loading
አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ከዳሸን ቢራ ቦርድ አባልነት ተሰናበቱ

የዳሸን ቢራ ፋብሪካ የቦርድ አባል የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ታደሰ ካሳና አቶ ወንድወሰን ከበደ ከቦርድ አባልነት መሰናበታቸውን ዳሽን ቢራ አክሲዮን ማህበር ለአርትስ ቲቪ በላከዉ መግለጫ አረጋግጧል፡፡ መግለጫው ተሰናባቾቹን የቦርድ አባላት የተኩት አዳዲሶቹ አባላትን አሳዉቋል፡፡ አባላቱም የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ አብተው፣ በቅርቡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ የሆኑት ዶክተር ይናገር ደሴ እና የጥረት […]

የ ኮድ 3 አጋዥ ታክሲ ባለቤቶች በሰልፍ አቤቱታ እያቀረቡ ነው ።

“ጥያቄአችን ካልተመለሰ ስራ እናቆማለን” ብለዋል ። በአዲስ አበባ ከተማ በአጋዥ ታክሲ ትራንስፖርት አግልግሎት ላይ የተሰማሩ ኮድ 3 ሚኒባስ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች 22 አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት ፊትለፊት አቤቱታ ለማቅረብ ስራ አቁመው ተሰልፈዋል። የተቃውሞው መነሻ “የተተመነው የታክሲ ታሪፍ ከተሰጠን ስምሪት ርቀት ጋር ባለመጣጣሙ ለኪሳራ እየዳረገን ስለሆነ ይሻሻልልን” የሚል ነው። በአሁኑ ሰአት በመቶዎች የሚቆጠሩ […]

በኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ላይ ጭማሪ ሊደረግ ነው::

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች ላይ የታሪፍ ጭማሪ ለማድረግ አስፈላጊው ሂደት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ማሻሻያው ዝቅተኛ የኃይል ተጠቃሚዎችን አያካትትም ተብሏል፡ ቢቢሲ የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ጌታሁን ሞገስን አናግሮ እንደዘገበዉ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪው በተለያዩ ደረጃዎች አልፎ ተቀባይነት ሲያገኝ ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል። አቶ ጌታሁን የታሪፍ ጭማሪ ማድረግ ያስፈለገበትን ምክንያት ለመጨረሻ ጊዜ የታሪፍ ጭማሪ ተደርጎ […]

በቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓት ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማዳን ተቻለ፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሚሽን ኤጀንሲ ከግብርና እንስሳት ሃብት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን የቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓትን በተመለከተ ውይይት አካሂዷል፡፡ የቀጥታ የዘር ግብይት ስርዓት በማስረጽ ከዚህ በፊት በዘር አከፋፋይ እና በአርሶ አደሩ ይደርስ የነበረውን ችግር እና ውጣውረድ በማስቀረት ዘር አምራቹን ከአርሶ አደሩ ጋር በቀጥታ በማገናኝት ይባክን የነበረውን የሰው ጉልበት እና ሃብት ማስቀረት ተችሏል፡፡ የግብርናና አንስሳት ሃብት ሚኒስቴር […]

አንድ ሺህ አምስት መቶ የዘንድሮ ተመራቂዎች በአንድ ሰዓት ውስጥ ከቀጣሪዎች ጋር ይገናኛሉ፡፡

ይህ የሚሆነዉ በናሽናል ኬረርስ ኤክስፖ 2018 ነዉ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮ ጆብስ ጋር በጋራ በመሆን ˝ ናሽናል ኬረርስ ኤክስፖ 2018 ˝ በሚል የዘንድሮ አመት ስራ ፈላጊ ተመራቄዎችን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የሚገናኙበት መድረክ በሚሊኒየም አዘገጅቷል፡፡ የኢትዮ ጆብስ ሪጅናል ኮርዲኔተር ወ/ሮ ህሊና ለገሰ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት ለመጀመሪያ ግዜ በተዘጋጀው አውደ ርዐዩ ቁጥራቸው አንድ ሺህ አምስት መቶ የዘንድሮ ተመራቂዎች […]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2010 በጀት አመት ከ89 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘሁ አለ፡፡

ገቢዉ ካለፈዉ አመት ጋር ሲነጻጸር የ1/4ኛ አድገት ማሳየቱንና፤ የተጣራ 6.8 ቢሊዮን ብር ማትረፉንም ተናግሯል፡፡ ዛሬ አየር መንገዱ የዘንድሮውን አመት እቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ባቀረበዉ ሪፖርት እንደጠቆመዉ በዚህ ዓመት በአፍሪካ ሀገራት የነበረዉን አለመረጋጋት፣የንግድ ጦርነት ፣የነዳጅ ዋጋ መጨመር ችግር የነበረ ሲሆን፤ከአየር መንገዱ አጠቃላይ ወጪ 40 በመቶ የሚሆነዉ ለነዳጅ ወጪ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ […]

አቡዳቢ ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ልትዘረጋ ነው ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሪም አል ሃሺሚ አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተው በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል። ሚድል ኢስት ሞኒተር የኢትዮጵያ የስራ ኃላፊዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሩ ከአዲስ አበባ አሰብ ይዘረጋል ። የጠቅላይ ሚንስትሩ የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አርጋ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ከአቡዳቢ ጋር የተደረገው ውይይት በኢንቨስትመንት፣በግብርናና በሌሎች ዘርፎች […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ ጎበኙ፡፡

ከጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ በተጨማሪ ዱከም ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጨምሮ በጅማና በቦንጋ የሚገኙ የጫካ ቡናዎችን ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ከመጡ ባለሀብቶች ጋር መጎብኘታቸውን የጅማ ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በጉብኝቱ ወቅትም ባለሀብቶቹ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። በ61 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር […]