loading
የቀድሞ የአፋር ክልል ፕሬዝደንት የነበሩት ሱልጣን ሀንፍሬ አሊ ሚራህ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

በሱልጣን ሐንፈሬ አሊ ሚራህ የሚመራውና በስደት በውጭ አገራት ሲኖሩ የነበሩ ልኡካን ቡድን አባላት ዛሬ አዲስ አበባ መግባቱን ኢብኮ ዘግቧል፡፡ ከአፋር ህዝብ ፓርቲ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ፣ከአፋር ሰብዓዊ መብት አቶ ጋአስ አህመድ እና ከአፋር ነፃ አውጪ ግንባር አቶ ኡመር አሊሚራህ ይገኙበታል፡፡ ልኡካኑ አዲስ አበባ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዲሪ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የአፋር ብሄራዊ […]

ከአዲስ አበባ የተለያዩ የጤና ተቋማት የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች በጅግጅጋ ጉዳት ለደረሰባቸው 128 ሰዎች የህክምና አገልግሎት ሰጡ፡፡

የህክምና ቡድን መሪ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ትላንት አመሻሽ ላይ ከጅግጂጋ ሲመለሱ በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ላይ ተገኝተው እንደገለጹት ቡድኑ በስምንት ቀን ቆይታው ለ128 ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች የህክምና አገልግሎት ድጋፍ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ ከተጎጅዎቹ መካከልም ግማሽ ያህሎቹ የጭንቅላት፣ የደረት፣ የሆድና የደረት ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገላቸው መሆኑን ዶ/ር ብርሃኑ ገልጸዋል፡፡ የህክምና ቡድኑ ወደ ጅግጂጋ ከማቅናቱ በፊትም በድሬዳዋ ከተማ […]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀጅ ተጓዦች ላይ የተፈጠረውን የበረራ መስተጓጎል ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ የሀጅ ተጓዦች በረራቸው ተሰርዞ በአየር መንገድ ውስጥ ያለ በቂ ምግብና ማረፊያ እየተጉላላን ነው ብለዋል፡ ይህን ተከትሎ አቢሲ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ስልክ ደውሎ ስለ ሁኔታው ለማጣራት ቢሞክርም አየር መንገድ ስለ ጉዳዩ በፌስ ቡክ ገፁ ካወጣው መረጃ ተጨማሪ የሚሰጠው መረጃ እንደሌለው የህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል፡፡ አየር መንገዱ በፌስ ቡክ ገፁ ባወጣው መግለጫ በሀጅ […]

ከ12 ከተሞች ተገልጋዮች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በሚሰጠው አገልግሎት አልረካንም አሉ፡፡

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ከዋልታ ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባበር በከተሞች የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ ከተሞች የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ቅንጅታዊ አሰራር ሊከተሉ ይገባል ተብሏል፡፡ ከተሞቻችን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር እጦት የሰፈነባቸው የምሬት ማዕከል ሆነዋል ያሉት የከተማ ልማትና ቤቶች ሚንስትር አቶ ጃንጥራር አባይ፤ በአመራሮችና ፈጻሚዎች ድክመት፣ የብቃት ችግር ፣ቀልጣፋና ፍትሃዊ […]

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ።

ልዑኩ ወደ ሀገር ቤት የመጣውም በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መካከል ባሳለፍነው ነሃሴ 1 2010 ዓ.ም የእርቅ ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ነው። ልዑኩ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም የኦህዴድ የከተማ ፖለቲካና የድርጅት ዘረፍ ሀላፊ አቶ ከፍያለው አያና እናሌሎች የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውለታል። የልዑካን ቡድኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስራ አስፈጻሚ […]

ዛሬ ሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጠራ ወረዳ በጨፋና ቀበሌ በደረሰ የመኪና አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ዛሬ ሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጠራ ወረዳ በጨፋና ቀበሌ በደረሰ የመኪና አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡አደጋዉ የደረሰዉ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ፡፡ሲሆን የህዝብ አይሱዙ ከሲኖትራክ ጋር ተጋጭተዉ ነዉ የሰዎች ህይወት ያለፈው ፡፡

ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ፡፡

በኮንስትራክሸን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በዋና ዳይሬክተርነት እንዲሁም በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮንትራት አስተዳደር እና በምህንድስና ግዢ ላይ በሃላፊነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ኃላፊው በቅርቡ የኢትዮጲያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙትን እና የቀድሞ የተቋሙን ኃላፊ ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝን በመተካት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ይመራሉ፡፡ የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት እንዳስታወቀው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ እና በከተማዋ የመንገድ መሰረተ […]

በ2019 የታዳጊዎች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ፡፡

በማጣሪያው የመጀመሪያ ጨዋታው የኡጋንዳ ቡድንን 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን በሁለተኛ ጨዋታው ጅቡቲን 4 ለ 0 በመርታት ወደ ተከታዩ ደረጃ ለማለፍ የሚያደርገውን ጉዞ አሳምሯል፡፡ የቀይ ቀበሮዎቹን የድል ጎሎች በየነ ባንጃ፤ በረከት ካሌብ፤ ቢንያም አይተን፤ መንተስኖት እንድርያስ አስቆጥረዋል፡፡ እዚሁ ምድብ ኬንያ ደቡብ ሱዳንን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በቀጣይ መጭው እሁድ ነሃሴ 13 በቻማዚ […]

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ከፖሊስ ከተጠየቀው 14 ቀን 8 ቀን ፈቀደ፡፡

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ከፖሊስ ከተጠየቀው 14 ቀን 8 ቀን ፈቀደ፡፡