loading

በማረሚያ ቤቶች የዜጎች ሰብአዊ አያያዝ መሻሻሉ ተገለፀ፡፡ የክልልማረሚያቤቶችኮሚሽነሮች፤አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በማረሚያ ቤቶች የዜጎች ሰብዓዊ አያያዝ መሻሻሉን ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ ክልሎች ማረሚያ ቤት ኮሚሽነሮች ገልጸዋል። የሶማሌ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር በሽር አህመድ እንደሚሉት ከዓመታት በፊት በህግ ጥላ ስር በሚገኙ ዜጎች ላይ የአካልና ሞራል ጉዳትን ጨምሮ በርካታ የመብት ጥሰቶች ይስተዋሉ ነበር። ሰዎችን ያለ አግባብ ማሰርና ፍርድ መስጠት ፣ መደብደብ፣ ማሰቃየት እና አካል ማጉደል የማረሚያ ቤ ቶች የዘወትር ስራ እንደነበርም አስታውሰዋለ። በተደረገው ማሻሻያ ግን በማረሚያ ቤቶች ያሁሉ ግፍና በደል ማቆሚያ ተበጅቶለታል ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ረታ በላቸው፤ ከአገራዊ ለውጡ በኋላ የ ዜጎች ሰብዓዊ መብት አያያዝ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል። የተለያዩ አሰራሮችን በመዘርጋት የሰብዓዊ መብት አያያዙ የተሻለ እንዲሆን ለፖሊስ ሰራዊቱ ተከታታይ የ ሙያ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። በክልሉ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ያሉ ዜጎች አያያዝ ሰብዓዊ መብትን ያከበረ መሆኑን ከኢትዮጵያ ሰ ብዓዊ መብት እና ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽኖች የተሰጡ ግብረ መልሶች ማሳያ ናቸው ያሉት ደግሞ የአፋር ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዑመር ኮቲና ናቸው። የህግ ታራሚዎች ትምህርት እንዲማሩ፣ የሙያ ስልጠና እንዲያገኙ ከማረሚያ ቤት ሲወጡም ህግ አክባ ሪ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በትራምፕ ዘመን የተጣለውን የግሪን ካርድ ክልከላ ህግ ሸረውታል::

አዲስ አበባ፣የካቲት 18፣ 2013 ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በትራምፕ ዘመን የተጣለውን የግሪን ካርድ ክልከላ ህግ ሸረውታል:: ትራምፕ 100 ሺህ 14 በሚል ድንጋጌ ያጸደቁት የቪዛ ክልከላ አዋጅ መነሻው የአሜሪካዊያንን የሥራ እድል ይጋፋል የሚል እንደሆነ ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ሆኖም አዲሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይህ አዋጅ አሜሪካን የሚጠቅም ሳይሆን የሚጎዳ ነው በማለት በፊርማቸው ሽረውታል፡፡ የባይደን አስተዳደር በዋናነት ህጉን የሻረበትን […]

በትግራይ ክልል የሰብአዊ ዕርዳታ ተጠናክሮ መቀጠሉን አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 3፣ 2013 ሚኒስቴሩ የኮቪድ -19 በሽታን ከመከላከል አንጻር ባለፉት 6 ወራት ዉጤታማ ስራዎችን ሰርቼያለሁ አለ፡፡ የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ለአርትስ በላከዉ መግለጫ በ2013 በጀት አመት ባለፉት 6 ወራት የኮቪድ ወረርሺኝ ለመከላከል እንዲያግዝ በመላ ሀገሪቱ ከ74 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ማሰባሰብ መቻሉን ገልጿል፡፡ በተጨማሪም በአማራ ክልል በአይነት እህል 1በንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና በቤት ዉስጥ […]