loading
አብዲ ሞሃመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

አብዲ ሞሃመድ ዑመር ትናንት ከክልሉ ፕሬዚዳንትነታቸው መነሳታቸው ቢገለጽም የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪ ሆነው ይቀጥላሉ ተብሎ ነበር። የቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንት በመከላከያ ሠራዊት አባላት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ከተደረጉ በኋላ ጅግጅጋ ከሚገኘው ቤተ መንግሥት እንደተወሰዱ ምንጮች ለቢቢሲ ሶማልኛ ገልጸዋል። ከቅዳሜ አንስቶ በጂግጂጋ እና በክልሉ ሌሎች ከተሞች የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ወደ […]

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ መጠሪያውን ወደ “ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” ለመቀየር ሀሳብ ማቅረቡ ተገለፀ።

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ መጠሪያውን ወደ “ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” ለመቀየር ሀሳብ ማቅረቡ ተገለፀ። የኦህዴድ የገጠር ፖለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንደገለጹት፥ የኦህዴድን የስያሜ እና የአርማ ለውጥ ለማድረግ ሀሳብ ቀርቧል። በዚህም መሰረት አዲሱ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ መጠሪያ “የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” እንዲሆን ሀሳብ መቅረቡን ነው አቶ አዲሱ ያስታወቁት። ከዚህ በተጨማሪም ኦህዴድ ከዚህ […]

ግብጽ ጥንታዊ ቅርሶቿን አስመለሰች፡፡

ግብጽ ከ500 ዓመት በላይ እድሜ ያላቸውን ቅርሶቿን ከእንግሊዝ መረከቧን የሀገሪቱ የባህል ሚኒስትር ኢሳም አብደል ዳይም ተናግረዋል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ቅርሶቹ የጥንታዊት ግብጽን ታሪኮች የሚያሳዩ የድንጋይ ላይ ጽሁፎችና ስዕሎች ናቸው፡፡ አብደል ዳይም እነዳሉት እነዚህ ጽሁፎች እና ስዕሎች በስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሙህዲን አል ካፊጂ በተባለ ጥበበኛ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ግብጽ ከ50 ዓመት በፊት ከ33 ሺህ በላይ […]

ግብጽ እስረኞችን በይቅርታ መፍታቷን ቀጥላለች፡፡

የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ግብጽ በሳምንት ዉስጥ ለሁለተኛ ግዜ እስረኞችን በይቅረታ ፈታለች፡ ታራሚዎቹ ይቅርታዉን ያገኙት በፕሬዝዳንት አብደልፈታ አልሲሲ በኩል ሲሆን ቁጥራቸዉም 1 ሺህ 188 ይሆናል ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር ነዉ የዘገበዉ፡፡ በይቅርታ ከተለቀቁ እስረኞች መካከል 723ቱ ቅደመ ሁኔታ የተቀመጠላቸዉ መሆኑንም ዘገባዉ አመልክቷል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (ዲ ኤፍ አይ ዲ) ዋና ፀሃፊ ፔኒ ሞርዳውንት ጋር ተወያዩ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (ዲ ኤፍ አይ ዲ) ዋና ፀሃፊ ፔኒ ሞርዳውንት ጋር ተወያዩ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በቲዉተር ገጻቸዉ እንዳስታወቁት ውይይታቸውን በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እና ድህነት ቅነሳ ላይ ያተኮረ ነዉ ብለዋል፡፡የሁለቱ ሀገራት ጠንካራ ግንኙነትን ኢትዮጵያ እንደምታደንቅ በገጹ ተጠቅሷል፡፡

ከተለያዩ ሆስፒታሎች የተዉጣጡ የህክምና ባለሞያዎች በጅግጅጋ በተከሰተዉ ግጭት የተጎዱ ወገኖችን ለማከም ወደ ጅግጅጋ አቀኑ፡፡

ከተለያዩ ሆስፒታሎች የተዉጣጡ የህክምና ባለሞያዎች በጅግጅጋ በተከሰተዉ ግጭት የተጎዱ ወገኖችን ለማከም ወደ ጅግጅጋ አቀኑ፡፡ ሀኪሞቹ ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፤ከየካቲት12 እና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኔየም ሜዲካል ኮሌጅ የተወጣጡ መሆናቸዉን የጤና ጥበቃ ምኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በፌስቡክ ገጻቸዉ ገልጸዋል ወደ ጂግጂጋ የተጓዙት የጤና ባለሞያዎች ሃያ አራት ናቸዉ፡፡

ቶኪዮ የ2020ን ኦሎምፒክ ኮሽ ሳይል እንዲጠናቀቅ ከወዲሁ እየተጋሁ ነዉ አለች፡፡

ቶኪዮ የ2020ን ኦሎምፒክ ኮሽ ሳይል እንዲጠናቀቅ ከወዲሁ እየተጋሁ ነዉ አለች፡፡ እንደ አዉሮፓዉያኑ አቆጣጠር በ2020 ጃፓን የምታስተናግደዉ የበጋ ኦሎምፒክ በደህንነቱ በኩል የተዋጣለት እንዲሆን በአይነቱ ልዩ የሆነ ቴክኖሎጂ እጠቀማለሁ ብላለች፡፡ በዉድድሩም ለመጀመርያ ግዜ ተግባራዊ የሚደረገዉ ይህ ቴክኖሎጂ በጃፓኑ ኩባንያ ኔክ የተፈበረከ ሲሆን እያንዳንዱን ተሳታፊ በፊት ገጽታዉ ማስታወስ የሚችል ነዉ፡፡ ይህ ማለት ሁሉም ተሳታፊዎች ልክ እንደ አሻራ መታወቂያቸዉ […]

የሰብአዊ መብት ጥሰት ደርሶብናል ያሉ 300 የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት ፤ዲያቆናትና አገልጋዮች ፍትህ ማግኘታቸዉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ካህናቱ ከአስተዳደረዊ በደል በተጨማሪም ከስራ መባረር፤ የደሞዝ ክፍያን አለማግኘት፤ ያለቅድመ ዝግጅትና ፍትሃዊ ያልሆነ ዝውውር እንዲሁም ያለ ስራ መንገዋልል ከዋነኞቹ የመብት ጥሰቶች እንደሚካተቱ ቅሬታው የደረሰው የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተናግሯል፡፡ በኮሚሽኑ የከፍተኛ ኮሚሽነር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድሜነህ ዘውዱ እንዳሉት ኮሚሽኑ ላለፉት ሁለት ዓመታት ጉዳዩን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር በመሆን ሲመረምር ቆይቶ ተገቢውን ውሳኔ አስተላልፏል ብለዋል […]

በጂግጂጋ እና ሌሎች ከተሞች የሃገር መከላከያ ሰራዊት እያደረገ ያለው የማረጋጋት ስራ መቀጠሉን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ ተናገሩ።

ሚኒስትሩ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ የሃገር መከላከያ ሰራዊት በጂግጂጋና በሌሎች የሶማሌ ክልል ከተሞች በመግባት የማረጋጋት ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። አሁን ላይ ችግሩን በአንድ ጊዜ ለመመለስ ከባድ ቢሆንም መከላከያ ሰራዊት በከተሞች በመግባት ችግር ሲፈጠር መቆጣጠርና ማረጋጋት የሚያስችል ዝግጅት ማድረጉንም ነው የተናገሩት። በስፍራው የተፈጠረውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለማረጋጋት የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም የሃገር ሽማግሌዎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል። […]

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኢምባሲ የመጀመርያ ዲግሪ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ነፃ ትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኢምባሲ የመጀመርያ ዲግሪ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ነፃ ትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ የመጀመርያ ዲግሪ ላላቸው ኢትዮጵያውን ነጻ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኢምባሲ ከፍተኛ የፖለቲካ ባለሙያ ጀሚ ኦርተን ገልጸዋል፡፡ ጀሚ ኦርተን ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ የእድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑት ተማሪዎች በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ የመጀመርያ ዲግሪ ያላቸው አምልካቾች መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ አመልካቾች ሁለት […]