loading
ደቡብ አፍሪካ የጣለችውን የእንቅስቃሴ እቀባ የማቅለል ሂደቷን ወደ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ አደረገች::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ደቡብ አፍሪካ የጣለችውን የእንቅስቃሴ እቀባ የማቅለል ሂደቷን ወደ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ አደረገች:: ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከመጭው የፈረንጆች ሰኔ 1 ጀምሮ ህዝቡ ወደ መደበኛ እንቅድቃሴው የሚገባበትን መንገድ መቀየሳቸውን አስታውቀዋል፡፡ ፕሪቶሪያ እገዳዎችን ለማንሳት ስትነሳ ባለ አምስት ደረጃ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በማስቀመጥ ነበር፡፡አሁን ሶስተኛውን ዙር ስትጀምር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ሲባል ጥብቅ የሆኑ የጤና መመሪያዎችን […]

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ምክንያት በማድረግ በትግራይ ክልል እየተፈፀመ ያለዉ ግፍ እንዲቆም ህጋዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልገዉ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ለአርትስ ቲቪ ገለፀ ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ምክንያት በማድረግ በትግራይ ክልል እየተፈፀመ ያለዉ ግፍ እንዲቆም ህጋዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልገዉ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ለአርትስ ቲቪ ገለፀ ፡፡በክልሉ አሁን ድረስ ቀደም ሲል የነበረዉ የአፈናና የእኔ አዉቅልሀለሁ አገዛዝ አሁንም እንደቀጠለ የተናገሩት የፓርቲዉ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት በተለይ የትግራይ ህዝብን ከመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የሚደረገዉ ጥረት ተቀባይነት እንደሌለዉ ተናግረዋል፡፡በመሆኑም በክልሉ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ የሀገራቸውን የፍትህ ስርዓት አጣጣሉ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ የሀገራቸውን የፍትህ ስርዓት አጣጣሉ::በሳምንቱ መጨረሻ ቀን በኢየሩሳሌም አውራጃ በሚገኝ ፍርድ ቤት ቀርበው የክስ ሂደታቸውን የተከታተሉት ኔታኒያሁ የተከሰስኩት በሀሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል፡፡የክሱ ዋና ዓላማ ጠንካራውን ጠቅላይ ሚስትር ከስልጣን ለማውረድ ቢሆንም ይህ ግን አይሳካም በማለት ሀገራቸውን በታማኝነት መምራታቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ኔታኒያሁ እሳቸው የሚመሩትን የቀኝ ዘመም ፖለቲካ አራማጅ የሆነውን ሊኩድ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ለአፍሪካ ቀን” የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ለአፍሪካ ቀን” የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸው አፍሪካ ባለ ብዙ ፀጋ ባለቤት ናት በመሆኑም የአፍሪካ ቀንን ስናከብር የምንፈልጋትን የአፍሪካን እዉን እንድትሆን አንድነታችንን እናጠናክር ብለዋል::የአፍሪካ ቀን “የአፍሪካ ነፃነት ቀን” እየተባለም የሚከበር ሲሆን እ.ኤ.አ ግንቦት 25 ቀን 1963 በ32 ነፃነታቸውን በተቀናጁ የአፍሪካ […]

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኳታር መንግስት ለኢትዮጵያ የሕክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረጉ አመሰገኑ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኳታር መንግስት ለኢትዮጵያ የሕክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረጉ አመሰገኑ:: “የኳታር መንግሥት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች፣ የሕክምና ጓንቶች፣ ፊትን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍኑ እና ሰውነትን ከንክኪ የሚከላከሉ ልብሶች እንዲሁም ሌሎች ኮቪድ-19ን የመከላከያ ግብአቶች መላካችሁ  ወረርሽኙን ለመግታት የምናደርገውን ጥረት ይደግፋል ነዉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ድጋፉ 470 ሺ ማስክ ፣ 70 […]

ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር ሉዓላዊነት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባቸው ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ግንቦት 18፣2012 ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር ሉዓላዊነት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባቸው ተገለጸ:: “የኢትዮጵያ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች ሚና ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግደብ ግንባታ ሁለንተናዊ ድጋፍ እና ተሳትፎ” በሚል መሪ ቃል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዳራሽ ውይይት ተደርጓልበውይይቱ ወቅት በሀገሪቱ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች በሀገር ሉዓላዊነት እና አንድነት ጉዳይ እንደማይደራደሩ ተናግረዋል። በተለያዩ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ልዩነት ቢኖርም […]

በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ አንድ ሺህን ተሻገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ግንቦት 18፣2012 በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ አንድ ሺህን ተሻገረ፡፡ በአህጉረ  አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር እያደገ በመምጣት አሁን ላይ 121ሺን የተሻገረ ሲሆን በወረርሽኙ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሶስት ሺን ማለፉን የአፍሪካ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠሪያ ማዕከል ሲዲሲ ይፋ አድርጓል፡፡ማዕከሉ ማክሰኞ እለት ባወጣው ሪፖርት በአፍሪካ ተጨማሪ ከ46 ሺህ በላይ ሰዎች […]

አቶ ገዱ የዓለም ምግብ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012 የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የዓለም ምግብ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን ዴቪድ ቢስሊይን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ሁለቱ  ወገኖች የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት፣ የበረሃ አንበጣ እና የጎርፍ አደጋ በቀጠናው ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።በተጨማሪም የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከተ መረጃ […]

ደቡብ ኮሪያ ከ49 ቀናት በኋላ ትልቁን የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር አስመዘገበች::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012 ደቡብ ኮሪያ ከ49 ቀናት በኋላ ትልቁን የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር አስመዘገበች::የደቡብ ኮሪያ የበሽታዎች መከላከያ   ማእከል ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳስታወቀው በሀገሪቱ በአንድ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ስፍራ ነው በርካታ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው የተገኙት፡፡ አልጀዚራ   እንደዘገበው ደቡብ ኮሪያ ክስተቱ ያጋጠማት የቫይረሱን ስርጭት ተቆጣጥሬዋለሁ በማለት ትምህርት ቤቶችን መክፈት በጀመረችበት ወቅት መሆኑ ድንጋጤን   ፈጥሯል፡፡ በዚህ […]

በእስር የሚገኙ 3 የሱዳን የቀድሞ ባለስልጣናት በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ታወቀ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 በእስር የሚገኙ 3 የሱዳን የቀድሞ ባለስልጣናት በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ታወቀ:: በቫይረሱ ከተያዙት ግለሰቦች መካከል ሁለቱ በዳርፉር በተፈፀመው የጦር ወንጀል እጃቸው አለበት ተብለው በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሚፈለጉ ናቸው ተብሏል፡፡ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በቫይረሱ የተያዙት የኦማር አልበሽር ረዳት የነበሩት አህመድ ሀሮን፣ የመከላከያና የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር የነበሩት አብደልራሂም ሞሀመድ ሁሴን እንዲሁም ምክትል […]