loading
በባህሬን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ የቦንድ ግዥ ተፈጸመ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014  በባህሬን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ የቦንድ ግዥ ተፈጸመ:: የኢትዮጵያ አዲስ ዓመትም ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤት አምባሳደር ጀማል በከር፣ ዲፐሎማቶችና ሰራተኞች፣ የኃይማኖት መሪዎች፣ በባህሬን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጰያዊያን በተገኙበት ተከብሯል። አምባሳደር ጀማል በከር ለኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳቸሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የብልጽግናና ስኬት […]

በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ከ260 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ወደሙ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014 በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ከ260 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ወደሙ፡፡ በአሸባሪው የህወሓት ወረራ ምክንያት ከ260 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ 2 ሺህ 511 የሚደርሱ ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል ጥቃት እንደደረሰባቸው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት እና ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ […]

አሸባሪው ቡድን ያደረሰው ውድመት በጦር ወንጀል የሚያስጠይቀው ነው -ጎንደር ዩኒቨርስቲ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014  አሸባሪ ቡድኑ በደቡብ ጎንደር ያደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት በጦር ወንጀል የሚያስጠይቀው ነው ሲሉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ኃላፊ አቶ ልጅ አለም ጋሻው ገለጹ፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ኃላፊና በደቡብ ጎንደር አሸባሪው ቡድን ያደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት የሚያጣራው የጥናት ግብረ ኃይል ሰብሳቢ አቶ ልጅ አለም ጋሻው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት […]

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የጀርመን-አፍሪካ 2021 ሽልማት አሸናፊ ሆኑ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014  የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የጀርመን-አፍሪካ 2021 ሽልማት አሸናፊ ሆኑ፡፡ ኢሰመኮ ለአርትስ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የጀርመን-አፍሪካ ፋውንዴሽን (DAS) ዛሬ መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ የሽልማቱን እጩዎችን የሚያወዳድረው ኮሚቴ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ  በጀርመን አገር በአይነቱ ከፍተኛ ለሆነው ሽልማት ሲመርጣቸው በሙሉ ድምጽ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ሽልማቱ ዋና ኮሚሽነሩ […]

አዲስ የመንግሥት ተሿሚዎች ስራ ከመጀመራቸው በፊት ሃብት እንዲያስመዘግቡ የሚደረግ መሆኑን የፌዴራል የስነ-ምግባር እና ፀረሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 አዲስ የመንግሥት ተሿሚዎች ስራ ከመጀመራቸው በፊት ሃብት እንዲያስመዘግቡ የሚደረግ መሆኑን የፌዴራል የስነ-ምግባር እና ፀረሙስና ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ በ2013 ዓ.ም የሃብት ምዝገባ አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም እቅድን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የኮሚሽኑ የሃብት ማሳወቅ እና ምዝገባ ዳይሬክተር መስፍን በላይነህ፤ በተጠናቀቀው ዓመት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የህዝብ ተመራጮች፣ የመንግስት ተሿሚዎች እና […]

የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ ከ3 መቶ ሺህ ባላይ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮቪድ -19 ክትባቶችን ለገሰ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ ከ3 መቶ ሺህ ባላይ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮቪድ -19 ክትባቶችን ለገሰ:: በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳስታወቀው አሁን የተለገሰው ክትባት አሜሪካ በቅርቡ ከለገሰችው 1ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶዝ ተጨማሪ ሲሆን ፤ይህም ለአፍሪካ ቃል ከተገባው 25 ሚሊዮን ህይወት አዳኝ ክትባት አካል ነው ተብሏል፡፡ የአሜሪካ መንግስት የክትባቶችን ስርጭት በተመለከተ ከአፍሪካ ህብረትና ከአፍሪካ […]

ኢትዮጵያ ክብሯን ለመድፈር የሚቅበዘበዙትን አደብ የሚያስገዙ ጀግኖች አጥታ አታውቅም ሲሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ ገለጹ።

አዲስ አበባ፣መስከረም 11 2014 ሚንስትሯ ኢንጂኔር አይሻ መሀመድ ይህን ያሉት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ2013 ዓ.ም በጀት የእቅድ አፈጻጸምና የ2014 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች አስመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡ ከውይይቱ ጎን ለጎንም የኢትዮጵያ ከተሞች የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግሥት ዘመቻን ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ አስጀምረዋል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሀገሩ አምባሳደርና ጠበቃ […]

ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከ60 ሺህ በላይ ዜጎች ለመከላከያ ሠራዊቱ ደም በመለገስ አጋርነታቸውን ማሳየታቸው ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣መስከረም 11 2014 ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከ60 ሺህ በላይ ዜጎች ለመከላከያ ሠራዊቱ ደም በመለገስ አጋርነታቸውን ማሳየታቸው ተገለጸ፡፡ የብሔራዊ ደም ባንከ አገልግሎት የህልውና ዘመቻውን ተከትሎ ደም የሚለግሱ ዜጎች ቁጥር መጨመሩም አስታውቋል። ይህም በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የደም ክምችት እጥረት በመቅረፍ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረጉን ነው የመከላከያ እና ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎቶች የገለጹት። የብሔራዊ ደም […]

የአሜሪካ የማዕቀብ ይጣል ፕሬዚዳንታዊ ትእዛዝ ዓላማው አዲሱን የመንግሥት ምስረታ ማደናቀፍ ነው ሲሉ አምባሳደርና ጋዜጠኛ ተፈራ ሻወል ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 የአሜሪካ የማዕቀብ ይጣል ፕሬዚዳንታዊ ትእዛዝ ዓላማው አዲሱን የመንግሥት ምስረታ ማደናቀፍ ነው ሲሉ አምባሳደርና ጋዜጠኛ ተፈራ ሻወል ተናገሩ፡፡አምባሳደርና ጋዜጠኛ ተፈራ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የአሜሪካ የማዕቀብ ይጣል ፕሬዚዳንታዊ ትእዛዝ የኢትዮጵያ መስከረም 24 ቀን 2014 የሚያካሂደውን የመንግሥት ምስረታ ማደናቀፍ፣ ስልጣን ለአሸባሪው ህወሓት ማጋራት ያም ካልሆነ ጦርነቱ ቆሞ አሽከሮቹ ነፍሳቸውን አድነው ለመውጣት […]