loading
ኢትዮጵያ የአጼ ቴዎድሮስን ሹርባ ከእንግሊዝ ለማስመለስ ጥያቄ አቀረበች፡፡

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1868 መቅደላ ላይ በኢትዮጵያና በእንግሊዝ መካከል በተደረገው ጦርነት የእንግሊዝ ወታደሮች ከዘረፏቸው ቅርሶች መካከል የአጼ ቴዎድሮስ ሹርባ ይገኝበታል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የንጉሱ ጉንጉን ጸጉር ለንደን ውስጥ በናሽናል አርሚ ሙዚየም ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ባለፈው ሚያዚያ ወር የአትዮጵያ አምባሳደር ሙዚየሙን ከገጎበኙ በኋላ የይመለስን ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ለጊዜው ለጎብኝዎች እይታ ከተቀመጠበት ቦታ ገለል ተደርጓል ሲል ዘ ጋርዲያን […]

በትግራይ ክልል በመኾኒ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 425 ተቀጣጣይ ፈንጅ ተያዘ።

ተቀጣጣይ ፈንጁ 75 ኪሎ ግራም ክብደት ሲኖረው መኾኒ ከተማ ልዩ ስሙ ገረብ አባ ሃጎስ በተባለ ስፍራ የተያዘ ነው ተብሏል። ፈንጁ ድልድይ ስር ተደብቆ ወደ መቐለ ከተማ ሊሻገር ሲል በህዝቡ ጥቆማ መያዙንም የትግራይ ክልል የህዝብና የመንግስት ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል።ፋና እንደዘገበዉ

የቀድሞ የአፋር ክልል ፕሬዝደንት የነበሩት ሱልጣን ሀንፍሬ አሊ ሚራህ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

በሱልጣን ሐንፈሬ አሊ ሚራህ የሚመራውና በስደት በውጭ አገራት ሲኖሩ የነበሩ ልኡካን ቡድን አባላት ዛሬ አዲስ አበባ መግባቱን ኢብኮ ዘግቧል፡፡ ከአፋር ህዝብ ፓርቲ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ፣ከአፋር ሰብዓዊ መብት አቶ ጋአስ አህመድ እና ከአፋር ነፃ አውጪ ግንባር አቶ ኡመር አሊሚራህ ይገኙበታል፡፡ ልኡካኑ አዲስ አበባ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዲሪ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የአፋር ብሄራዊ […]

ከአዲስ አበባ የተለያዩ የጤና ተቋማት የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች በጅግጅጋ ጉዳት ለደረሰባቸው 128 ሰዎች የህክምና አገልግሎት ሰጡ፡፡

የህክምና ቡድን መሪ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ትላንት አመሻሽ ላይ ከጅግጂጋ ሲመለሱ በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ላይ ተገኝተው እንደገለጹት ቡድኑ በስምንት ቀን ቆይታው ለ128 ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች የህክምና አገልግሎት ድጋፍ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ ከተጎጅዎቹ መካከልም ግማሽ ያህሎቹ የጭንቅላት፣ የደረት፣ የሆድና የደረት ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገላቸው መሆኑን ዶ/ር ብርሃኑ ገልጸዋል፡፡ የህክምና ቡድኑ ወደ ጅግጂጋ ከማቅናቱ በፊትም በድሬዳዋ ከተማ […]

ከ12 ከተሞች ተገልጋዮች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በሚሰጠው አገልግሎት አልረካንም አሉ፡፡

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ከዋልታ ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባበር በከተሞች የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ ከተሞች የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ቅንጅታዊ አሰራር ሊከተሉ ይገባል ተብሏል፡፡ ከተሞቻችን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር እጦት የሰፈነባቸው የምሬት ማዕከል ሆነዋል ያሉት የከተማ ልማትና ቤቶች ሚንስትር አቶ ጃንጥራር አባይ፤ በአመራሮችና ፈጻሚዎች ድክመት፣ የብቃት ችግር ፣ቀልጣፋና ፍትሃዊ […]

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ።

ልዑኩ ወደ ሀገር ቤት የመጣውም በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መካከል ባሳለፍነው ነሃሴ 1 2010 ዓ.ም የእርቅ ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ነው። ልዑኩ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም የኦህዴድ የከተማ ፖለቲካና የድርጅት ዘረፍ ሀላፊ አቶ ከፍያለው አያና እናሌሎች የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውለታል። የልዑካን ቡድኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስራ አስፈጻሚ […]

ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ፡፡

በኮንስትራክሸን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በዋና ዳይሬክተርነት እንዲሁም በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮንትራት አስተዳደር እና በምህንድስና ግዢ ላይ በሃላፊነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ኃላፊው በቅርቡ የኢትዮጲያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙትን እና የቀድሞ የተቋሙን ኃላፊ ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝን በመተካት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ይመራሉ፡፡ የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት እንዳስታወቀው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ እና በከተማዋ የመንገድ መሰረተ […]

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር በጅቡቲ ተወያዩ።

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፥ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት በሁኔታዎችና በአጋጣሚ የማይለወጥ ስትራቴጂካዊ ወዳጅነት ነዉ ብለዋል፡፡ ዶክተር ወርቅነህ፥ በድሬዳዋ በተፈጠረው ክስተት የጅቡቲ ዜጎች ህይወታቸውን በማጣታቸው ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ የተፈጠረው ክስተት የሁለቱን ህዝቦች አጠቃላይ ግንኙነት አያሳይም ያሉት ዶክተር ወርቅነህ፥ ጥፋተኞቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ በመሆኑ በሕግ ተገቢውን […]