loading
የእስራኤል አቃቤ ህግ ከምርጫ በፊት ኔታንያሁ ላይ ክስ ልመሰርት እችላለሁ አለ

የእስራኤል አቃቤ ህግ ከምርጫ በፊት ኔታንያሁ ላይ ክስ ልመሰርት እችላለሁ አለ አቃቤ ህግ የሰጠው ፍንጭ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሚያዚያ 9 ከሚካሄደው ምርጫ በፊት ሊከሰሱ እንደሚችሉ ያመላክታል ተብሏል፡፡ አቃቤ ህግ በመግለጫው  ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ምርጫው ከመካሄዱ በፊት እንዳይከሰሱ የሚያደርግ ህጋዊ ምክንያት የለም ነው ያለው፡፡ አቃቤ ህግ ይህን ያለው የኔታኒያሁ ጠበቃ ከምርጫው […]

ኤርባስ ኤ 380 የተሰኘውን አውሮፕላን ማምረት አላዋጣኝም አለ፡፡

ኤርባስ ኤ 380 የተሰኘውን አውሮፕላን ማምረት አላዋጣኝም አለ፡፡ በአውሮፓ ትልቁ አውሮፕላን አምራች ኤር ባስ ኩባንያ በፈረንጆቹ 2021 ሱፐር ጃምቦ ጀት የመንገደኞች አውሮፕላን ማምረቱን ለማቆም ማሰቡን ይፋ አድርጓል፡፡ ኤር ባስ ምርቱን ለማቆም የተገደድኩት ገበያው ስለተቀዛቀዘ ነው ማለቱን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ ኤር ባስ ይህን አውሮፕላን ማምረት የጀመረው ከቦይንግ 747 ጋር በመፎካከር የገበያ ድርሻውን ለመቆጣጠር ቢሆንም አብዛኞቹ አየር […]

ሪያድ ወደ ውጭ የምትልከውን የነዳጅ መጠን ልትቀንስ ነው፡፡

ሪያድ ወደ ውጭ የምትልከውን የነዳጅ መጠን ልትቀንስ ነው፡፡ ሳውዲ አረቢያ ከመጭው መጋቢት ወር ጀምሮ በቀን ወደ ውጭ ትልከው የነበረውን 8.2 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ወደ 6.9 ሚሊዮን በርሜል ዝቅ ልታደርግ መሆኑን ተናግራለች፡፡ የሳውዲ የኢነርጂ ሚኒስትር ካሊድ አል ፋሊህ ለፋይናንሺያል ታይምስ እንደተናገሩት ሪያድ ወደ ውጭ የምትልከውን ነዳጅ ብቻ ሳይሆን የምርት መጠኗንም የመቀነስ ሃሳብ አላት፡፡ በዓለም አቀፉ የነዳጂ […]

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው  በቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ትምህርት ቤቶችን ሊያስገነቡ ነው

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው  በቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ትምህርት ቤቶችን ሊያስገነቡ ነው   ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ በሁለቱ ክልሎች  20 ሚሊዮን ብር ትምህርት ቤቶቹን ለማስገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ከሁለቱም ክልሎች ትምህርት ቢሮ ተወካዮች ጋር ተፈራርመዋል።   እንደ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ገለፃ ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት ፍትሃዊ በሆነ ሁኔታ ተደራሽማድረግ የሀገሪቱን የወደፊት ትውልድ ለማነጽ እና ለማዘጋጀት ቁልፍ ተግባር ነው ።   በተያያዘ ዜናም ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተለያዩ የውጭ ሀገር ተቋማትን በማስተባበር ያሰባሰቧቸውን የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች የህፃናት አልጋዎች፣የደም ማስቀመጫ ፍሪጆች  እና ተሽከርካሪ የሆስፒታል ወንበሮች ለሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስረክበዋል። የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ለአርትስ ቲቪ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው  የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት  በገጠር አካባቢ በትምህርት ቤት ርቀት ምክንያት ትምህርት የሚያቋርጡ ተማሪዎችን ችግር ለመቅረፍ ባቅራቢያቸው ትምህርት ቤቶቹን እንደሚገነባ ገልጿል፡፡

ታይዋን  ዲሞክራሲን የሚጋፋ ስምምነት አልፈፅምም አለች፡፡

  ታይዋን  ዲሞክራሲን የሚጋፋ ስምምነት አልፈፅምም አለች፡፡ የታይዋኗ ፕሬዝዳንት ፃይ ኢንግ ዌን ከየትኛውም አካል የሚመጣ ጥያቄ ዲሞክራሲን አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ በምንም መልኩ አንቀበለውም ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቷ ይህን ያሉት ለቻይና ጥሩ አመለካከት አለው የሚባለው ፓርቲ መጭውን ምርጫ ካሸነፍኩ ከቤጂንግ ጋር ስምምነት የማድረግ ሀሳብ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ነው፡፡ ዌንግ የታይዋንን ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ የትኛውም ስምምነት ተቀባይነት […]