loading
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ነገ ወደ አሜሪካ ይሄዳሉ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩንም እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሚያደርጉት ጉዞ በአጠቃላይ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፥ በሀገራቸው እየተካሄደ ላለው ሁለንተናዊ ለውጥ አካል ሆነው ለሀገሪቱ ልማትና እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ያለመ ነው ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሎስ አንጀለስ እና በዋሽንግተን ዲ ሲ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ሐምሌ 24 ቀን ድረስ ነው በአሜሪካ ቆይታ የሚያደርጉት። የኢፌዴሪ […]

ቡናችን በዓለም ገበያ የሚፈለገዉን ያህል አልተዋወቀም ተባለ

ይህ የተባለዉ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንና ከቡና ላኪዎች ማህበር ጋር በጋራ ባዘጋጁት ቡናን በአለም ማስተዋወቅ ላይ ባተኮረ የዉይይት መድረክ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ የቡናና ሻይ ባለስልጣን የገበያ ልማት ቁጥጥርና የግብይት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሻፊ ዑመር በሀገራችን ከ25 ሚሊየን በላይ ህዝብ ኑሮዉ በቡና ምርት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የምናመርተዉ ቡና ግን ጥራቱን የጠበቀ ባለመሆኑ አምራቹን መጥቀም አልተቻለም […]

ሺ ጂፒንግ ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ ለብሪክስ ስብሰባ ነው ደቡብ አፍሪካ የተገኙት፡፡ ፕሬዝዳንቱ በመካከለኛው ምስራቅና በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ጉብኝታቸውን የጀመሩ ሲሆን ከነገ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ በሚካሄደው 10ኛው የብሪክስ ጉባዔ ይሳተፋሉ፡፡ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይናና ደቡብ አፍሪካ በጋራ ያቋቋሙት የትብብር ተቋም በዋናነት በሀገራቱ መካከል ያሉትን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት ታስቦ ነው የተመሰረተው፡፡ ፕሬዝዳንት ሺ ጆሀንስበርግ በምታስተናግደው በዚህ ጉባዔ […]

በግሪክ በተቀሰቀሰ ሰደድ እሳት በርካቶች ህይወታቸውን አጥተዋል

በቦታው የተሰማሩ የነፍስ አድን ሰራተኞች እንዳሉት በዋና ከተማዋ አቴንስ አቅራቢያ በተከሰተው አደጋ እስካሁን 49 ሰዎች ሞተዋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ከሟቾቹ መካከል ህጻናት የሚበዙ እንደሆነ ታምኗል፡፡ ሲ ኤን ኤን በዘገባው እንዳሰፈረው በግሪክ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2007 ወዲህ እንደዚህ ዓይነት የከፋ የእሳት አደጋ አጋጥሞ አያውቅም፡፡ ከሟቾቹ በተጨማሪ 156 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡ ከነዚህ መካከል ደግሞ አስራ አንዱ […]

ሰሜን ኮሪያ የሮኬት ማስወንጨፊያ ጣቢያዎቿዋን ማፍረስ መጀመሯ ተሰማ

የሳተላይት ምስል እንደሚያሳየው ፒዮንግያንግ ቁልፍ የሮኬት ማስወንጨፊያ ጣቢያዎቿን እያፈረሰች መሆኗ ተረጋጋጧል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው በተችዎቻቸው ዘንድ መቆሚያ መቀመጫ ላጡት ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ ትልቅ እፎይታ ነው፡፡ በሁኔታው የተደሰቱት ትራምፕም እኔ ያላልኩትን የሚያራግቡና የሀሰተኛ ወሬ የሚያናፍሱ በሰሜን ኮሪያ ድርጊት ተበሳጭቷል ለሚሉ ሁሉ ይሄው እኔ ደስተኛ ነኝ የሚል ጽሁፍ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ ይሁንና የአሜሪካ ባለስልጣናት ሰሜን ኮሪያ የምታፈርሰው […]

የሞሮኮ አየር መንገድ ለዛሬ ተይዘው የነበሩ በረራዎችን ለመሰረዝ ተገዷል

ምክንያቱ ደግሞ አብራሪዎቹ የስራ ማቆም አድማ በመምታታቸው ነው ብሏል የሞሮኮ ሮያል አየር መንገድ በድረ ገጹ ባሰራጨው ጽሁፍ፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው አብራሪዎቹ ስራ ለማቆም ያስገደዳቸው ላቀረቡት የደሞዝና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ጥያቄ ከአሰሪ ድርጅታቸው አጥጋቢ መልስ አለማግኘታቸው ነው፡፡ በድርጅቱና በሰራተኞቹ መካከል ለወራት የዘለቀ ድርድር ቢደረግም መግባባት አልተቻለም ብለዋል የአብራሪዎች ማህበር አመራሮች፡፡ አየር መንገዱም ሰራተኞቹ ወደ ስራ ገበታቸው […]

የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች “መደመር በተግባር ” እያሉ ነው

የኪነጥበብ ባለሙያዎች የገቡትን ቃል ጠብቀው በጥቁር አንበሳ፣ በአለርት እና በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታሎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ አርቲስቶቹ ከአድናቂዎቻቸው ጋር በመሆን “መደመር በተግባር” የሚል መሪ ቃል ይዘው ደም የመለገስ ተግባር ፈጽመዋል፡፡

መሪዎቹ ሜዳልያ ተሸለሙ

በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዲሰፍን ላበረከቱት አስተዋፅኦ የሀገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ ሜዳሊያ ሸለሙ።