loading
የአሸንዳ ክብረ በአል ከባህላዊ እሴትነቱ ባሻገር ለነጋዴዎች የገቢ ማስገኛ መንገድ ነው ።

አርትስ ቲቪ በመቀሌ ከተማ ያነጋገራቸው ነጋዴዎች በአሸንዳ በአል ነጋዴዎች ልጃገረዶች የሚለብሷቸውን ባህላዊ አልባሳት፣ፀጉርላይ የሚታሰሩ (እንቁ)የሚባሉ ማጌጫዎች ፣ በቀሚስ ላይ የሚደረግ የተገመደ ክር (ድሪ) የአንገትና የጆሮ ጌጣጌጦች በአዘቦቱ ቀን ከሚሸጡበት የ20 እና 30 ብር ጭማሪ አንዳለው ነው የተናገሩት። በአሉን ልጃገረዶች በተለየ መንገድ ስለሚያከብሩት የፀጉር ባለሙያዎችንም ትርፋማ የሚያደርግ እንደሆነ ተመልክተናል ።

በነገው እለት የሚከበረውን የአሸንዳ በአል አስመልክቶ በመቀሌ ከተማ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የፓናል ውይይቱ አብይ አላማ ያለፉት አመታት የበዓሉን አከባበር መገምገም፣አሸንዳን በአለም አቀፍ ደረጃ ስለማስተዋወቅ እንዲሁም ከዩኔስኮ ጋር የተያያዙ ጥናቶች እና ሀሳቦችን ማንሳት ነው ተብሏል፡፡ የትግራይ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ዘነቡ ሐለፎም እንደገለፁት አሸንዳ ከባህላዊ እና ሃይማኖታዊ አንድምታው በተጨማሪ ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር እንዲሁም ፖለቲካዊ ተሳትፎአቸውን የሚያሳይ የነጻነት ቀን ነው ብለዋል፡፡ በውይይቱ የቀደሙ […]

ተወረወረች ጨረቃ …በመድሃኒዓለም ጫንቃ

ተወረወረች ጨረቃ በመድሃኒዓለም ጫንቃ . ይሄ አዳራሽ ….ኧኸ የማን አዳራሽ የጌታዬ ድርብ ለባሽ። . ይኸው ሲዞር ወገቧ ባቄላ ነው ቀለቧ . ይሄው ወገቤ ነጭ ጤፍ ነው ቀለቤ። በሚለው የልጃገረዶች ጨዋታ ለሚደምቀው አሸንድዬ በላሊበላ ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በአዲስ አበባ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ዛሬ ነፃ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከዘመን እና ሞጋቾች ድራማ ጋር በመሆን ፥ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት ድረስ በመዲናዋ ጎዳና ላይ የሚገኙ ሰዎች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋሉ። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ወር በገባ በ16ኛው ቀን በቀጣይነት እንደሚሰጥ እና ወደ ሌሎች ከተሞችም ለማስፋት መታቀዱን የዘመን ድራማ ደራሲ አቶ መስፍን ጌታቸው ተናግረዋል። ሰኔ 16 ቀን በአዲስ አበባ […]

በመሬት፣ በቀበሌ ቤቶች፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በህንፃዎች ላይ የኦዲት ሥራ በመስራት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት በከተማ አስተዳደሩ እስካሁን የነበሩ ተግባራትን ቆም ብሎ በማየት ሀገራዊ ለዉጡን ለማስቀጠል በመሬት፣ በቀበሌ ቤቶች፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በህንፃዎች ላይ የኦዲት ሥራ እየተሰራ ነዉ፡፡ ምክትል ከንቲባዋ ˝የአዲስ ተስፋ ቀመር˝ በሚል መሪ ቃል አዲሱን ዓመት ለማክበር ጥላቻን በመቀነስ (-)፣ ያለንን በማካፈል (÷)፣ […]

በፍቅር እንደመር በይቅረታ እንሻገር በሚል መሪ ቃል ጳግሜ 5 ቀን የአዲሱን አመት መግቢያ በማስመልከት አዲስቷን ኢትዮጵያን ለመገንባት ቃል የመግባት ፕሮግራም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳች ፅህፈት ቤት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሣሁ ጎርፌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በዝግጅቱ አድስቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚያስችለንን ቃል የምንገባበት ከመሆኑም በላይ በሁለም የህብረተሰብ ከፍል እና በመላው ሀገሪቱ የመነቃቃት ስሜት በሚፈጠርበት በመደመር ስሜት በውጭ ሀገር የሚኖሩትን ጨምሮ አዲሲቷ ኢትዮጵያ በጋራ የምንገነባበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በዝግጅቱ ከ 2 መቶ በላይ ኤርትራውያን ለመጋበዝ ከውጭ ጉዳይ ጋር በጋራ በመሆን […]

የአቃቂ ግድብ መሙላት አደጋ ስለሚያስከትል የማስተንፈስ ስራ አሁንም ይቀጥላል ተባለ፡፡

ይህንን ያለዉ የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ነዉ፡፡ በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሄደት መሪ አቶ እስጢፋኖስ ብስራት ለአርትስ ቲቪ በትላንትናው ዕለት አቃቂ አካባቢ የደረሰውን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ በተለያዩ ማህበራዊ ድረገፆች ላይ የአቃቂ ግድብ ሞልቶ ለማስተንፈስ በተደረገ ጥረት ውስጥ ቸግሩ እንደተከሰተ እና የሚመለከተውም አካል ማስጠንቀቄያ እንዳልተሰጠ ተደርጎ ሲነገር የነበረዉ ሀሰት ነዉ ብለዋል፡፡፡ በክረምት ሁሌ የማስተንፈስ ስራ […]

ትላንት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ስራ አስፈጻሚ ሆነዉ የተሾሙት ዶክተር አብርሃም በላይ ማን ናቸዉ?

አርትስ 18/12/2010 ዶክተር አብርሃም በላይ በ1972 ዓ.ም በአዲግራት የተወለዱ ሲሆን ፤ከ1991 ጀምሮ የኢፌድሪ መከላከያ ስራዊት አባል በመሆን እስከ ሌተናል ኮሌኔል ማዕረግ ደርሰዋል፡፡ከ1996-1998 ዓ.ም የመከላከያ ኢንጂነሪነግ ኮሌጅን በአሰተማሪነት አገልግለዋል፡፡ ከ19 98 ዓ.ም ጀምሮም በተለያዩ ሀላፊነቶች በኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግለዋል፡፡ ከ2007-2009 ባለዉ አመት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚመራ የሀገር አቀፍ የምርምር ካዉንስል ቴክኒካል አማካሪ አባል በመሆንም ዶክተር አብርሃም […]