loading
ኮቪድ 19ን ተከላክለን የተሻለች ሀገር ለመገንባት ባለን ሀብት ላይ እውቀትና ፈጠራን አቀናጅተን መጠቀም ይኖርብናል አሉ ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2012 ኮቪድ 19ን ተከላክለን የተሻለች ሀገር ለመገንባት ባለን ሀብት ላይ እውቀትና ፈጠራን አቀናጅተን መጠቀም ይኖርብናል አሉ ጠ/ሚ ዐቢይ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ፈጠራን በተመለከተ ባስተላለፉት መልእክት፥ ብዙዎቹ የፈጠራ ውጤቶች የፈተና ልጆች ናቸው ይባላል ብለዋል። የሰው ልጆች ከዛሬው ሥልጣኔያቸው ላይ የደረሱት በየዘመናቱ የተደቀኑባቸውን እንቅፋቶች ለማለፍ እውቀትና ክሎታቸውን በስፋት በመጠቀማቸው […]

ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል::

ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል ። የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በተሸጋገረበት ወቅት የህዝቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን የአማራ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ላቀ ጥላዬ ለኢዜአ እንደገለጹት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማጠናቀቅ የአገራችን ሉአላዊነትና የፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ጉዳይ ነው። መንግስትና ህዝብ […]

የደቡብ ሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፐሬዚዳንት ሪክ ማቻር በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው::

የደቡብ ሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፐሬዚዳንት ሪክ ማቻር በተደገላቸው ምርመራ የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው:: ሲጂ ቲ ኤን በዘገባው እንዳስነበበው የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት የማቻር ባለቤት አንጀሊና ቴኒም በቫይረሱ መጠቃታቸው ታውቋል፡፡የማቻር ፕሬስ ሴክሬተሪ ጀምስ ጋትዴት ዳክ እንዳሉት የቢሮ ሰራተኞቻቸው እና የግል ጠባቂዎቻቸው ጭምር በኮቪድ 19 መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ምትል ፕሬዚዳንቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በይፋ ለህዝብ መናገራቸውን እና […]

የብሩንዲ የምርጫ ኮሚሽን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የድምፅ ቆጠራ ውጤቱን በትግዕስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012 የብሩንዲ የምርጫ ኮሚሽን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የድምፅ ቆጠራ ውጤቱን በትግዕስት እንዲጠብቁጥሪ አቀረበ ብሩንዲያዊያን ባለፈው ረቡዕ የኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝ ሳያስፈራቸው የወደፊት ፕሬዚዳንታቸውን ወደ ስልጣን ለማምጣት የሚያስችላቸውን ድምፅ ሲሰጡ ታይተዋል፡፡ የብሩንዲ ብሄራዊ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ቆጠራው ገና ቀናትን ስለምወስድ ከወዲሁ የሚተላለፉ የአሸናፊነት መልእክቶች እንዲቆሙ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ይሁን እና የተቃዋሚ መሪው አጋቶን ሩዋሳ የድምጽ ቆጠራው […]

1441ኛው የኢድ አል-ፊጥር በዓል አርብ ምሽት ጨረቃ ከታየች ቅዳሜ ካልሆነ ግን እሁድ ይከበራል፡፡

1441ኛው የኢድ አል-ፊጥር በዓል አርብ ምሽት ጨረቃ ከታየች ቅዳሜ  ካልሆነ ግን እሁድ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታዉቋል፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ለምእመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በዕለቱ የጀምዓ ሶላት እንደማይኖር የገለጹት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ምእመናን በዓሉን በየቤታቸው እንዲያከብሩት አሳስበዋል፡፡  ምእመናን በዓሉን የተራቡትን በማጉረስ፣ የተጠሙትን በማጠጣት በአጠቃላይ የተቸገሩትን በመርዳት እንዲያከብሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የቴንሴንት ፋውንዴሽን የላካቸውን የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ቁሳቁሶች ተረከበ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012  ጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እነዳስታወቁት  የቴንሴንት በጎ አድራጎት ድርጅት ኮቪድ19 ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚሰራውን ስራ ለማገዝ የሚያስችሉ 1ነጥብ6 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የመመርመሪያ ኪቶችንና ጓንቶችን ድጋፍአድርጓል፡፡ ዶ/ር ሊያ በጎ አድራጎት ድርጅቱ  ስላደረገልን ድጋፍ ልባዊ ምስጋናዬን እየገለጽኩ ሁሌም ትብብራቸው የማይለየንን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ላመሰግንን እወዳለሁ ብለዋል  በፌስቡክ ገጻቸዉ፡፡ የቴንሴንት ኩባንያ የታዋቂው […]

የኮሮና በሽታን ለመከላከል የሚያስችሉ ፈጠራዎችን ያቀረቡ ተወዳዳሪዎች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተላቸዉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012  የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ጋር ባደረጉት የድጋፍ ስምምነት እና በመንግስት እገዛ ሲካሄድ የነበረው የኮቪድ 19 ቴክኖሎጂ ሶሊዩሽን ቻሌንጅ ዉድድር ተለይተዉ ታዉቀዋል።  በአጭር  ጊዜ ተተግባሪና መፍትሔ ሊያመጡ የሚችሉት ምርጥ ፕሮጀክቶች ተለይተው እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ፍጻሜውን ያገኘውን የውድድር ሂደት በንግግር የከፈቱት የኢኖቬሽን ምርምር ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ሲሳይ ቶላ በችግር […]

ጄምኮርፕ ኩባንያ የብሔራዊ የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን አደጋን ለመቀነስ ለሚያደርገዉ ዝግጅት ድጋፍ እያደረኩኝ ነዉ አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ጄምኮርፕ ኩባንያ የብሔራዊ የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን አደጋን ለመቀነስ ለሚያደርገዉ ዝግጅት ድጋፍ እያደረኩኝ ነዉ አለ፡፡ ኩባንያዉ የብሔራዊ የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን 200,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለመግዛት ላወጣው ጨረታ ተወዳዳሪ ሆኖ በመገኘት በድጋሚ ማሸነፉን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ አስታዉቋልጄምኮርፕ ኢኮኖሚውን በንግድ ሥራ ለመደገፍ እና ኢንቨስት ለማድረግ የኢትዮጵያን ገበያ የተቀላቀለው በ2010ዓ.ም. […]

ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆነ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆነ:: በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆኗል።በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የለይቶ ሕክምና ማእከል ውስጥ ክትትል እየተደረገላት ከምትገኝ የ34 ዓመት እናት ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም የተወለደው ሕፃን 3.1 ኪ.ግ. ክብደት ያለው ወንድ ልጅ መሆኑም ታውቋል።ከሕፃኑ በተወሰደው ናሙና ላይ በተካሔደው […]

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀቺው ተጠርጣሪ ተያዘች::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀቺው ተጠርጣሪ ተያዘች:: የአማራ ፖሊስ ከሚሽን እንዳስታወቀዉ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ የሁለት ዓመት ዕድሜ ያለው ህፃን ይዛ በመሰወር የማስለቀቂያ 600 ሺህ ብር የጠየቀችው ተጠርጣሪ መያዟን የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ግለሰቧ በሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት መኖሪያ ቤት ከግብረአበሯ ጋር በመሆን ህፃኑን ይዛ በመሰወር ለህፃኑ […]