loading
በአማራና ትግራይ ህዝቦች መካከል ግጭትም ይሁን የግጭት ፍላጎትም  የለም አሉ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች

በአማራና ትግራይ ህዝቦች መካከል ግጭትም ይሁን የግጭት ፍላጎትም  የለም አሉ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ። ርዕሳነ መስተዳደሮቹ ይህንን ያሉት የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተለያዩ አከባቢዎች ሲያደርጉት በነበረውን የሰላም ጉዞ ማጠቃለያ መድረክ ላይ ተገኝተው ነው፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በጋራ […]

በአማራ ክልል የሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

በአማራ ክልል የሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የኮሚሽኑ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ አህመድ እንደገለጹት የጥምቀት በዓል ሠላማዊ ሆኖ እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በዓሉ በአደባባይ የሚከበር በመሆኑ ከተለመደው ጊዜ የተለየ እና የተጠናከረ ጥበቃ ይደረጋልም ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ፡፡ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ወንጀል የሚፈጽሙ አካላትን ለመቆጣጠር […]

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስደተኞች ጉዳይ አዋጅን አፀደቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስደተኞች ጉዳይ አዋጅን አፀደቀ። ምክር ቤቱ 19ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደ ሲሆን፥ በውይይቱ በቀረቡለት ሁለት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል። በዚህም ምክር ቤቱ የህግ፣ ፍትህና ዴሞከራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ተመልክቷል። ረቂቅ አዋጁ ኢትዮጵያ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ […]

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ያደረገውን ዝግጅት አጠናቅቆ ከዛሬው ከተራ በዓል ጀምሮ ወደ ስራ ገብቷል። ፖሊስ ኮሚሽኑ ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ፣ ከሌሎች የፀጥታ እና የፍትህ አካላት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በጋራ ስራ መጀመሩንም አስታውቋል። በዓላቱ በሰላም ተጀምረው […]

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤትን ገበኙ።

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤትን ገበኙ። በጉብኝቱ ወቅትም በትምህርት ቤቱ አሉ በተባሉ ችግሮች ዙሪያ እና በመፍትሄዎቻቸው ላይ ምክክር አድርገዋል። በውይይቱ ላይ የተማሪዎች ማደሪያ ክፍል የትምህርት ቁሳቁስ፣ የተማሪዎች ወንበር እና የቤተ ሙከራ መሳሪያዎች እንዲሁም የህክምና ተቋም ቸግሮች ተነስተዋል። ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው  በውይይቱ ወቅት በተነሱ ችግሮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር […]

የህጻናትን ጤንነት ላይ መንከባከብ ሀገርን የማስቀጠል ዋስትና መሆኑን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ

የህጻናትን ጤንነት ላይ መንከባከብ ሀገርን የማስቀጠል ዋስትና መሆኑን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ። ፕሬዚዳንቷ ይህን ያሉት በኪዩር ኢትዮጵያ ሆስፒታል የ10ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ በተገኙበት ወቅት ነው። ኪዩር ኢትዮጵያ ከረጂ ድርጅቶችና ከኢትዮጵያውያን በጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር ባለፉት 10 ዓመታት ከጡንቻና ከአጥንት ችግር ጋር በተያየዘ አካል ጉዳተኛ ሆነው ለተወለዱ ህፃናት 17 ሺህ የህፃናት ቀዶ ህክምና ማድረጉን ያሳወቀ […]