loading
በኒጀር ፅንፈኛ ሃይሎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 100 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 26፣ 2013 በኒጀር ፅንፈኛ ሃይሎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 100 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ:: በሀገሪቱ መንግስት አክራሪ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ቡድኖቹ ጥቃቱን ያደረሱት በማሊ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ በሁለት መንደሮች ነው ተብሏል፡፡ የኒጀር ጠቅላይ ሚኒስትር ጥቃቱ ወደ ተፈፀመባቸው መንደሮች በማቅናት የጎበኙ ሲሆን የተጎጂ ቤተሰቦችና ነዋሪዎቹን አበረታተዋል፡፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው ተዋጊ ሃይሎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ሁለት ተዋጊ ሚሊሻዎቻቸው […]

ጃፓን የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ልትደነግግ ነው::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 26፣ 2013 ጃፓን የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ልትደነግግ ነው:: ጃፓን በሶስተኛው ዙር የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስረጭት አደጋ ውስጥ መሆኗን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዮሺሂንዴ ሱጋ በመግለጫቸው እንዳሉት አሁን ላይ ሀገሪቱ ያጋጠማትን የበሽታውን ስርጭት ስጋት ለመቀነስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመደንገግ እንገደዳለን ብለዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ጃፓን ከ4 ቀናት በፊት በ24 ሰዓታት […]

የላልይበላ ከተማ አስተዳደር የገና በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጌያለሁ አለ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 28፣ 2013 የላልይበላ ከተማ አስተዳደር የገና በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጌያለሁ አለ:: የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን ነው የከተማ አስተዳደሩ የገለፀው፡፡ የቅዱስ ላልይበላን ዓመታዊ ክብረ በዓል ምዕምናንና ጎብኚዎች ወደ ሥፍራው መግባት ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል። ቅድስቲቷ ምድርም በምዕመናንና በጎብኝዎች ተውባለች። የበዓሉን ዝግጅት አስመልክቶ […]

ሴት አመራሮች የላቀ የአመራር ጥበብና በውሳኔ አሰጣጥ የተግባቦታዊ ኪሂል በመጎናፀፍ ተቋማቸውን በብቃት ሊመሩ እንደሚገባ ተገለፀ ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 03፣ 2013 ሴት አመራሮች የላቀ የአመራር ጥበብና በውሳኔ አሰጣጥ የተግባቦታዊ ኪሂል በመጎናፀፍ ተቋማቸውን በብቃት ሊመሩ እንደሚገባ ተገለፀ ፡፡ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከሁሉም የፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ሴት ሚኒስትሮች፣ ሴት ሚኒስቴር ዴኤታዎች፣ ሴት የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ ኮሚሽነሮችና በከፍተኛ ሴት አመራር ደረጃ ለሚገኙ አካላት የአመራር ጥበብና ተግባቦታዊ ክሂላቸውን የሚያዳብሩበት ስልጠናና እርስ በርሳቸው የካበተ […]

በመላዉ ዓለም የኮቪድ 19 ክትባት መሰጠት መጀመሩ ኢትዮጵያን ከቫይረሱ እንዳይጠነቀቁ ሊያደርግ አይገባም::

አዲስ አበባ፣ጥር 03፣ 2013 በመላዉ ዓለም የኮቪድ 19 ክትባት መሰጠት መጀመሩ ኢትዮጵያን ከቫይረሱ እንዳይጠነቀቁ ሊያደርግ አይገባም ሲሉ አርትስ ያነጋገራቸዉ በሚሊኒየም የኮቪድ 19 ኬር ሴንተር የነርስኒግ ዳይሬክተር ሲስተር ንጋት ወ/ማርያም አሳሰቡ ፡፡ በማዕከሉ ቀደም ሲል ከነበረዉ የታማሚዎች ቁጥርና የፅኑ ህክምና  የሚያስፈልጋቸዉ ሰዎች ቁጥር መበራከታቸዉን ያስታወሱት ሲስተር ንጋት ፤የኮቪድ 19 ክትባት ቢገኝም ለአፍሪካ ብሎም ለኢትዮጵያ ተዳራሽ የመሆኑ […]

ኬንያ እና ሶማሊያ አሁንም በመልካም ጉርብትናቸው የሚቀጡሉበት መንገድ አልተዘጋም ተባለ::

አዲስ አበባ፣ጥር 03፣ 2013 ኬንያ እና ሶማሊያ አሁንም በመልካም ጉርብትናቸው የሚቀጡሉበት መንገድ አልተዘጋም ተባለ:: ሶማሊያ ባለፈው ዲሴምበር ወር በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገባችብኝ በሚል መነሻ ከኬንያ ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነቷን በይፋ አቋርጣለች፡፡ ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸው ወደ ነበረበት እንዲመለስ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርጉ የአፍሪካ ህብረትም ውዝግቡ በሰላም እንዲፈታ አሳስቦ ነበር፡፡ ሶማሊያ ውስጥ በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ኬንያዊያን ሰራተኞች እንዳሉና በኬንያም […]

በዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው ::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 በዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው ::የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከዩ ኤን የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ነው በዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና የሚሰጠው፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ስልጠናው በምርጫው ላይ በተለያዩ ዘርፎች የሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞችን አቅም ለማሳደግ አንደሚረዳ ተናግረዋል። ለበጎ ፈቃደኞቹ ክፍተት ባለበት […]

የሃይሌ ማናስ አካዳሚ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ት/ቤት የመጀመሪያ ተማሪዎቹን ተቀበለ::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 የሃይሌ ማናስ አካዳሚ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ት/ቤት የመጀመሪያ ተማሪዎቹን ተቀበለ:: የሃይሌ- ማናስ አካዳሚ ውጤት የሆነው ይህ አዲስ ጥራቱን የጠበቀ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ት/ቤት በደብረ ብርሃን ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎቹን ተቀብሏል፡፡ በአዲሱ ካምፓስ ወላጆች በአካል ተገኝተው ልጆቻቸውን ያስመዘገቡ ሲሆን የጉብኝት እና የኮቪድ-19 የጥንቃቄ መመሪያ ገለፃ ላይ […]

ደቡብ አፍሪካ እስከመጪው ወር አጋማሽ ድረስ 20 የሚሆኑ የድንበር ኬላዎቿን ለመዝጋት ወሰነች::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 ደቡብ አፍሪካ እስከመጪው ወር አጋማሽ ድረስ 20 የሚሆኑ የድንበር ኬላዎቿን ለመዝጋት ወሰነች:: ደቡብ አፍሪካ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ ስላሳሰባት ነው፡፡ ድንበሮቹ ዝግ ሆነው በሚቆይበት ወቅትም ወደ ሀገሪቱ የሚገቡም ሆኑ ወደ ውጭ የሚወጡ ተጓዦች አይኖሩም ነው የተባለው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ለ20 ሚሊዮን ሰዎች […]

በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ጂሃዲስቶች ባደረሱት ጥቃት 13 ወታሮች ተገደሉ::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ጂሃዲስቶች ባደረሱት ጥቃት 13 ወታሮች ተገደሉ:: በዮቤ ግዛት በምትገኝ አንዲት መንደር አቅርቢያ በሚጓዙ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች ላይ በድንገት በተከፈተ ጥቃት ነው ወታደሮቹ የተገደሉት ተብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው የደፈጣ ተዋጊዎቹ በከባድ መሳሪያዎችና በሮኬት በሚወነጨፉ የእጅ ቦንቦች ጭምር ነው ጥቃቱን ያደረሱት፡፡ ወታደሮቹ ጥቃቱ ከተፈፀመበት 20 ኪሎሜትር ርቀት ላይ […]