loading
የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ባለፈው ሳምንት በ16 በመቶ ቀንሶ መታየቱን ገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣ 2013 የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ባለፈው ሳምንት በ16 በመቶ ቀንሶ መታየቱን ገለፀ፡፡ ድርጅቱ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ባወጣው ሪፖርት ከኮቪድ 19 ጋር የተያያዘ የሞት መጠን መቀነሱንም አስታውሷል፡፡ ድርጅቱ ከስድስት የቁጥጥር ቀጠናዎች ከተላኩለት የበሽታው ስርጭት ሪፖርቶች መካከል በአምስቱ አዲሱ ቫይረስ በሁለት አሃዝ መቀነስ ሲያሳይ በሜዲትራኒያን አካባቢ ብቻ በ7 በመቶ ጭማሪ መመዝገቡ ታውቋል፡፡ […]

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በትራምፕ ዘመን የተጣለውን የግሪን ካርድ ክልከላ ህግ ሸረውታል::

አዲስ አበባ፣የካቲት 18፣ 2013 ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በትራምፕ ዘመን የተጣለውን የግሪን ካርድ ክልከላ ህግ ሸረውታል:: ትራምፕ 100 ሺህ 14 በሚል ድንጋጌ ያጸደቁት የቪዛ ክልከላ አዋጅ መነሻው የአሜሪካዊያንን የሥራ እድል ይጋፋል የሚል እንደሆነ ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ሆኖም አዲሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይህ አዋጅ አሜሪካን የሚጠቅም ሳይሆን የሚጎዳ ነው በማለት በፊርማቸው ሽረውታል፡፡ የባይደን አስተዳደር በዋናነት ህጉን የሻረበትን […]

የሮማው ሊቀጳጳስ አባ ፍራንሲስ በኢራቅ የሚያደርጉት ጉብኝት የበርካቶችን ቀልብ ስቧል::

አዲስ አበባ፣የካቲት 26፣ 2013 የሮማው ሊቀጳጳስ አባ ፍራንሲስ በኢራቅ የሚያደርጉት ጉብኝት የበርካቶችን ቀልብ ስቧል:: ፖፕ ፍራንሲስ በኢራቅ ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው ሲሆን የኮሮቫይረስ ከተከሰተ ወዲህ ዓለም አቀፍ ጉ ሲያደርጉም ቀዳሚው ነው ተብሏል፡፡ የፖፑ ጉብኝት በኢራቅ ለሚገኙ ክስርስቲያኖች ልዩ ሃይማኖታዊ ትርጉም ያለው ሲሆን በጥንታዊት ባቢሎን ዘመን ጀምሮ የነበረውን የባህልና የቋንቋ እሴቶች ትስስር ያጠናክራል ነው የተባለው፡፡ ሊቀጳጳሱ […]

በአሜሪካ በኮቪድ-19 ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀነሱ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 30፣ 2013 በአሜሪካ በኮቪድ-19 ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀነሱ ተሰማ፡፡ ከሶስት ወር ተኩል በኋላ በአሜሪካ በየቀኑ የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ በታች ሆኖ መመዝገቡን ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ይፋ አድርጓል፡፡ ለአሜሪካዊያን በ24 ሰዓታት ውስጥ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች 749 ብቻ መሆናቸው ከወራት በኋላ የተሰማ መልካም ዜና ሆኗል፡፡ ፍራንስ 24 እንደዘገበው 10 […]

የአሜሪካ ጦር የሞዛምቢክ ባህር ሃይል የጂሃዲስቶችን አመጽ ለመውጋት ያግዘው ዘንድ ሊያሰለጥን መሆኑ ተነገረ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2013 የአሜሪካ ጦር የሞዛምቢክ ባህር ሃይል የጂሃዲስቶችን አመጽ ለመውጋት ያግዘው ዘንድ ሊያሰለጥን መሆኑ ተነገረ ፡፡ የሞዛምቢክ ባህር ሃይል በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ ካቦ ዴልጋዶ ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የጂሃዲስት አመጽ ለመዋጋት የሚያስችለውን አቅም የአሜሪካ ልዩ ኦፕሬሽን ሃይል ለሁለት ወራት እንደሚያስታጥቀው በማፑቶ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡ በአካባቢው አል- ሸባብ በመባል የሚታወቁት የታጠቁት […]

በአውስራሊያ የተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ በርካታ ሺዎችን ከመኖሪያቸው እያፈናቀለ ነው::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 በአውስራሊያ የተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ በርካታ ሺዎችን ከመኖሪያቸው እያፈናቀለ ነው:: የሀገሪቱ መንግስት እስካሁን የአደጋ ስጋት ያለባቸውን 18 ሺህ ገደማ ነዋሪዎችን ከአካባቢያቸው እንዲነሱ አድርጓል፡፡ በአውስትራሊያ የተከሰተው ጎርፍ በአስከፊነቱ ከ60 ዓመታት ወዲህ ታይቶ እንደማይታወቅ ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡ የኒው ሳውዝ ዌልስን እና ሌሎች አካባቢዎችን ያጥለቀለቀው ጎርፍ በቀጣዮቹ ሳምንታትም ተጠናክሮ እደሚቀጥል የአየር ሁኔታ […]

የፖለቲካ ቀውስ እና የኩቪድ 19 ወረርሽኝ ቦልሶናሮን አስጨንቋቸዋል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013 የፖለቲካ ቀውስ እና የኩቪድ 19 ወረርሽኝ ቦልሶናሮን አስጨንቋቸዋል ተባለ:: የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጃየር ቦልሶናሮ ከዚህ ቀደም ብራዚላውያን ስለ ኮቪድ -19 ማልቀስ ማቆም እንዳለባቸው ሲናገሩ ነበር ጃየር ቦልሶናሮ የጦር ኃይሎች ፣ የባህር ኃይል እና የአየር ኃይል ሀላፊዎች በሙሉ ቸል ባሉበት በዚህ ወቅት አገሪቱ በየቀኑ ከፍተኛ የኮቪድ -19 የሞት ቁጥር እያስመዘገበች […]

የ533 ሚሊየን ፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ በነፃ በበየነ መረብ ተለቀቀ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2013 በመረጃ መረብ ጠላፊያዎች የፌስቡክ መረጃዎቻቸው ከተጠለፈባቸው 533 ሚሊየን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መካከል ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑት በኢትዮጵያ መሰረታቸውን ያደረጉ የፌስቡክ አካውንቶች ናቸው ተብሏል። የመረጃ ጣለፊያዎች ከፌስቡክ የዘረፉት የግለሰቦች መረጃ በነፃ በጠላፊዎች ህዝባዊ ፎረም ላይ እንደሚገኝ ነው ብሌፒንግ ኮምፒዩተር የዘገው። ይህ የተሰረቀ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በጠላፊዎች ለአባላቱ መሸጥ […]

ጥቁር ቆዳ ቀለም ያለዉ አንድ ሰዉ በፖሊሶች በግፍ ከተገደለ በኋላ በሚኒያ ፖሊስ አቅራቢያ የተቃውሞ ሰልፎች ተቀጣጠሉ፡፡

አዲስ አበባ፣  ሚያዚያ ፡ 04፣ 2013 ጥቁር ቆዳ ቀለም ያለዉ አንድ ሰዉ በፖሊሶች በግፍ ከተገደለ በኋላ በሚኒያ ፖሊስ አቅራቢያ የተቃውሞ ሰልፎች ተቀጣጠሉ፡፡ በአሜሪካ ብሩክሊን ማእከል ውስጥ የትራፊክ ማቆሚያ አካባቢ ፖሊሶች ጥቁር ቀለም ያለዉን አንድ ሰዉ በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተኩሰው ከገደሉ በኋላ የተቃውሞ ሰልፎች በሚኒያፖሊስ አቅራቢያ መካሄዳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ሟች ዱዋንት ራይት የ20 ዓመት ወጣት መሆኑን […]

ቴክኖ ታዋቂውን የሆሊውድ ተዋናኝ ክሪስ ኢቫንስን የቴክኖ አለም አቀፍ የንግድ አምባሳደሩ አድርጎ ሾመው::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2013 ቴክኖ ታዋቂውን የሆሊውድ ተዋናኝ ክሪስ ኢቫንስን የቴክኖ አለም አቀፍ የንግድ አምባሳደሩ አድርጎ ሾመው:: ክሪስ ኢቫንስ በግንቦት 20 በሚደረገው የTECNO የምርት አውደ ርዕይ ላይ የቴክኖ የንግድ አምባሳደር በመሆን የሚቀርብ ሲሆን በሚቀጥሉት የቴክኖ ዓለም አቀፍ የምርት ዘመቻዎች ላይም ቴክኖን በወከል ይሳተፋል:: ዓለም አቀፉ ፕሪሚየም ስማርት ስልክ ብራንድ TECNO ዛሬ ከሆሊሁዱ […]