loading
ፕሮፌሰር አንቶኒ ፋውቺ አሜሪካ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የምትሄድበት መንገድ ስህተት ነው አሉ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013  ፕሮፌሰር አንቶኒ ፋውቺ አሜሪካ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የምትሄድበት መንገድ ስህተት ነው አሉ፡፡ ፕሮፌሰሩ ከሲ ኤን ኤን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በመላው አሜሪካ በርካታ በቀላሉ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች አሁንም ክትባት አላገኙም ብለዋል፡፡ ይሄ ደግሞ የበሽታውን ስርጭት ለማሰፋት ዋነኛ መንስኤ ይሆናል ነው ያሉት ፕሮፌሰር ፋውቺ፡፡ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ስርጭት የሥርጭት […]

ዩ ኤስ ኤድ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት የሚውል 720 ሚሊዮን ዶላር ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 29፣ 2013 ዩ ኤስ ኤድ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት የሚውል 720 ሚሊዮን ዶላር ይፋ አደረገ:: ዩ ኤስ ኤድ የተሰኘው የአሜሪካ ዓለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅት ለኮቪድ 19 ምላሽ እና ማገገሚያ የሚውል 720 ሚሊዮን ዶላር ማፅደቁ ተሰማ፡፡ የአሜሪካ ዓለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅት ኃላፊ ሳማንታ ፓወር እንደገለፁት በጀቱ የኮቪድ 19 ስርጭትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመግታት ያለመ […]

ሳዑዲ አረቢያ የኮቪድ -19 ክትባት ለወሰዱና ከተለያዩ ሀገራት ለመንፈሳዊ ጉዞ ወደ መካ መዲና የሚገቡ የኡምራ ተጓዦች መቀበል እንደምትጀመር አስታውቃለች ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 ሳዑዲ አረቢያ የኮቪድ -19 ክትባት ለወሰዱና ከተለያዩ ሀገራት ለመንፈሳዊ ጉዞ ወደ መካ መዲና የሚገቡ የኡምራ ተጓዦች መቀበል እንደምትጀመር አስታውቃለች ፡፡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ ከሰኞ ጀምሮ የኡምራ ተጓዦችን ጥያቄ መቀበል መጀመራቸውን ነው የገለጹት ፡፡ ሳዑዲ አረቢያ በኮቪድ-19 ስርጭት ምክንያት ለ18 ወራት ከተለያዩ ሀገራት መግቢያ በሮቿን ዝግ አድርጋ ቆይታለች፡፡ አሁን ላይ […]

በኒውዚላንድ አንድ የኮቪድ-19 ተጠቂ መገኘቱን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዕቀባ ተጣለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013 በኒውዚላንድ አንድ የኮቪድ-19 ተጠቂ መገኘቱን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ገደብ መጣሉ ተነገረ፡፡በኒው ዚላንድ በስድስት ወር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ፤ ኦክላንድ ውስጥ አንድ ሰው የኮቪድ-19 ተህዋሲ ተጠቂ መሆኑን ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ ከሶስት ቀን እስከ ሳምንት የሚደርስ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ታውቋል። በተህዋሲው የተያዘው ሰው የተጎበኘችው የባህር ዳርቻዋ ከተማ ኮሮማንዴል እንደ ኦክላንድ ሁሉ ለሰባት ቀናት […]

በአፍጋኒስታን ጉዳይ አሁንም አቋሜ የጸና ነው -ጆ ባይደን

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013  የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአፍጋኒስታን ወታደሮቼን በማውጣት ውሳኔዬ የምጸጸትበት አይደልም ሲሉ ተናገሩ፡፡ አንድም የአሜሪካ ወታደር በአፍጋኒሰታን ምድር ሊሞት አይገባም ያሉት ባይደን በአወጣጥ ላይ ክፍተቶች እንደነበሩ አልሸሸጉም፡፡ ጆ ባይደን ማስተባበያ በሰጡበት በዚህ ንግግራቸው እንዳብራሩት፣ የአፍጋኒሰታን ጦር ታሊባንን ለመዋጋት ፍላጎት እንዳልነበረው፤ የአፍጋኒሰታን መንግሥትም ወዲያውኑ ተስፋ እንደቆረጠ ከገለጹ በኋላ ፤ታሊባን ካቡልን ይቆጣጠራል ብለን ከገመትንበት […]

ለ39 ዓመታት ያህል ራሱን ስቶ የቆየው የቀድሞ የፈረንሳይ እግር ኳስ ተጫዋች አረፈ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 ለ39 ዓመታት ያህል ራሱን ስቶ የቆየው የቀድሞ የፈረንሳይ እግር ኳስ ተጫዋች አረፈ፡፡ ለ39 ዓመታት ያህል ራሱን ስቶ የቆየው የቀድሞ የፈረንሳይ እግር ኳስ ተጫዋች ዣን-ፒር አዳምስ ህይወቱ አለፈ።  በህክምና ስህተት የተነሳ ራሱን ስቶ ለ39 ዓመታት የቆየው የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ ዣን-ፒር አዳምስ ለፓሪስ ሴይንት ጀርማይን ተጫውቶ አሳልፏል። እ.አ.አ በ1982 ላጋጠመው የጉልበት ጉዳት […]

ዲዲዬር ድሮግባ የዓለም ጤና ድርጅት የስፖርት እና የጤና አምባሳደር ሆኖ ተሾመ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 09፣ 2014  የቀድሞው ኮትዲቯሪያዊው እግር ኳስ ተጫዋች በጤና ድርጅቱ የአምባሳደርነት ሚና ሲሰጠው በአካላዊ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊነት ላይ የድርጅቱን መመሪያ የማስተዋወቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል ተብሏል፡፡ ድሮግባ የዓለም ጤና ድርጅት የመልካም ፍቃድ የስፖርት እና ጤና አምባሳደር ስብስብ በመቀላቀሉ ደስታ እንደተሰማው የተናገረ ሲሆን የ2022 የዓለም ዋንጫን ጤናማ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ በዓለም ጤና ድርጅት፣ በፊፋ የዓለም ዋንጫ […]

ቱርክ ምዕራባውያን ሀገራትት በዩክሬን ጉዳይ ሽብር የመንዛት ዘመቻቸውን ሊያቆሙ ይገባል ስትል አሳሰበች፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 ቱርክ ምዕራባውያን ሀገራትት በዩክሬን ጉዳይ ሽብር የመንዛት ዘመቻቸውን ሊያቆሙ ይገባል ስትል አሳሰበች፡፡ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ምዕራባውያን ሀገራት በዩክሬን ሁኔታ ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ መግለጫዎችን ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስተያየት የተሰማው ሩሲያ በዩክሬን ላይ በማንኛውም ጊዜ ጥቃት ልትፈፅም ትችላለች በማለት አሜሪካ ካስጠነቀቀች በኋላ ነው። እንዲህ ዓይነቱ […]

የሆንዱራስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት በአደንዛዥ ዕፅ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 የሆንዱራስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት በአደንዛዥ ዕፅ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ። አሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሁዋን ኦርላንዶ ሄርናንዴዝ በአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪነት ክስ ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ ካቀረበች ከሰዓታት በኋላ ነው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ በፍርድ ቤት የዕስር ትዕዛዝየወጣባቸው ተብሏል፡፡ የፍርድ ቤቱ ቃል አቀባይ ሜልቪን ዱአርቴ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሄርናንዴዝ ላይ የእስር ማዘዣ […]

ከአማካይ ሰራተኞቹ ክፍያ በ1400 እጥፍ የሚበልጠው ስራ አስኪያጅ ደመወዝ…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 አፕል ኩባንያ ሰራተኞቹ ገቢያችን ከኑሯችን አልመጣጠን አለ የሚል ቅሬታ በሚያሰሙበት ወቅት የዋና ስራ አስፈፃሚው ቲም ኩክ ገቢ በ500 ፐርሰንት ማድረጉ በርካቶቸን እያነጋገረ ነው፡፡ ዋና ስራ አስፈጻሚው ባለፈው ዓመት ከደመወዝ ጭማሪ፣ ከጥቅማጥቅም፣ እንዲሁም በጉርሻ መልክ ወደ ኪሳቸው የገባው ገንዘብ ሲሰላ አንድ አማካይ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ ከሚያገኘው በ1,400 እጥፍ ይበልጣል ነው የተባለው፡፡ […]