loading
ዶክተር አብይ አህመድ ከአሜሪካዉ ኮንግርስ አባል ክሪስ ስሚዝ ጋር ተወያዩ፡፡

አርትስ 18/12/2010 የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጽህፈት ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በቲዉተር ገጻቸዉ እንዳስታወቁት ሁለቱ ወገኖች ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ዶክተር አብይም ለክሪስ ስሚዝ በሀገሪቱ ያሉ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለዉጦች ላይ ማብራርያ ሰጥተዋቸዋል፡፡  

በትምህርት ሚኒስቴር ፍኖተ ካርታ ላይ የተካሄደዉ የሶስት ቀን ዉይይት ዉጤታማ እንደነበር ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ  በቲዉተር ገጻቸዉ ገለጹ፡፡

አርትስ 18/12/2010 ዶክተር ጥላዬ በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ የቀጣዩን 15 ዓመታት ፍኖተ-ካርታ ላይ በተደረገዉ ውይይት ፍኖተ ካርታዉን የሚያዳብሩ ሀሳቦች ተገኝተዉበታል ብለዋል፡፡ ምኒስትሩ አሁን ያለዉ ፍኖተ ካርታ በረቂቅ ደረጃ መሆኑን ማሳሰብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከቬትናሙ ፕሬዚዳንት ትራን ዳይ ኩአንግ ጋር ተወያዩ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በቲዉተር ገፃቸው አንዳስታውቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ   ፕሬዝዳንት ትራን ዳይኩአንግን በፅህፈት ቤታቸዉ ተቀብለዉ አነጋግረዋቸዋል፡፡ መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት ባህል፣ ኢኮኖሚ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡  በተጨማሪም በኢንቨስትመንት እና በቪዛ አገልግሎት ሁለቱ ሀገራት ተባብረው መስራት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡ የቬትናሙ ግሬዝደንት በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ […]

ትላንት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ስራ አስፈጻሚ ሆነዉ የተሾሙት ዶክተር አብርሃም በላይ ማን ናቸዉ?

አርትስ 18/12/2010 ዶክተር አብርሃም በላይ በ1972 ዓ.ም በአዲግራት የተወለዱ ሲሆን ፤ከ1991 ጀምሮ የኢፌድሪ መከላከያ ስራዊት አባል በመሆን እስከ ሌተናል ኮሌኔል ማዕረግ ደርሰዋል፡፡ከ1996-1998 ዓ.ም የመከላከያ ኢንጂነሪነግ ኮሌጅን በአሰተማሪነት አገልግለዋል፡፡ ከ19 98 ዓ.ም ጀምሮም በተለያዩ ሀላፊነቶች በኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግለዋል፡፡ ከ2007-2009 ባለዉ አመት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚመራ የሀገር አቀፍ የምርምር ካዉንስል ቴክኒካል አማካሪ አባል በመሆንም ዶክተር አብርሃም […]

ለኢቢሲ ለውጥና እድገት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ዶክተር መረራ ጉዲና ገለጹ።

ከመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳች ደረ-ገፅ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ዶክተር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል በመሆን እያገለገለሉ ይገኛሉ። ዶክተር መረራ ወደ ሀላፊነት ከመጡ ጀምሮ በተቋሙ ስብሰባዎች ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ገልጸዋል። በተቋሙ ያለው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሚያሰራ ነው ያሉት ዶክተር መረራ  እስካሁን ከቦርድ አመራር አባላት ጋር በነበራቸው ውይይት […]

የ 2010 የአሸንዳ በዓል ብዛት ያለዉ ቱሪስት የተገኘበት ነዉ ተባለ፡፡

አርትስ 18/12/2010 የዘንድሮዉ የአሸንዳ በዓል ከማነኛዉም ግዜ በበለጠ ከመላዉ አለም የመጡ ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን በስፋት የተሳተፉበትና ብዛት ያላቸዉ ኤርትራዊያን የተገኙበት መሆኑን የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ  ለአርትስ ቲቪ ገልጸዋል፡፤ የቢሮዉ ሃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት ስለነበርም ግብይቱ እንደተነቃቃ ነግረዉናል፡፡ለበዓሉ ማድመቂያ የሚሆኑ አልባሳት ሽያጭም ከፍተኛ እንደነበር ሰምተናል፡፡ከተለያዩ የሀገራችን አከባቢዎችም የመጡ የተለያዩ ብሄር […]

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳን ከአባልነት አግዷቸዋል፡፡

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ አሁን ባላቸው ወቅታዊ አቋም የአማራን ህዝብ ጥቅም እንደማያስጠብቁ በመረጋገጡና በጥረት ኮርፖሬት ላይ በሰሩት ጥፋት እስከ ሚቀጥለው የድርጅቱ መደበኛ ጉባኤ ድረስ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አግዷቸዋል፡፡