loading
ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የተጠናከረ ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2013 ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የተጠናከረ ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ:: ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር እየደረሰ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የተጠናከረ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ የብሔራዊ መንገድ ደህንነት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ገለጸ። ለፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት እንዲሁም ለትራፊክ ማኔጅመንት ጽህፈት ቤት አባላት የአደጋውን ምክንያት ለመቀነስ […]

በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ኮቪድ 19ን ለመከላከል እና ህክምናዉን ለማገዝ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር በጥሬ እና 2 ነጠብ 7 መሊዮን ዶላር በቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸዉ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013  በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ኮቪድ 19ን ለመከላከል እና ህክምናዉን ለማገዝ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር በጥሬ እና 2 ነጠብ 7 መሊዮን ዶላር በቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸዉ ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸዉ በዶክተር እናዉጋዉ መሀሪ የተመሰረተዉ ፒፕል ቱ ፕፕል የተባለዉ ግብረሰናይ ድርጅት ባዘጋጀዉ ዌቢናር ላይ ነዉ ፡፡በዌቢናሩ ከኮቪድ 19 […]

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ከቦንድ ሽያጭ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ለማሰባሰብ እየተሰራ ነው ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ለታላቁ የኢትዮዽያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ እየተካሄደ መሆኑን የዞኑ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበርያ ምክር ቤት አስታዉቋል::የታላቁ የኢትዮዽያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 10ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የቦንድ ግዢ ሳምንት በዞኑ አወዳይ ከተማ በይፋ ተጀምሯል:: የዞኑ የታላቁ የህዳሴግድብ ግንባታ ማስተባበርያ ምክር […]

በኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ከሚቀርብባቸው መንገድ አንደኛው የሪል እስቴት ዘርፉ ነው፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 በኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ከሚቀርብባቸው መንገድ አንደኛው የሪል እስቴት ዘርፉ ነው፡፡መኒ ላውንደሪንግ ወይም የገንዘብ እጥበት ሌላኛው ስሙ ነው፡፡በኢትዮጵያ ከመኒ ላውንደሪንግ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አልሚዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለሸገር ነግሯል፡፡ ገንዘብ ከማሸሽ እና በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ከማቅረብ ማዕዘን […]

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይህን ያሉት ለሁለት ቀናት ወደ ኤርትራ ባደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር በአስመራ ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው:: ሁለቱ መሪዎች በትግራይ ክልል ከተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና ተያያዥ ጉዳዮች […]

ኢትዮጵያ 300 ሺህ ሲኖፋርማ የኮቪድ19 ክትባት ከቻይና ተረከበች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2013 ኢትዮጵያ 300 ሺህ ሲኖፋርማ የኮቪድ19 ክትባት ከቻይና መንግስት ተረከበች። በኢትዮጰያ የቻይናው አምባሳደር ዣሆ ዢያን ኢትዮጵያ ቻይና በኮቪድ19 በተጠቃች ጊዜ ወዳጅነቷን ያሳየች ጠንካራ አጋር መሆኗን ተናግረዋል። አምባሳደሩ በቀጣይም ቻይና መሰል ድጋፎችን ታደርጋለችም ነው ያሉት፡፡ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ቻይና ዛሬ ካደረገችው ድጋፍ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም የኮቪድ19 መከላከያ […]

ዳያስፖራው ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013 ዳያስፖራው ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ ፡፡ ዳያስፖራው ባለፉት 10 ዓመታት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓም መቀመጡ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና […]

ተቋማቱ በቁጥጥር የተለዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013 የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ አበባ ሪጂን በቁጥጥር ለተለዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ።ተቋሙ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስአበባ ሪጂን ላይ በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በተለዩ ግኝቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት […]

አራት ተጠርጣሪዎች ከተሰረቁ የመኪና መለዋወጫዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዋሉ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 24 ፣ 2013 በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለልማት በተዘጋጁ ቦታዎች ላይ በተደረገ አሰሳ አራት ተጠርጣሪዎችን ከተሰረቁ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ክልል ልዩ ቦታ አሜሪካ ግቢ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው። መንግስት ለልማት ብሎ ባዘጋጀቸው ቦታዎች […]

ኢዜማ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች ችግር ያቃልላሉ ያላቸውን 138 ቁልፍ ግቦችን የያዘ የቃል ኪዳን ያለውን ሰነድ ዛሬ ይፋ አደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 ፓርቲው በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለመዲናዋ ነዋሪዎች ሊሰሩላቸው ይገባሉ ብሎ የለያቸውን 138 ቁልፍ ግቦች አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዳሉት ‘‘ኢዜማ እውነተኛ ፌዴራሊዝም መሰረቱ ያልተማከለ የአስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ነው’’፡፡አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ከተማ ብትሆንም በቅድሚያ ለሚኖሩባት ዜጎች ምቹ ሆና እንድትገኝ ማድረግ ይገባናልም ብለዋል። “ፓርቲው ከሕዝቡ ጋር ወርዶ ባደረገው […]