loading
በአክሱም ጽዮን ለሀገራችን ሰላም ምህላ እየተደረገ ነዉ፡፡

በምህላዉ ከ50 ሺህ ሰዉ በላይ እየታደመ እንደሚገኝ በአክሱም ጺዮን የስብከተ ወንጌል ምክትል ሀላፊ በኩረ ትጉሃን ስቡህ ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ ከነሐሴ አንድ ጀምሮ የፍልሰታ ጾምን አስመልክቶ የተጀመረዉ ምህላ አስከ ጾሙ ማብቂያ ድረስ ይቀጥላል፡፡፡በአክሱም ፂዮን ሁልጊዜ ወር በገባ ከ1-7 ባሉት ቀናት ምህላ የሚደረግ ሲሆን የፍልሰታ ፆም አስመልክቶ ደግሞ እስከ ጾም ፍቺ ምህላ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በኩረ ትጉሃን የዘንድሮዉን […]

የመን ውስጥ በደረሰ የአየር ጥቃት ህጻናት ህይዎታቸው አልፏል።

ቢቢሲ እንደዘገበው በጥቃቱ አርባ ሶስት ሰዎች ተገድለዋል። ከሞቱት ሰዎች መካከልም አብዛኞቹ ህጻናት መሆናቸውን የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል። የቀይ መስቀል ሰራተኞችም በርካታ ህጻናት ቆስለው ወደ ሆስፒታል መምጣታቸውን ምስክርነታቸውን ሰጠተዋል። የጥምር ሃይሉ ሆን ብሎ ሲቪል ሰዎችን ኢላማ አድርጎ ጥቃቱን እንዳላደርሰ ቢናገርም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ግን ዓለም አቀፍ ህግን የጣስ ተግባር ሲል ድርጊቱን ኮንኖታል። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው […]

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚያካሄድ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ዶክተር ታቦር ገብረ መድህን ገለጹ።

አፈ ጉባኤው ዶክተር ታቦር እንዳሉት ምክር ቤቱ ዛሬ ሰባት ሰዓት በሚያካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ከሚመለከታቸው አጀንዳዎች መካከል አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትን ማጽደቅ እና ምክር ቤቱ በወረዳ ደረጃ የሚገኙ አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀትን የሚመለከት አዋጅም መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል አፈ ጉባኤ።

የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳልህ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ።

የኤርትሪያን ፕሬስ እንደዘገበዉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኢፌዴሪ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጉብኝቱ ዳግም የተጀመረውን የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንደሚያግዝም ታምኖበታል። ኢትዮጵያና ኤርትራ ለ20 አመታት አቋርጠውት የነበረውን ግንኙነት ዳግም መጀመራቸው ይታወሳል። በቅርቡም የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ወደ ኤርትራ በማቅናት ከኤርትራው […]

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጀዋር ሙሃመድ ዛሬ በባሕር ዳር ከሚገኙ ወጣቶች እና አክቲቪስቶች ጋር በአቫንቲ ብሉ ናይል ሆቴል ይወያያል።

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጀዋር ሙሃመድ ዛሬ በባሕር ዳር ከሚገኙ ወጣቶች እና አክቲቪስቶች ጋር በአቫንቲ ብሉ ናይል ሆቴል ይወያያል። ከጃዋር ጋር ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳን ጨምሮ ከኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የተገኙ ልዑካንም የሚሳተፉ ሲሆን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ አስር ግለሰቦች ከጎንደር እንዲሚገኙ ታውቋል።

አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ፖለቲካ ትግሉ ልንመጣ የምንችለው ያፈረሰን የምርጫ ቦርድ እራሱ ከፈረሰ ብቻ ነው አሉ፡፡

ፓርቲ ከሌለኝ በግለሰብ ደረጃ የማደርገው ተሳትፎ ብዙም ጥቅም ይኖረዋል ብዬ አላስብም ብለዋል ለቢቢሲ፡፤ መቀሌ ተዘጋጅቶ በነበረ ጉባኤ መሳተፋቸው ያላስደሰታቸው ወገኖች ዛቻና ማስፈራሪያ እንዳደረሱባቸውና ይህም ለውሳኔ እንዳበቃቸው ተናግረዋል። ለምን መቀሌ ሄዶ ስብሰባ ተካፈለ ብለው ከፍተኛ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተውብኝ፤ እንገድልሃለን፤ ንብረትሀን እናቃጥላለን የሚሉ መልእክቶች እየደረሱኝ ነው ብለዋል። በድርጅት ደረጃ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ እስከሌለ ድረስ፤ ነጻ ሐሳባቸውን […]

ናይጄሪያ የሰብል ምርት እጥረት አሳስቧታል።

በአፍሪካ በህዝብ ብዛቷ ቀዳሚ የሆነችው ናይጄሪያ በየዓመቱ ስድስት መቶ ሚሊዮን ቶን ሩዝ ለምግብ ፍጆታ ታውላለች። ሲ ጂቲ ኤን እንደዘገበው ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉን የምታስገባው ከቻይና ነው ። የናይጀሪያ የግብርና ተማራማሪዎች በሃገሪቱ ያለውን የምርት እጥረት ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው። ተማራማሪዎቹ ከቻይና የተሻሻለ የሩዝ ዝርያ በማስገባት አርሶ አደሮቹን ምርታማ ለማድረግ ነው እየሰሩ ያሉት። የተሻሻለው ዝርያ ቀድሞ […]