loading
አሸባሪዉ ህዉሃት ሰቆጣን ለመቆጣጠር ያደረገዉ ተደጋጋሚ ሙከራ እንዳይሳካ የሰቆጣ ወጣቶች ተደራጅተዉ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነዉ ሲል ተደራጅተዉ አከባቢያቸዉን ከሚጠብቁ ወጣቶች አንዱ የሆነዉ ሙሉቀን ዳኘዉ ለአርትስ በስልክ ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 አሸባሪዉ ህዉሃት ሰቆጣን ለመቆጣጠር ያደረገዉ ተደጋጋሚ ሙከራ እንዳይሳካ የሰቆጣ ወጣቶች ተደራጅተዉ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነዉ ሲል ተደራጅተዉ አከባቢያቸዉን ከሚጠብቁ ወጣቶች አንዱ የሆነዉ ሙሉቀን ዳኘዉ ለአርትስ በስልክ ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡ በተለይም የተደራጀዉ የአካባቢዉ ወጣት ሃይል ህዝቡ ከተማውን ለማንም ጥሎ እንዳይወጣ የማረጋጋትና ማንኛውም የታጠቀ ሃይል በአንድ ኮማንድ ስር ሆኖ በፈረቃ ከተማውን እንዲጠብቅ በማድረግ […]

በህገወጥ መንገድ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በማስገጠም  ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያውቀውን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በማስገጠም የኤሌክትሪክ ሃይል ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች እና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ። የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ሰፈራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ ተመላክቷል። በአካባቢው የሚኖሩ አምስት ግለሰቦች የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ለማስገባት ፈልገው ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  አገልግሎት ምስራቅ […]

ጦርነቱ ህዝባዊ ይደረግ ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 10፣2013 የአማራ ክልል ህዝብ ጦርነቱን ህዝባዊ እንዲያደርገው ርዕሰ መስተዳደር ጥሪ አቀረቡ:: የህወሓት የሽብር ቡድን ጦርነቱን ህዝባዊ ስላደረገው የአማራ ክልል ህዝብም በተመሳሳይ መንገድ ጦርነቱን ህዝባዊ እንዲያደርገው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ጥሪ አቀርበዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳደሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የህወሓት የሽብር ቡድን በዋናነት በሶስት ግንባሮች ማለትም በሰሜን እና በደቡብ ጎንደር እንዲሁም በሰሜን […]

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አለፈ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 11፣2013 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አለፈ፡፡ የጤና ሚኒስቴር በ24 ሰዓቱ የኮቪድ-19 ሪፖርት መረጃው ላይ እንዳስታወቀው ፤ በቫይረሱ ምክንያት 11 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡ እስካሁንም በሀገሪቱ በኮሮና ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም 4 ሺህ 4 መቶ 89 ደርሷል፡፡ በ24 ሰዓታት ዉስጥ 5ሺህ 1 መቶ 73 ሰዎች ላብራቶሪ ምርመራ […]

ጠ/ሚ ዐቢይ በወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ዝግጅቶችን ላቀረቡ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ምስጋና አቀረቡ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 11፣2013 ጠ/ሚ ዐቢይ በወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ዝግጅቶችን ላቀረቡ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ምስጋና አቀረቡ::ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ መቼም፣ የትም፣ በምንም በሚል መሪ ቃል፣ የብሔራዊ ቴአትር፣ ኦሮሞ የባህል ማዕከልና የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች በወታደራዊ ማሠልጠኛዎች ተገኝተው ዝግጅቶችን አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት÷ኪነ ጥበብ ምንጊዜም ከኢትዮጵያ ጀግንነት ጋር ናት ብለዋል፡፡ በዚህም ዝግጅቶቹን […]

በአዲስ አበባ ትላንት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከአንድ ቤተሰብ 5 ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል-ተጎጂዎች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013  በመዲናዋ ትናንት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ እስካሁን የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ:: የአዲስ አበበ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰለሞን ፍሰሃ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በተከሰተው አደጋ በህይወት እና ንብረት ላይ የደረሱ ጉዳቶች እየተጣሩ ነው፡፡ እስካሁን በአደጋው የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉን የገለጹት ኮሚሽነሩ÷አጠቃላይ የደረሰው ጉዳት ዛሬ ከሰዓት ይፋ እንደሚደርግም ጠቁመዋል፡፡ በመካነየሱስ […]

በሳዑዲ አረቢያ እስርቤቶች የሚገኙ ኢትጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013 በሳዑዲ አረቢያ የተለያዩ ማቆያ ማእከላትና እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ተገለፀ፡፡ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት በሪያድ የሚገኘነውን የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጠቅሶ በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር በመቀናጀት በሳምንት ሶሶት በረራዎችን በማድርግ በሳዑዲ አረቢያ የተለያዩ ማቆያ ማዕከላትና እስር ቤቶች የሚገኙ ዜጎችን ከዚህ […]

በኒውዚላንድ አንድ የኮቪድ-19 ተጠቂ መገኘቱን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዕቀባ ተጣለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013 በኒውዚላንድ አንድ የኮቪድ-19 ተጠቂ መገኘቱን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ገደብ መጣሉ ተነገረ፡፡በኒው ዚላንድ በስድስት ወር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ፤ ኦክላንድ ውስጥ አንድ ሰው የኮቪድ-19 ተህዋሲ ተጠቂ መሆኑን ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ ከሶስት ቀን እስከ ሳምንት የሚደርስ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ታውቋል። በተህዋሲው የተያዘው ሰው የተጎበኘችው የባህር ዳርቻዋ ከተማ ኮሮማንዴል እንደ ኦክላንድ ሁሉ ለሰባት ቀናት […]

51 ሺህ 89 ኢትዮጵያዊያን ከሀገር ወጥተው የት እንዳሉ አይታወቅም::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013 ከሀገር ውጪ ፈልሰው አድራሻቸው ያልታወቁ 51 ሺ 89 ዜጎች መኖራቸውን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ኤጀንሲው የአለማቀፍ ፍልሰት ድርጅት እና ዳኒሽ ከተባለ ግብርሰናይ ድርጅት ጋር በመተበባር ባስጠናው ጥናት 51 ሺ 89 ኢትዮጵያዊያን ከሀገር እንደወጡ የት እንዳሉ እንዳልታወቀ ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡ ከ41 ሺህ በላይ ቤተሰቦች ለተካተቱበት ለዚህ ጥናት የኢትዮጵያ መንግስት 36 ሚሊዮን ብር ያወጣበት […]

በአፍጋኒስታን ጉዳይ አሁንም አቋሜ የጸና ነው -ጆ ባይደን

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013  የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአፍጋኒስታን ወታደሮቼን በማውጣት ውሳኔዬ የምጸጸትበት አይደልም ሲሉ ተናገሩ፡፡ አንድም የአሜሪካ ወታደር በአፍጋኒሰታን ምድር ሊሞት አይገባም ያሉት ባይደን በአወጣጥ ላይ ክፍተቶች እንደነበሩ አልሸሸጉም፡፡ ጆ ባይደን ማስተባበያ በሰጡበት በዚህ ንግግራቸው እንዳብራሩት፣ የአፍጋኒሰታን ጦር ታሊባንን ለመዋጋት ፍላጎት እንዳልነበረው፤ የአፍጋኒሰታን መንግሥትም ወዲያውኑ ተስፋ እንደቆረጠ ከገለጹ በኋላ ፤ታሊባን ካቡልን ይቆጣጠራል ብለን ከገመትንበት […]