loading
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ብአዴን ወደፊት የሚመራባቸውን የፖለቲካ መስመሮች ለመወሰን እየመከረ ነው፡፡ 

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ይመራበት የነበረውን አብዮታዊ ዲሞክራሲ እናሻሽል ወይም አናሻሸል በሚሉ እና ሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው፡፡ በዋናነትም አብዮታዊ ዴሞክራሲን እናሻሽል ወይም አናሻሸል? በሚል መሰረታዊ የማሻሻያ ጉዳዮችይወያያል፡፡ የድርጅቱ ስያሜ እና ዓርማ የአማራን ህዝብ አይወክልም በመባሉም ይመከርበታል፡፡ ድርጅቱ ባለፉት ጊዜያት ይመራባቸው የነበሩ ህጎች አንዳንዶቹ ወቅቱን ያላገናዘቡ በመሆኑ ይመከርባቸዋል፡ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በክልሉ ካሉ አመራሮች የሰበሰባቸውን […]

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል 11 ዞኖች ከተውጣጡ የሴቶችና ወጣቶች ተወካዮች፣ ምሁራንና ከተለያዩ የአለም አገራት ከመጡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በክልሉ ወቅታዊና የለውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ እየተወያዩ ነው።

  ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል 11 ዞኖች ከተውጣጡ የሴቶችና ወጣቶች ተወካዮች፣ ምሁራንና ከተለያዩ የአለም አገራት ከመጡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በክልሉ ወቅታዊና የለውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ እየተወያዩ ነው። ምንጭ ኢቢሲ  

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት አለን አሉ ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ፡፡

  አርትስ 18/12/2010 የአሜሪካ ኮንግረንስ አባላት ልኡካን ቡድን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይቷል፡፡ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ ኮንግረንስማን ክሪስ ስሚዝ አሁን እየተካሄደ ያለው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ዕድገት ለምታደርገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀው […]

ዶክተር አብይ አህመድ ከአሜሪካዉ ኮንግርስ አባል ክሪስ ስሚዝ ጋር ተወያዩ፡፡

አርትስ 18/12/2010 የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጽህፈት ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በቲዉተር ገጻቸዉ እንዳስታወቁት ሁለቱ ወገኖች ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ዶክተር አብይም ለክሪስ ስሚዝ በሀገሪቱ ያሉ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለዉጦች ላይ ማብራርያ ሰጥተዋቸዋል፡፡  

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከቬትናሙ ፕሬዚዳንት ትራን ዳይ ኩአንግ ጋር ተወያዩ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በቲዉተር ገፃቸው አንዳስታውቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ   ፕሬዝዳንት ትራን ዳይኩአንግን በፅህፈት ቤታቸዉ ተቀብለዉ አነጋግረዋቸዋል፡፡ መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት ባህል፣ ኢኮኖሚ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡  በተጨማሪም በኢንቨስትመንት እና በቪዛ አገልግሎት ሁለቱ ሀገራት ተባብረው መስራት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡ የቬትናሙ ግሬዝደንት በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ […]

ለኢቢሲ ለውጥና እድገት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ዶክተር መረራ ጉዲና ገለጹ።

ከመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳች ደረ-ገፅ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ዶክተር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል በመሆን እያገለገለሉ ይገኛሉ። ዶክተር መረራ ወደ ሀላፊነት ከመጡ ጀምሮ በተቋሙ ስብሰባዎች ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ገልጸዋል። በተቋሙ ያለው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሚያሰራ ነው ያሉት ዶክተር መረራ  እስካሁን ከቦርድ አመራር አባላት ጋር በነበራቸው ውይይት […]

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳን ከአባልነት አግዷቸዋል፡፡

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ አሁን ባላቸው ወቅታዊ አቋም የአማራን ህዝብ ጥቅም እንደማያስጠብቁ በመረጋገጡና በጥረት ኮርፖሬት ላይ በሰሩት ጥፋት እስከ ሚቀጥለው የድርጅቱ መደበኛ ጉባኤ ድረስ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አግዷቸዋል፡፡

አዲሰ አባበ ውስጥ እያካሄደ ባለው የማጣራት ሥራ ባለቤት የሌላቸውን ሕንፃዎችና ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችን ማግኘቱን የከተማዋ አስተዳደር አስታውቋል።

አዲሰ አባበ ውስጥ እያካሄደ ባለው የማጣራት ሥራ ባለቤት የሌላቸውን ሕንፃዎችና ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችን ማግኘቱን የከተማዋ አስተዳደር አስታውቋል።