loading
የኢንጂነር ስመኘው ቤተሰቦች የምርመራው ውጤት በምንፈልገው ፍጥነት እየሄደ አይደለም አሉ፡፡

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ባልታወቀ ምክንያት ህይወታቸው አልፎ ከተገኘ ሁለት ሳምንታት አለፉ። ቢቢሲ እንደዘገበዉ የኢንጂነር ስመኘው ባለቤት የወ/ሮ ዕሙን ጌታሁን ታናሽ ወንድም የሆነው አካሉ ጌታሁን ”ሃዘናችን እጅግ ከባድ ቢሆንም እየበረታን ነው። ከቀብሩ ጀምሮ መንግሥት እየደገፈን ነው። ምንም ያወጣነው ወጪ የለም” ብሏል። አካሉ ጨምሮም […]

ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ 11 የፖሊስ አመራሮች በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም አቃቤ ህግ አስታወቀ

ሰኔ 16ቱ የመስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የአመራርነት ክፍተት አሳይተዋል ተብለው ምርምራ እየተካሄደባቸው የሚገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በዋስ ቢለቀቁ አቃቤ ህግ እንደማይቃወም ገለጸ፡፡ አቃቤ ህግ ምክትል ኮሚሽነሩን ጨምሮ ሌሎች 11 የፖሊስ አመራሮችም በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም አስታውቋል፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎትም በጉዳዩ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ መስጠቱ ተገልጿል፡፡ […]

አቶ ጀዋር መሀመድ በሻሸመኔ የተፈጸመዉን ድርጊት አወገዘ፡፡

በሻሸመኔ ከተማ ለሰዉ ህይወት መጥፋትና የአካል መጉደል ምክንያት የሆኑ ግለሰቦች ለህግ እንዲቀርቡም በፌስቡክ ገጹ ጠይቋል፡፡ አቶ ጀዋር የሻሸመኔ ህዝብ በታላቅ አክብሮትና ፍቅር ተቀብሎናል፤ነገርግን በከተማዋ ሊቀበለን የወጣዉ ህዝብ ቁጥር ከተጠበቀዉ በላይ በመሆኑና በህዝቡም መካከል ሀሰተኛ መረጃ በመሰራጨቱ ምክንያት የሰዎች ህይወት አልፏል፤ አካል ጉዳትም ደርስዋል ፤ በዚህም በጣም ማዘኑን ተናግሯል፡፡ ተጨባጭ ባልሆነ መረጃ ንጹህ የሆነ ሰዉን መጉዳት […]

የኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች በሀገሪቱ የተከሰቱ ግጭቶች እና እየተባባሰ የመጣውን ስርዓት አልበኝነትን አጥብቀን እናወግዛለን አሉ፡፡

የሀይማኖት አባቶቹ ይህንን ያሉት የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነዉ፡፡ የሃይማኖት አባቶቹ በቅርቡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጅጅጋ ከተማ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የሰው ህይወት መጥፋቱ እና አብያተ ክርስቲያናት መቃጠል የትኛውንም ሃይማኖት የማይወክል ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ነዉ ብለዋል፡፡ በተያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው ስርዓት አልበኝነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት የሃማኖት አባቶቹ […]

የቡሄ ባህል መሰረታዊ ይዘቱን መቀየሩ አሳስቦኛል አለ::

ይህንን ያለዉ የአዲስ አበባ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ነዉ፡፡ በባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የጋራ ባህል እሴትዳይሬክተር አቶ አለማየው ጌታቸው የቡሄ ባህል መሰረታዊ ይዘት እየተቀየረ መምጣቱንና ስነቃሎቹም ላይ ጥናት ሊደረግ መሆኑን ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ባህል እና ቱሪዝም ቡሄን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማደረጉን ገልፀው በመጪው ቡሄ ስነቃላዊ ጥናቶችን ለማድርግ በፌደራል ደረጃ መስሪያ ቤቱ […]

በቢሾፍቱ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለፋና እንደተናገሩት ፥ አዲስ የሚገነባውን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማስጀመር እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። አውሮፕላን ማረፊያውን ለመገንባት የሚያስፈልገውን የቦታ ጥያቄ ለመፍታት ከኦሮሚያ ክልል ጋር ምክክር እየተደረገ መሆኑን አቶ ተወልደ ተናግረዋል። ሊገነባ የታሰበው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ […]

ኢትዮጵያ የአጼ ቴዎድሮስን ሹርባ ከእንግሊዝ ለማስመለስ ጥያቄ አቀረበች፡፡

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1868 መቅደላ ላይ በኢትዮጵያና በእንግሊዝ መካከል በተደረገው ጦርነት የእንግሊዝ ወታደሮች ከዘረፏቸው ቅርሶች መካከል የአጼ ቴዎድሮስ ሹርባ ይገኝበታል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የንጉሱ ጉንጉን ጸጉር ለንደን ውስጥ በናሽናል አርሚ ሙዚየም ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ባለፈው ሚያዚያ ወር የአትዮጵያ አምባሳደር ሙዚየሙን ከገጎበኙ በኋላ የይመለስን ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ለጊዜው ለጎብኝዎች እይታ ከተቀመጠበት ቦታ ገለል ተደርጓል ሲል ዘ ጋርዲያን […]

በትግራይ ክልል በመኾኒ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 425 ተቀጣጣይ ፈንጅ ተያዘ።

ተቀጣጣይ ፈንጁ 75 ኪሎ ግራም ክብደት ሲኖረው መኾኒ ከተማ ልዩ ስሙ ገረብ አባ ሃጎስ በተባለ ስፍራ የተያዘ ነው ተብሏል። ፈንጁ ድልድይ ስር ተደብቆ ወደ መቐለ ከተማ ሊሻገር ሲል በህዝቡ ጥቆማ መያዙንም የትግራይ ክልል የህዝብና የመንግስት ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል።ፋና እንደዘገበዉ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ ይገኛሉ፡፡

የ2010 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ባለድሉ ጅማ አባጅፋር እ እንደ ኦኪኪ አፎላቢ እና መሰሎቹ ወደ ሌላ ክለብ ማምራታቸውን ተከትሎም የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት እስካሁን በአጠቃላይ 11 ያህል ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል፡፡ በትላንትናው ዕለትም ከረጅም ዓመታት ቆይታ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተሰናበቱት አሉላ ግርማ እና ዘሪሁን ታደለ በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ቡናው አስቻለው ግርማ ጅማ አባጅፋርን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ሁነዋል። ወደ ዋናው […]