loading
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ መቐለ ከጅማ አባ ጅፋር ይጫወታሉ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ መቐለ ከጅማ አባ ጅፋር ይጫወታሉ   የሊጉ የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ተስተካካይ ጨዋታ በመቐለ 70 እንደርታ እና ጅማ አባ ጅፋር መካከል ትግራይ ስታዲየም ላይ ቀን 9፡00 ላይ ይጫወታሉ፡፡ በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ የሚሰለጥኑት መቐለ፤ በተከታታይ ስምንት ጨዋታዎች ላይ ድልን ያሳኩ ሲሆን ዘጠነኛውን ድል በጅማው ቡድን ላይ በመቀዳጀት የሊጉን መሪነት ከተከታዮቻቸው በነጥብ ርቀው ያስቀጥላሉ […]

ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለ33 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረበ

ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለ33 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረበ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን በመጋቢት 12 ቀን 2011 ዓ.ም ከማሊ አቻው ጋር ላለበት ጨዋታ 33 ተጫዋቾች በዕጩነት የተመረጡ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ተጫዋቾቹ የካቲት 26/2011 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚገኘው የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተገኝተው ሪፖርት […]

በቶክዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል

በቶክዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል   በጃፓኗ መዲና ቶክዮ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አድርገዋል፡፡   በሴቶች የተካሄደውን ውድድር ሩቲ አጋ በ2፡20፡40 አሸናፊ ስትሆን፤ ሄለን ቶላ በ2፡21፡01 ሁለተኛ እንዲሁም ሹሬ ደምሴ በ2፡21፡05 ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡ ኬንያዊቷ ፍሎረንስ ኪፕላጋት 4ኛ፣ በዳቱ ሂርጳ 5ኛ፣ አባብል የሻነህ 6ኛ በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡ በወንዶች የተደረገውን የሩጫ ውድድር […]