰብ ክፍሎች እንዲከተቡ ጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የኮቪድ ክትባት ከወሰዱ ሶስት ወር የሞላቸው ዜጎች ከነገ ጀምሮ እንደሚከተቡ እና በክልሎች ደግሞ ክትባቱን ከሐምሌ 9 […]

የአማራ ክልል በህወሓት ላይ የተጀመረው “ሕግን የማስከበር” ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 7፣ 2013  የአማራ ክልል በህወሓት ላይ የተጀመረው “ሕግን የማስከበር” ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ:: በትግራይ ክልል በህወሓት ላይ የተጀመረው ሕግን የማስከበር ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ሕዝብ አስፈላጊውን ርብርብ እንዲያደርግ የአማራ ክልል ጠየቀ፡፡ ክልሉ ትናንት ባወጣው መግለጫ “ትህነግ አገር ከማፍረስ እኩይ ተልዕኮው ሊታቀብ የሚችለው የአገራችንን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት በጽናትና በአላማ ቁርጠኝነት በጋራ […]

የሲሚንቶ ግብይትን ለመቆጣጣር የወጣው መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ ተነሳ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 7፣ 2013  የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሲሚንቶ ግብይትን ለመቆጣጣር የወጣው መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ መነሳቱን አስታወቀ፡፡ በዚህ መሰረት የግብይት ሂደቱ በነፃ ገበያ መርህ እንዲከናወን ተወስኗል ብሏል። የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ እቃዎች ዋጋ ጥናት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት፥ በሲሚንቶ ግብይት ላይ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት ሲባል ወደ ቀደመ የነፃ ገበያ አሰራር ተመልሰናል […]

የቀጥታ በረራም ሆነ ከአውሮፕላን ላይ እርዳታ መጣል የሚለው ሀሳብ ተቀባይነት የላቸዉም::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8፣ 2013 ለትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ በቀጥታ በረራም ሆነ የሀገር ሉዓላዊነትን በሚጥስ ሌላ ተግባር የሚደረግ እንቅስቃሴ አይፈቀድም ተባለ:: የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በተለይ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት፤ በዓለም ምግብ ፕሮግራምና ሌሎች ዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በኩል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የእርዳታ አቅርቦቶች በተገቢው መንገድ ወደ መቀሌ እንዲያጓጓዙ […]

የ4ዓመት ከ9ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን አግቶ የወሰደዉ ግለሰብ ተያዘ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8፣ 2013 የ4ዓመት ከ9ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን አግቶ የወሰደዉ ግለሰብ ተያዘ:: የ4ዓመት ከ9ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን ከትምህርት ቤት አግቶ በመውሰድ ገንዘብ የጠየቀው ግለሰብ ከአዲስ አበባ ውጪ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀዉ የእገታ ወንጀሉ የተፈፀመው ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10 ሰዓት ተኩል ገደማ በጉለሌ ክፍለ ከተማ […]

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ተረከበች::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013 አሜሪካ ለኢትዮጵያ የለገሰችውን 453 ሺህ 600 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ጤና ሚኒስቴር ተረከበ:: በአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የተደረገው ድጋፍ  ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተባለው  ክትባት ሲሆን ቃል ከገባችው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶዝ 453 ሺህ 600 ዶዙ አዲስ አበባ  ገብቷል። ድጋፉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት […]

ኢትዮጵያ በጽናት ትገሰግሳለች-ጠ/ሚ ዐቢይ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013  ጠ/ሚ ዐቢይ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን አስመልክተው በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ በጽናት ትገሰግሳለች ብለዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ÷የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት መርሃግብር […]

በጣና ሀይቅ በተሰወረችው ጀልባ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስክሬን ተገኘ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013 በጣና ሀይቅ በተሰወረችው ጀልባ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስክሬን ተገኘ:: በጣና ሀይቅ በተሰወረችው ጀልባ ህይወታቸው ያለፈ የ7 ሰዎች አስክሬን ተገኘ በማእከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ በጣና ሀይቅ 13 ሰዎችን አሳፍራ በጉዞ ላይ እንዳለች በተሰወረችው አነስተኛ ጀልባ ህይወታቸው ያለፈ የሰባት ሰዎች አስክሬን መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ። የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ […]

የሕወሃት ትንኮሳ በሰብዓዊ ድጋፍ ስርጭት ላይ የፈጠረው ጫና…

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 16፣ 2013 አሸባሪው ህወሓት ትንኮሳውን ወደሌሎች ክልሎች በማስፋቱ የእርዳታ እህል ለማጓጓዝ መቸገሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ:: መንግስት ለሰብአዊ ድጋፍ ሲል ያሳለፈውን የተናጠል ተኩሱ አቁም አሸባሪው ህወሓት ወደ ጎን በመተው ትንኮሳውን ወደ አማራ እና አፋር ክልል ማስፋቱ ይታወቃል። በዚህ ግጭት ምክንያትም የእርዳታ እህል እና መሰል ድጋፎችን ወደ ትግራይ ክልል ለማስገባት መቸገሩን የተባበሩት […]