loading
የአፍሪካ ህብረት በዚህ ዓመት የአፍሪካ ፓስፖርትን ስራ ላይ አውላለሁ አለ

በአፍሪካ ሀገራት መካከል ነፃ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማድረግ ሲባል ህብረቱ በዚህ የፈረንጆች ዓመት የአፍሪካ  ፓስፖርት መመሪያ ማዘጋጀትና ማተም ላይ እንደሚሰራ ይፋ አድርጓል፡፡ ፓስፖርቱን በመጭው የካቲት ወር በአዲስ አበባ በሚካሄደው 32ኛው የህብረቱ ጉባኤ እንደሚበሰር ይጠበቃል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መህመት በአዲስ ዓመት መልዕክታቸው ‹‹ ዓባል ሀገራቱ በአህጉሪቱ የሀገራት ድንበር በቀላሉ ለመግባትና ለመንቀሳቀስ እየወሰዳችሁት ላለው  እርምጃ አባል […]

ሪያድ የካሾጊ ገዳዮች የሞት ቅጣት ይገባቸዋል እያለች ነው

ሪያድ የካሾጊ ገዳዮች የሞት ቅጣት ይገባቸዋል እያለች ነው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊን በመግደል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የፍርድ ሂደት በትናንትናው ዕለት መሰማት ጀምሯል፤  ሳውዲ አረቢያም በጠቅላይ አቃቢ ህግ በኩል ከተጠርጣሪዎች መካከል አምስቱ በሞት እንዲቀጡ ጠይቃለች፡፡ በመንግስት የሚተዳደረው የሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ እንደዘገበው፤ ሪያድ ላይ በዋለው ችሎት አቃቢ ህግ በግድያው ተጠርጥረው በቀረቡት 11 ተከሳሾች ተገቢ ቅጣት እንዲፈርድባቸው የጠየቀ ሲሆን በቀጥታ […]

በመጪው የገና በዓል ኤሌክትሪክ እንዳይቋረጥ በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

በበዓላት በሚኖረዉ ከፍተኛ የሀይል ፍላጎት የተነሳ ሊያጋጥም የሚችለውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ለማስቀረት በቂ ዝግጅት ማድረጉን ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ ለአርትስ ቲቪ በላከው የፕሬስ መግለጫ እንዳስታወቀው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ጋር በመተባበር ለሚፈጠረው የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ አፋጣኝ መፍትሔ የሚሰጥ የጋራ ተጠባባቂ ኮሚቴ አቋቁሜያለሁ ብሏል። ችግሩ ይከሰትባቸዋል የተባሉ አካባቢዎችን የበዓሉ ቀን ከመድረሱ በፊት መለየቱንና የመልሶ ግንባታ፣ […]

የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከበርካታ ሹማምንቶቻቸው ጋር ግላዊ ሚስጥራቸው ለሳይበር ምዝበራ መጋለጡ ተገለጸ

የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከበርካታ ሹማምንቶቻቸው ጋር ግላዊ ሚስጥራቸው ለሳይበር ምዝበራ መጋለጡ ተገለጸ፡፡   የመራሂተ መንግስቷ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ  ባለስልጣናት የስልክ ግንኙነት ፣ የግል የስልክ ምልልሶችን  ጨምሮ የገንዘብ ዝውውር መረጃዎች ባልታወቁ ጠላፊዎች ተመንትፎ በድረ ገፅ መለለቁ እየተነገረ ነው፡፡   እንደ ቢቢሲ ዘገባ እስካሁን ከድርጊቱ ጀርባ የነማን እጅ እንዳለበት የታወቀ ነገር የለም ተብሏል፡፡ የመረጃው […]

መከላከያ ሰራዊት ጎሳን መሰረት ያደረገ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች በፍጥነት በመግባት ኅብረተሰቡን እያረጋጋሁ ነው አለ

መከላከያ ሰራዊት ጎሳን መሰረት ያደረገ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች በፍጥነት በመግባት ኅብረተሰቡን እያረጋጋሁ ነው አለ። መከላከያ ሚኒስቴር ይህንን የተናገረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የሚኒስቴሩን የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነው። የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሐመድ እንዳሉት፤ የመከላከያ ሰራዊትን ብቁና ገለልተኛ ለማድረግ ባለፉት 6 ወራት የአሰራርና የአደረጃጀት […]

ሂትሮው አየርመንገድ በድሮን ምክንያት በረራ አቋርጦ ነበር

ሂትሮው አየርመንገድ በድሮን ምክንያት በረራ አቋርጦ ነበር በምእራብ ለንደን በሚገኘው የሂትሮው አየር መንገድ አቅራቢያ ድሮን በመታየቱ  ለሰዓታት በረራ እንዲቋረጥ እና መንገደኞች ባሉበት እዲቆዩ ተደርጎ ነበር፡፡ የአየር መነገዱ ቃል አቀባይ  ከፖሊስ እና ከደህንነት አካላት ጋር  ሁኔታውን እያጠኑት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው መንገደኞቹ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ምክንያት ከበረራቸው እንዲዘገዩ ሲነገራቸው የመደናገጥ ስሜት ተፈጥሮባቸው ነበር ፡፡ በወቅቱ በረራው […]

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በታህሳስ ወር 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የሚያወጡ ምርቶችን ማገበያየቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በታህሳስ ወር 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የሚያወጡ ምርቶችን ማገበያየቱን አስታወቀ። የምርት ገበያ 39 ሺህ 240 ቶን ሰሊጥ፤ 27 ሺህ 773 ቶን ቡና  እና 10 ሺህ 995 ቶን  ነጭ ቦሎቄ ነው ማገበያየቱን የገለጸው፡፡ ሰሊጥ ከግብይት መጠኑ 51 በመቶ በመሸፈን የመጀመሪያው ሲሆን፥ በዋጋ ደረጃ ደግሞ ቡና 40 በመቶ በመያዝ ቀዳሚ መሆኑን ጠቅሷል። ቡና […]