loading

አስቶን ቪላ ለፍፃሜ ጨዋታ ደርሷል ኖርዊች እና ሸፊልድ ዩናይትድ በሚቀጥለው ዓመት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ተሳታፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ሶስተኛውን ክለብ ለመለየት ደግሞ የቻምፒዮንሽፕ የደርሶ መልስ/play off ጨዋታዎች እየተደረጉ ነው፡፡ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ቅዳሜ ዕለት የተደረጉ ሲሆን ትናንት ምሽት አስቶን ቪላ ወደ ፍፃሜው መሻገሩን ሲያረጋግጥ፤ ዛሬ ሌላኛው ቡድን ይታወቃል፡፡ ትናንት ምሽት ዌስት ብሮሚች አልቢዮን በሜዳው ዘ ሀውቶርንስ […]

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ እና በቀጣዮቹ ቀናት ይደረጋሉ፡፡

የሳምንቱ መርሀግብር ጨዋታዎች ዛሬ ቀን 9፡00 ሰዓት ደደቢት እና ባህር ዳር ከነማ ትግራይ ላይ በዝግ ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡ በነገው ዕለት ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ፤ ወላይታ ድቻ ወደ ትግራይ አቅንቶ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 9፡00 ላይ ይጎበኛል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም 10፡00 ላይ ደግሞ መከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ይገናኛሉ፡፡ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ስቱዋርት ሃልን ካሰናበተ በኋላ በምክትሉ ዘሪሁን ሸንገታ […]

በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የተካሄዱ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መልካም ውጤት አስመዝግበዋል::

ቅዳሜ ዕለት በተካሄደ የሻንጋይ የዲያመንድ ሊግ ውድድር ፡- በወንዶች የ5000 ሜትር ርቀት ኢትዮጵያውያኑ ተከታትለው በመግባት አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ዮሚፍ ቀጀልቻ… በ13:04.16 ሰለሞን ባረጋ… በ13:04.71 ሃጎስ ገ/ህይወት… 13:04.83 በሴቶች 1500 ሜትር ውድድር ደግሞ   ራባቢ አራፊ… በ4፡01.15 (ሞሮኮ) ጉዳፍ ፀጋዬ… በ4:01.25 ዊኒ ናንዮንዶ… በ4፡01.39 (ኡጋንዳ) ዳዊት ስዩም… በ4:01.40 … በመሆን ሲጨርሱ አክሱማዊት እምባዬ 6ኛ እና አልማዝ ሳሙኤል […]

የኮፓ ዴል ሬይ የፍፃሜ ጨዋታ ነገ ምሽት ይደረጋል፡፡

117ኛው የስፔን ኮፓ ዴል ሬይ ወይንም የስፔን ንጉስ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በነገው ዕለት ምሽት 4፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል፡፡ ግጥሚያው በባርሴሎና እና ቫሌንሲያ መካከል ሲቪያ ውስጥ በሚገኘው በሪያል ቤትስ ቤኒቶ ቪያማሪን ስታዲየም ይደረጋል፡፡ በአሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ የሚመራው የካታላኑ ቡድን በግማሽ ፍፃሜው ተቀናቃኙን ሪያል ማድሪድ በደርሶ መልስ 4 ለ 1 ድል በማድረግ ለተከታታይ ስድስተኛ የፍፃሜ ጨዋታ ሲበቃ […]

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደደቢት ከሊጉ መሰናበቱን ሲያረጋግጥ፤ ጊዮርጊስ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሀግብር ጨዋታዎች፤ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በአዲስ አበባ እና ክልል ስታዲየሞች ላይ ተካሂደዋል፡፡ ትናንት አዲስ አበባ ላይ የምስራቁን ድሬዳዋ ከነማ ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 0 ድል በማድረግ ወደ ድል ጎዳና መመለስ ችሏል፡፡ ፈረሰኞቹ መረብ ላይ ያሳረፏቸው ሁለት ግቦች በተከላካይ መስመር ተሰላፊው አስቻለው ግርማ የፍፁም ቅጣት ምት ጎሎች ተገኝተዋል፡፡ የመጀመሪያው አጋማሽ […]

ዛማሊክ የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሸናፊ ሆነ፡፡

የ2018/19 የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ የመልስ ግጥሚያ ትናንት ምሽት ግብፅ ላይ ተካሂዷል፡፡ የፍፃሜው ጨዋታ ደግሞ ግብፁ ኤል ዛማሊክ እና የሌላኛዋ ሰሜን አፍሪካዊት ሀገር ሞሮኮ ተወካይ ሬነሳንስ ስፖርቲቭ ዴ ቤርካኔ መካከል ዛማሊክ በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት 5 ለ 3 በመርታት በታኩ የመጀመሪያውን የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሳክቷል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት ሞሮኮ ላይ የመጀመሪያ ግጥሚያቸውን አድርገው፤ […]