loading
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ያለውን ልማት እንደሚደግፍ ገለጸ

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ያለውን ልማት እንደሚደግፍ ገለጸ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በዳቮስ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዜዳንት ፒተር ማዉረር ጋር ተወያይተዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች በታየው ለውጥ ምክንያት ተስፋ መታየቱን ተናግረው ዓለም አቀፉ የቀይ […]

የመንግስት ንግድ ቤት ተከራዮች የቤቶች ኮርፖሬሽን የወሰነውን የዋጋ ጭማሪ  በድጋሚ እንዲያጤንላቸው መንግስትን ጠየቁ

የመንግስት ንግድ ቤት ተከራዮች የቤቶች ኮርፖሬሽን የወሰነውን የዋጋ ጭማሪ  በድጋሚ እንዲያጤንላቸው መንግስትን ጠየቁ፡፡ ነጋዴዎቹ ይህን የጠየቁት ዛሬ በግሎባል ሆቴል አዳራሽ ባደረጉት የጋራ ውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡ በውይይታቸውም ለቤት ኪራይ የተወሰነው ውሳኔ በበቂ ጥናት ላይ ያልተመሰረተ እና በቂ ባለሙያዎችን ያሳተፈ አይደለም ብለዋል፡፡ አቋማችን ጭማሪው አይደረግ የሚል ሳይሆን ተመጣጣኝ ጭማሪ ይደረግ የሚል ነው ብለዋል፡፡ ውሳኔው ነጋዴዎቹ ከቤታቸው […]

በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ እሳት ተቀሰቀሰ

በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ እሳት ተቀሰቀሰ። በደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ዞን የሚገኘው የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ ትናንት ማምሻውን መነሻው ያልታወቀ ሰደድ እሳት መቀስቀሱ ታውቋል። ሰደድ እሳቱ በተለይም የእግዜር ድልድይ የሚሰኙትን ሰንሰለታማ ተራሮች እየተዛመተ ነው ተብሏል። በአካባቢው የሚገኙ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት  በፓርኩ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት በንፋስ ምክንያት በስፋት በመዛመት ላይ ሲሆን ጉዳቱን ለመቀነስ የመከላከያ ሰራዊት አባላት […]

የሀገር ሽማግሌዎቹ በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት ተስማሙ

የሀገር ሽማግሌዎቹ በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት ተስማሙ። ሰሞኑን በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች መስማማታቸው ተገለጸ። በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣  የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በውይይቱም የተፈጠረውን ግጭት  ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና […]

17ኛው የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ቀን በጂንካ ከተማ እየተከበረ ነው

17ኛው የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ቀን በጂንካ ከተማ እየተከበረ ነው።  በክብረ በዓሉ ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፤ የሰላም ሚንስትሯ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። በዚህ በ17ኛዉ የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ቀን በሚከበርበት ወቅት በጂንካ የተገኙት  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአርብቶ አደሩ አካባቢ የመልማት ግብን ለማሳካት መንግስት ውኃን መሰረት አድርጎ እንደሚሰራ  ተናገረዋል፡፡ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የአለም አቀፍ አሰላሳዮች  መድረክ ተሸላሚ ሆኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የአለም አቀፍ አሰላሳዮች  መድረክ ተሸላሚ ሆኑ፡፡ የአለም አቀፍ የአሳቢዎች መድረክ (Global Thinkers Forum) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ተሸላሚ ያደረጋቸው ከፍተኛ የሆነ የማሰብ ችሎታቸውን በመጠቀም ሃላፊነታቸውን በብቃት ተወጥተዋል ብሎ ነው። በ2012 የተመሰረተው ይኸው ለግለሰቦችና መሪዎች እውቅናና ሽልማት የሚሰጠው  አለም አቀፍ የሽልማት ድርጅት በ24 በተለያዩ ዘርፎች በ2019 ተሸላሚ ናቸው ካላቸው ግለሰቦችና […]

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን ጎበኙ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን ጎበኙ ፕሬዚዳንቷ በጉብኝታቸው ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ከ60 ሽህ በላይ የሚሆኑ ወጣት ኢትዮጵያዊያንን በማከም ከፊስቱላ ህመም መፈወስ የቻለ አንጋፋ ድርጅት ነው ብለዋል። በተጨማሪም ድርጅቱ ንፁህና ሳቢ ተቋም መስርቶ ከሚሰጠው ዘመናዊ ህክምና ባለፈ አዋላጅ ነርሶችን በብቃት እያሰለጠነ ለሌሎች የህክምና ተቋማት ጭምር ከፍተኛ ደጋፍ በማድረግ ላይ የሚገኝ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለውለታ […]