loading
ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የቦንድ ሳምንት  በማዘጋጀት 500 ሚሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዷል፡፡

ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የቦንድ ሳምንት  በማዘጋጀት 500 ሚሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዷል፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ከመጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሚኖረው የቦንድ ሳምንት 500 ሚሊዮን ብር ለማግኘት መታቀዱን ገለጸ። ለግድቡ ግንባታ በሰባት ወራት ጊዜ ውስጥ 400 ሚሊዮን ብር ብቻ መሰብሰቡን ያስታወሰዉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት […]

የሁሉም የተፋሰሱ አባል አገራት በአባይ የመጠቀምና የመልማት ተፈጥሯዊ መብትም እውቅና ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ገለጹ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 የሁሉም የተፋሰሱ አባል አገራት በአባይ የመጠቀምና የመልማት ተፈጥሯዊ መብትም እውቅና ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ገለጹ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት  ሣህለ ወርቅ ዘውዴ  ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት  ፖል ካጋሜ ጋር በኪጋሊ ተገናኝተው በሁለትዮሽና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡ ፕሬዝደንት ፓል ካጋሜ በዚህ ወቅት ባደረገት ንግግር በአባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል የሚደረገው የትብብር እንቅስቃሴ ከሁሉ በፊት […]

የአለም ባንክ ለአገራት የገንዘብ ድጋፍ ፈቀደ::

የአለም ባንክ ለአገራት የገንዘብ ድጋፍ ፈቀደ:: የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ቦርዶች ለሀገራት እና ኩባንያዎች ለለኮቪድ -19 መስፋፋት ለመከላከል ፣ ለመለየት እና ምላሽ ለመስጠት በሚያደርጉት ጥረት 14 ቢሊዮን ዶላር ለፈጣን ቁጥጥር ፋሲሊቲ እንዲጨምር ፈቀደ ፡፡በሳምንቱ መጨረሻ የዓለም ባንክ ለፈጣን ቁጥጥር 1ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በ 40 አገሮች ውስጥ ፕሮጀክቶችን እያዘጋጀ ነውም ተብሏል፡፡ በአፍጋኒስታን እና […]

በኬንያ በዓለም አቀፍ ተቋሞች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ያላቸውን ድጋፍ ገለፁ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 በኬንያ በዓለም አቀፍ ተቋሞች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ያላቸውን ድጋፍ ገለፁ:: በናይሮቢ በተባበሩት መንግስታትና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ማህበር (በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ በመደገፍ የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ መግለጻቸዉን በኬኒያ ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡ የማህበሩ አባላት በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ከመከሩ በኋላ ባወጡት የጋራ አቋም መንግስት […]