loading
የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ መቀመጫዉን አስመራ ካደረገዉ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ (አዲኃን) ጋር ይወያያሉ፡፡

አዲኃን ባለፉት ስምንት ዓመታት መቀመጫውን ኤርትራ አድርጎ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስርዓት በመቃወም የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የነበረ የፖለቲካ ፓርቲ ነዉ፡፡ የአማራ መገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቀዉ አዲኃን ከመንግስት ጋር የሚያደርገዉ ድርድር ምን ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር አስካሁን አልታወቀም፡፡ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ትላንት አስመራ መግባታቸዉ ይታወሳል፡፡

ባለፉት ዓመታት በተጠርጣሪዎችና በታራሚዎች አያያዝ ላይ ያሉ ችግሮች መሻሻል አልታየባቸውም ተባለ::

ይህን ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ከሚሽን በቢሸፍቱ ከተማ ለፌደራልና ክልል የጸጥታ ተቋማት ሀላፊዎች ባዘጋጀዉ ስልጠና ላይ ነዉ ። ስልጠናው በአትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን ማክበርና ማስከበር ላይ ያተኮረ ሲሆን ለአምስት ቀናት የሚሰጥ ነው ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሄር ስልጠናዉን ሲከፍቱ ሰልጣኞቹ ሰብዓዊ መብት መከበርና ማስከበር ላይ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል ። ስልጠናው […]

የተሽከርካሪ አደጋ አስከፊ እየሆነ በቁጥርም እያሻቀበ ነው፡፡

በአገራችን 2010 ዓ.ም 40ሺህ 998 የተሸከርካሪ አደጋ ደርሷል፡፡ 5ሺህ 118 ሰዎች በተሸከርካሪ አደጋ ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል፡፡ 7ሺህ 754 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 7ሺህ 775 ሰዎች ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከ 920 ሚሊዮን 771 ሺህ ብር በላይ የተገመተ ንብረት ወድሟል፡፡ ባለፈው ዓመት 2009ዓ.ም የደረሰው አደጋ 38ሺህ 737 ነበር፡፡ አቶ ይግዛው ዳኘው የትራንስፖርት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት […]

ዓለም አቀፍ የሴቶች እና ወጣቶች የሰላም ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ ተካሄደ

የሰላም ኮንፍረንሱ የተካሄደው በአዲስ አበባ የኢሲኤ አዳራሽ ነው፡፡ አለም አቀፍ የሴቶችና ወጣቶች የሰላም ኮንፈረንስ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ስለሰላም የሚያወሳ አጫጭር ጹሁፎችን አቅርበዋል። ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሴቶች እና ወጣቶች ለሰላም መረጋገጥ […]

የትግራይ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስድስተኛ ሙት አመትን በማስመልከት ሀገራዊ የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱን ገለፀ፡፡

የውይይት መድረኩ የፊታችን እሑድ ነሐሴ 13 ቀን ይካሔዳል፡፡ በትግራይ ክልል የፖሊሲ ጥናት ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፍሰሃ ሀብተ ፂዮን እንደተናገሩት የውይይት መድረኩ የመለስ ዜናዊ ስራዎች ላይ የሚያተኩር ሲሆን የሃገሪቱ የህዳሴ ጉዞ እንዲሁም ወቅታዊ ሁኔታዎች ይዳሰሱበታል፡፡ የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ ዶ/ር ፍሰሀ በመድረኩ ነባር እና አዲስ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ምሁራን፣ፖለቲከኞች፣የተለያዩ ድርጅት ተወካዮች እነዲሁም የመቀሌ ከተማ እና […]

ከ92 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዘ፡፡

ቪኦኤ እንደዘገበዉ ሌሎች የተለያዩ የውጭ ሀገር የገንዘብ ኖቶችን ጨምሮ ከ92 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር ነዉ የተያዘዉ። በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 92 ሺህ 100 የአሜሪካ ዶላር፣ 13 ሺህ ዩሮ፣ 17 ሺህ የአረብ ኢሚሬት ድርሃም እና 52 ሺህ 600 የኢትዮጵያ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም መኮንን ገልጸዋል። የገንዘብ […]

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገር ቤት ሊገባ ነዉ፡፡

ቪኦኤ እንደዘገበዉ አትሌት ፈይሳ በቅርቡ ቤተሰቡን ይዞ ወደ ሀገር ቤትለመመለስ ወስኗል፡፡ ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በጋራ ባወጡት መግለጫ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ወደ ሀገሩ እንዲመለስ መጋበዛቸዉ ይታወሳል፡፡በወቅቱም ለአትሌቱ የጀግና አቀባባል እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2010 በጀት ዓመት ካቀድኩት ማሳካት የቻልኩት 49.5 በመቶ ብቻ ነዉ አለ፡፡

አገልግሎቱ ለ468 ሺህ ደንበኞች ኤሌክትሪክ ለማዳረስ አቅዶ ለ231 ሺህ 781 ደንበኞች ብቻ ነው ኤሌክትሪክ ማድረስ የቻልኩት ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2010 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2011 በጀት አመት ዕቅድን ዛሬ ባቀረበበት ወቅት የተቋሙ ምክትል ስራ አስፈጻሚና የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ብዙወርቅ ደምሰዉ ኃይል በማምረት ደረጃ ሰፊ ስራዎችን ማከናወን ቢችልም ለተጠቃሚዎች በማዳረስ ረገድ […]

የአማራ ክልል ልዑክ በአስመራ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ጋር ምክክር ጀመረ፡፡

አዴኃንና የአማራ ክልል መንግስት የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የዉይይታቸዉ ሀሳብ ነዉ፡፡ አዴኃን ወደ ሀገሩ ገብቶ በሰላም እንዲንቀሳቀስና ጥሩ አጋር ሆኖ እንዲሰራ የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግለትም ገልጧል ልዑኩ፡፡ የልኡኩ አባል የአማራ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን የኤርትራ መንግስት ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ያሳየውን አጋርነት ማድነቃቸዉን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡ የኤርትራ ውጭ […]