loading
በሰራተኞች ጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ምክንያት ዛሬ አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረውን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በጥቂት ቻይናውያን ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

በሰራተኞች ጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ምክንያት ዛሬ አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረውን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በጥቂት ቻይናውያን ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሜሪካ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ግንቡን እናፍርስ ድልድዩንም እንገንባ” በሚል መሪ ቃል በአሜሪካ በሚያደርጉት ቆይታ ከ40 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይታደማሉ ተባለ፡፡ በዋሽንግተንዲሲ፣ በሎሳንጀለስና በሚኔሶታ በሚካሄዱ የድጋፍ ሰልፎችም የተለያዩ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተዋል፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ በሚደረገዉ የድጋፍ ሰልፍ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊና ትዉልደ ኢትዮጵያዊ የሚሳተፍበት ሲሆን ፤በሎሳንጀለስ ደግሞ የጥያቄና መለስ የዉይይት መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡ በሚኔሶታ በሚደረገዉ ሶስተኛዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቆይታ የተለያዩ ፖለቲካዊ […]

መንግስት ባወጣው የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ ለመሆን ከታራሚዎች ምን ይጠበቃል?

መንግስት ባወጣው የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ ለመሆን ከታራሚዎች ምን ይጠበቃል? መንግስት ያወጣው የምህረት አዋጅ ከወጣበት ሐምሌ13ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል፡፡ የምህረት አሰጣጡ ለሚቀጥሉት 6 ወራት ስራ ላይ የሚውል ሲሆን፤ የምህረቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ታራሚዎች የተጠየቁበት ወንጀል እስከ ግንቦት 30 የተፈጸመ ከሆነ ብቻ ነዉ ተብሏል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በእነዚህ […]

አዋሽ ባንክ ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰትን የሚቀንስ ዲጂታል የገንዘብ ማስተላልፊያ አገልግሎት መስጠት ጀምሬያለሁ አለ፡፡

አዋሽ ባንክ ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰትን የሚቀንስ ዲጂታል የገንዘብ ማስተላልፊያ አገልግሎት መስጠት ጀምሬያለሁ አለ፡፡ ባንኩ ና ወርልድሪሚት ገንዘብ በዲጂታል ማስተላለፍን በጋራ ለመስራት መፈራረማቸውን ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ወርልድ ሪሚት የገንዘብ ማስተላለፊያ ከ 50 በላይ ሀገራትና ከ145 በላይ መዳረሻዎች ላይ እየሰራ መሆኑን እና በ ኢትዮጲያ ውስጥ በወርልድ ሪሚት የተደረገ የገንዘብ ልውውጥ ከ160 በመቶ በላይ እንዳደገ በምስራቅ እና […]

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ነገ ወደ አሜሪካ ይሄዳሉ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩንም እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሚያደርጉት ጉዞ በአጠቃላይ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፥ በሀገራቸው እየተካሄደ ላለው ሁለንተናዊ ለውጥ አካል ሆነው ለሀገሪቱ ልማትና እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ያለመ ነው ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሎስ አንጀለስ እና በዋሽንግተን ዲ ሲ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ሐምሌ 24 ቀን ድረስ ነው በአሜሪካ ቆይታ የሚያደርጉት። የኢፌዴሪ […]

ቡናችን በዓለም ገበያ የሚፈለገዉን ያህል አልተዋወቀም ተባለ

ይህ የተባለዉ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንና ከቡና ላኪዎች ማህበር ጋር በጋራ ባዘጋጁት ቡናን በአለም ማስተዋወቅ ላይ ባተኮረ የዉይይት መድረክ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ የቡናና ሻይ ባለስልጣን የገበያ ልማት ቁጥጥርና የግብይት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሻፊ ዑመር በሀገራችን ከ25 ሚሊየን በላይ ህዝብ ኑሮዉ በቡና ምርት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የምናመርተዉ ቡና ግን ጥራቱን የጠበቀ ባለመሆኑ አምራቹን መጥቀም አልተቻለም […]

የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች “መደመር በተግባር ” እያሉ ነው

የኪነጥበብ ባለሙያዎች የገቡትን ቃል ጠብቀው በጥቁር አንበሳ፣ በአለርት እና በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታሎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ አርቲስቶቹ ከአድናቂዎቻቸው ጋር በመሆን “መደመር በተግባር” የሚል መሪ ቃል ይዘው ደም የመለገስ ተግባር ፈጽመዋል፡፡