loading
የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን መሳሪያ ገዝቶ ሊሰጥ መዘጋጀቱን የህብረቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ::

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን መሳሪያ ገዝቶ ሊሰጥ መዘጋጀቱን የህብረቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ:: የአውሮፓ ህብረት ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን እሁድ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ለኬቭ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ተስማምተናል ብለዋል፡፡ ይህን የምናደርገው ዩክሬን ራሷን ከሩሲያ ጥቃት እንድትከላከል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ መሰረታቸውን በህብረቱ አባል ሀገራት ያደረጉ የሩሲያ ሚዲያዎችን ከስርጭት ማገዳቸውንም ገልጸዋል፡፡ ዩክሬናዊያን ሞስኮ […]

በ7 ቀናት ውስጥ 2 በመቶ የዩክሬን ዜጎች ተሰደዋል- ተ.መ.ድ በጦርነቱ ሳቢያ በ7 ቀናት ውስጥ 1 ሚሊዮን ዩክሬናዊያን ወደ ጎረበት ሀገራት መሰደዳቸው ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 በ7 ቀናት ውስጥ 2 በመቶ የዩክሬን ዜጎች ተሰደዋል- ተ.መ.ድ በጦርነቱ ሳቢያ በ7 ቀናት ውስጥ 1 ሚሊዮን ዩክሬናዊያን ወደ ጎረበት ሀገራት መሰደዳቸው ተሰማ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ የዩክሬናዊያን ስደት በፍጥነቱ የክፍለ ዘመኑን ክብረ ወሰን ሊይይዝ እንደሚችል ያሳያል ብሏል፡፡ በቅርብ ቀናት ውስጥ ይህ ቁጥር ወደ 4 ሚሊዮን ከፍ […]

ዩክሬን እና ሩሲያ ሶስተኛውን ዙር የሰላም ድርድር ለማካሄድ ተዘጋጅተዋል ተባለ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 ዩክሬን እና ሩሲያ ሶስተኛውን ዙር የሰላም ድርድር ለማካሄድ ተዘጋጅተዋል ተባለ። ለሁለት ሳምንታት ከሚጠጋ ጦርነት በኋላ ሁለቱ ሀገራት ለሦስተኛው ዙር ድርድር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት የልዑካን ቡድን አባላት ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በምዕራብ ቤላሩስ በሚገኘው ብሬስት ክልል የሁለት ዙር የሰላም ድርድር ላይ ሲሆን ከቀያቸው የሚፈናቀሉ […]

ሱዳን በቀይ ባህር አካባቢ ሩሲያ የጦር ሰፈር እንድታቋቁም መፍቀዷ ግብፅን ቅር አሰኝቷል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 ሱዳን በቀይ ባህር አካባቢ ሩሲያ የጦር ሰፈር እንድታቋቁም መፍቀዷ ግብፅን ቅር አሰኝቷል ተባለ፡፡ የሱዳንን ሉዓላዊ ምክር ቤትን በምክትልነት የሚመሩት ጄኔራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ሞስኮ ደርሰው በተመለሱ ማግስት ሀገራቸው ለሩሲያ የጦር ሰፈር ግንባታ መፍቀዷን ይፋ አድርገዋል፡፡ዳጋሎ በመግለጫቸው ይህን በማድረጋችን ብሔራዊ ጥቅማችን እስካልተነካ ድረስ ስህተት የለውም የሚፈጥረው የፀጥታ ስጋትም የለም ብለዋል፡፡ የግብጽ […]

አሜሪካ እና እንግሊዝ በሩሲያ የነዳጅ እና የጋዝ ሽያጭ ላይ እገዳዎችን አሳለፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 21 አሜሪካ እና እንግሊዝ በሩሲያ የነዳጅ እና የጋዝ ሽያጭ ላይ እገዳዎችን አሳለፉ:: ሁለቱ ሀገራት በሩሲያ ላይ የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ጫና የገፉበት ሲሆን ሞስኮ የነዳጅ ምርቷን ለገበያ እንዳታቀርብ ተባብረውባታል፡፡ የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ በሩሲያ የጋዝ ምርት ላይ ያለውን ጥገኝነት በማቆም ለዩክሬን ወረራ ኢኮኖሚያዊ የማዕቀብ ምላሽ እየሰጠ ይገኛል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተወሰደው እርምጃ […]

ኢራን በሰሜናዊ ኢራቅ በሚገኝ የእስራኤል ጦር ሰፈር ላይ የድሮን ድብደባ ማደረሷ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2014 ቴህራን ይህን እርምጃ የወሰደችው ባለፈው ወር የእስራኤል አየር ሃይል በአንድ የድሮን ፋብሪካዋ ላይ የፈጸመውን ጥቃት ለመበቀል ነው ተብሏል፡፡ እስራኤል ጥቀት ፈጸመችበት የተባለው ፋብሪካ የኢራን ሁነኛ የወታደራዊ ድሮኖች ማምረቻና ማከማቻ መሆኑ ነው የተሰማው፡፡ ይሁን እንጂ እስራኤል እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ ማስተባበያም ይሁን ድርጊቱን ስለመፈፀሟ አንዳችም መግለጫ አልሰጠችም፡፡ ደረሰ የተባለው ጥቃትም […]

በቻይና 132 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበር ቦይንግ 737 አውፕላን መከስከሱ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 በቻይና 132 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበር ቦይንግ 737 አውፕላን መከስከሱ ተሰማ፡፡ የምስራቅ ቻይና አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላኑ ጉዋንግዚ በተባለች ግዛት የተከሰከሰ ሲሆን የአደጋው መንስኤ እተጣራ ነው ተብሏል፡፡ አደጋው የተከሰተው አውሮፕላኑ መንገደኞችን ከኩሚንግ ወደ ጉዋንግዙ ከተማ በሚያጓጓጉዝበት ወቅት መሆኑን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡ አልጀዚራ ከቻይና ባሰራጨው ዘገባ ሀገሪቱ በዓመት […]

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሩሲያን በመቃወም ከጎናቸው እንዲቆም ዳግም ጥሪ አሰተላለፉ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሩሲያን በመቃወም ከጎናቸው እንዲቆም ዳግም ጥሪ አሰተላለፉ:: ሩሲያ የዩክሬንን ድንበር ጥሳ በመግባት ጦርነት ከከፈተች ድፍን አንድ ወር ያስቆጠረች ሲሆን እስካሁን በጦርነቱ ሳቢያ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን ሀገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በቴሌግራም ገጻቸው ባስታላለፉት መልእክት ዩክሬንን መደገፍ ነጻነትን መደገፍ ነው እናም መላው ዓለም […]

ኢምፔሬያሊስቶችን አደብ ማስገዛት የሚቻለው ወታደራዊ አቅምን ባማሳደግ ነው-ኪም ጆንግ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2014 ኢምፔሬያሊስቶችን አደብ ማስገዛት የሚቻለው ወታደራዊ አቅምን ባማሳደግ ነው-ኪም ጆንግ ፕሬዚዳንት ኪም ጆን ኡን ሀገራቸው የሚሳኤል ጦር መሳሪያ ትጥቋን ይበልጥ ለማዘመን ማቀዷን ይፋ አደረጉ፡፡ በአንድ ዓመት ውስጥ 12 የሚሳኤል ሙከራዎችን ያደረገችው ፒዮንግያንግ ሰሞኑን አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳኤል በተሳካ ሁኔታ መሞከሯ በአሜሪካና አጋሮቿ ዘንድ ስጋትና ቁጣን ቀስቅሷል ነው የተባለው፡፡ ዋሶንግ […]

የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በዳርፉር ያለውን የክስ ሁኔታ መቋጫ ማበጀት እፈልጋለሁ አሉ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በዳርፉር ያለውን የክስ ሁኔታ መቋጫ ማበጀት እፈልጋለሁ አሉ፡፡የፍርድ ቤቱ ዋና አቃቤ ህግ ካሪም ካህን በሄግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር በቅርቡ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ወይ ተብለው ሲጠየቁ በዳርፉር ያለውን ሁኔታ መዝጋት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል ተብሏል። የቀድሞ የሱዳን ሚሊሻ ሃላፊ አሊ […]