ቻይና የጸረ ሚሳኤል ሙከራና የቀጠናው ውጥረት ማገርሸት
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 የ ቻይና የተሳካ የመካከለኛ ርቀት የጸረ ባለስቲክ ሚሳኤል ሲስተም ሙከራ ማድረጓን ይፋ አደረገች፡፡ የቻይና መካለከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሙከራው ቤጂንግ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊቃጣባት የሚችለውን የሚሳኤል ጥቃት መከላከል ላይ ያተኮረ ነው ብሏል፡፡ ሙከራው የታቀደለትን ግብ ያሳካ ነበር ያለው ሚኒስቴሩ ዓላማውም መከላከልን እንጂ በየትኛውም ሀገር ላይ ስጋት ለመፍጠር እንዳልሆነ ይታወቅልን ነው ያለው፡፡ […]