loading
በድሬዳዋ ግጭት በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 54 ግለሰቦች ክሳቸው ተቋርጦ ሊለቀቁ ነው

አሁን በደረሰን ዜና በድሬዳዋ ከነበረው ሁከትና ግጭት በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 54 ተጠርጣሪዎች ከህብረተሰቡ ጋር ከሚካሄድ ውይይት ጋር ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ሊለቀቁ መሆኑን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። ኮሚሽኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው ከሚለቀቁት ተጠርጣሪዎች ጋር ውይይት ይካሄዳል። በትናንትናው ዕለት  32 ተጠርጣሪዎች በተመሳሳይ  ምርመራቸው ተቋርጦ ከእስር የተፈቱ መሆኑ ይታወሳል። በቀጣይ ቀናትም እየተጣሩ ያሉ የምርመራ […]

ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ስልጠናውን የሰጠው ከፌደራል፣ከክልሎች እና ከከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ 70 የስራ ስምሪት ባለሙያዎች ነው። በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ብርሀኑ አበራ እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ ለሥራ ወደ ውጭ ሀገር ሄደው መስራት የሚፈልጉ ዜጐች ህግና ሥርዓትን ተከትለው በመሄድ በሚሰሩበት አገር መብታቸው፣ ደህንነታቸውና […]

ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ እና ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ አዲስ ለተቋቋመው የብሔራዊ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን  ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ ሆነዉ ተሾሙ፡፡

ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ እና ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ አዲስ ለተቋቋመው የብሔራዊ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን  ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ ሆነዉ ተሾሙ፡፡

የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላት ወኪልነታቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ለመጡበት ተቋምና ማንነት አይደለም ተባለ

የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላት ወኪልነታቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ለመጡበት ተቋምና ማንነት እንዳልሆነ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ። ኮሚሽኑ በጥናት ላይ የተመሰረተና ትውልድ ተሻጋሪ ተግባር እንዲያከናውን ጥሪ ያቀረቡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስራው ላይ መንግስታዊ ጣልቃገብነት እንደማይኖርበትም አረጋግጠዋል። ከአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላት ጋር የተካሄደውን የመጀመሪያ የትውውቅና የስራ ምክክር መድረክ የመሩት ምክትል ጠቅላይ […]

“የሴት ልጅ ግርዛትን የማይታገስ ህብረተሰብ እንፍጠር!” በሚል አገራዊ መሪ ቃል የሚከበረዉ የንቅናቄ መድረክ በይፋ ተከፍቷል

“የሴት ልጅ ግርዛትን የማይታገስ ህብረተሰብ እንፍጠር!” በሚል አገራዊ መሪ ቃል የሚከበረዉ የንቅናቄ መድረክ በይፋ ተከፍቷል፡   የንቅናቄዉ ዋና ዓላማ በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን የመብት ጥሰት ለማስቆም የሚረዱ ምክረ ሃሳቦች ላይ በመወያየት ድርጊቱን ለማስቆም የሚካሄደውን ጥረት ማጠናከር ነዉ ብሏል የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር፡፡   ሃዋሳ ከተማ ላይ በተጀመረውና ለሚቀጥሉት አራት ቀናት በሚቆየው በዚሁ መድረክ ላይ የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ […]