loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በገበታ ለሀገር እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ።

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በገበታ ለሀገር እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ የዛሬ ዓመት ቃል የገባነውን ፈጽመን በተግባር አሳይተናል ብለዋል። በገበታ ለሀገር ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን እንዲያዋጡ የተዘጋጀውን የባንክ ሂሳብም ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚህም የ10 ሚሊየን እና የ5 ሚሊየን ብር ገቢ ለማድረግ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ ማንኛውም […]

የመንገድ ፈንድን ኤጀንሲ ደረሰኝ በማስመሰል ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ እያጣ እንደሆነ ገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 20፣ 2012 የመንገድ ፈንድን ኤጀንሲ ደረሰኝ በማስመሰል ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ እያጣ እንደሆነ ገለፀ፡፡ ኤጀንሲዉ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ፤ለመንገድ ፈንድ በአዋጅ ከተለዩ የገቢ ምንጮች አንዱ ክብደትን መሰረት ካደረገ አመታዊ የተሽከርካሪዎች ፈቃድ ማደሻ ክፊያ የሚገኝ ገቢ ነው እሱም እየተጭበረበረ ነዉ ብሏል፡፡ ይሄንን ገቢ ከኢትዮጵያ ፖስታ ቤት ጋር የመንግድ ፈነደ ጽ/ቤት […]

በግል ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች የምዝገባ እና የትምህርት ክፍያ ላይ ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ እንደማይደረግ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 27፣ 2012  በግል ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች የምዝገባ እና የትምህርት ክፍያ ላይ ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ እንደማይደረግ ተገለፀ:: የትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ ከነሃሴ 20 ጀምሮ እንዲከናወን ሚኒስቴር ማስታወቁን ተከትሎ ከተማሪዎች ምዝገባ እና ከትምህርት ክፍያ ጋር ተያይዞ ወላጆች ቅሬታን እያቀረቡ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ የግል ትምህርት ቤቶቹ የትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ […]

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 27፣ 2012 ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።ዩኒቨርስቲዉ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ከ5 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በሻምቡ ካምፓስ እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ ፕሮጄክቶች ያሉበት ደረጃ ተጎብኝተዋል። የጉብኝቱ ዋና አላማም በመገንባት ላይ ያሉ እና ተገንብተው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ያሉበት ደረጃ በመገምገም የወደፊት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ታቅዶ የተካሄደ መሆኑን የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት […]

የአንድ ሀገር ብልጽግና ከማኅበራዊ ኃላፊነት መጎልበት ጋር ከፍተኛ ትሥሥር አለው ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ:

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012 የአንድ ሀገር ብልጽግና ከማኅበራዊ ኃላፊነት መጎልበት ጋር ከፍተኛ ትሥሥር አለው ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ::የአንድ ሀገር ብልጽግና ከማኅበራዊ ኃላፊነት መጎልበት ጋር ከፍተኛ ትሥሥር እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት “ማኅበራዊ ኃላፊነት ዝቅተኛ የሆነባቸው ሀገራት ለዕድገት ብዙ ማገዶ ይጨርሳሉ” ብለዋል። “የመሠልጠን ጉዟቸውም መሰናክል […]

አቶ ልደቱ አያለው በምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በሌላ መዝገብ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012 አቶ ልደቱ አያለው በምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በሌላ መዝገብ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል። አቃቤ ህግም በችሎቱ ተገኝቶ እጃቸው ላይ የተገኘ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ የሚል እና ለውጡን ተቃርኖ “ለውጡ ከድጡ ወደ ማጡ” የሚል ርእስ የተሰጠው የፖለቲካ ይዘት ያለውና ህገ መንግስቱን ለመናድ አልሞ የተዘጋጀ ሰነዶችን ተከትሎ ክስ ለመመስረት እየመረመረ […]

የአሜሪካ ልማት ተርአዶ ድርጅት የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ አበረከተ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012 የአሜሪካ ልማት ተርአዶ ድርጅት የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ አበረከተ:: ዓለም አቀፉ የአሜሪካ ልማት ተርአዶ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤይድ) የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ አበረከተ። ዩ.ኤስ.ኤይድ ኢትዮጵያ በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው፥ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ባለበት በዚህ ወቅት ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር የመመርመር አቅመን ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ […]

የጎንደር ከተማን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል በ64 ሚሊዮን ብር የተቆፈሩ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012 የጎንደር ከተማን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል በ64 ሚሊዮን ብር የተቆፈሩ:: ጥልቅ ጉድጓዶች በቅርቡ አገልግሎት እንደሚጀምሩ የከተማው አስተዳደር አስታወቀ።   የአስተዳደሩ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃይማኖት በለጠ ለኢዜአ እንደገለጹት የከተማውን የውሀ አቅርቦት ለማሻሻል በመካከለኛ ጊዜ እቅድ ከተያዙ አምስት ጥልቅ ጉድጓዶች የሁለቱ ቁፋሮ ተጠናቋል ። ጥልቅ ጉድጓዶቹ የሚያመነጩትን ውሀ ወደ […]

አርትስ ቴሌቭዥን በአርትስ ቨርችዋል ባዛር ለሚሳተፉ ተመልካቾቹ የመኪና ሽልማት አዘጋጀ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 29፣ 2012 አርትስ ቴሌቭዥን በአርትስ ቨርችዋል ባዛር ለሚሳተፉ ተመልካቾቹ የመኪና ሽልማት አዘጋጀ፡፡አዲስ ሱዙኪ አልቶ 2020 ሞዴል መኪናም ለሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡አርትስ ቴሌቭዥን ባዘጋጀዉ የመጀመርያዉ ቨርችዋል ባዛር እየተካሄደ ሲሆን ለተመልካቾቹ እና ሸማቾችም በየቀኑ ከሞባይል አነስቶ ተለያዩ ሽልማቶችን በየቀኑ ይሸልማል፡፡ የአርትስ ቲቪ ስራ አስፈጻሚ አዜብ ወርቁ እንደገለጹት የመኪና ቶምቦላ ሽልማቱ ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፍቃድ ያገኘ ሲሆን ከዳሽን […]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን የአንድ ዓመት ወጪ ለመሸፈን ቃል ገባ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4፣ 2012 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን የአንድ ዓመት ወጪ ለመሸፈን ቃል ገባ:: ለ2013 ዓ.ም የሚሆን ስጦታ በሚል በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን በሙሉ የአንድ ዓመት የህክምና ወጪ እንደሚሸፍን የከተማ አስተዳደሩ ቃል ገብቷል፡፡ ዛሬ እየተከበረ የሚገኘውን የምስጋና ቀን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ […]