loading
በብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የአየር ወለድ አሰልጣኝ የነበረችው መ/አለቃ አይዳ አሌሮ ተፈታች፡፡

ወደ መከላከያ ሠራዊት የተቀላቀለችው በ1997 ዓ.ም የሥልጠና ቦታው ብር ሸለቆ የምልምል ወታደሮች ማሠልጠኛ ነው፡፡ አይዳ በውትድርና ስልጠና ከፍተኛ ውጤት ያመጣች ተመራቂ ናት፡፡ በፓራሹት 27 ጊዜ በመዝለል የምትታወቀው አይዳ በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በ2009ዓ.ም ስትሰለጥን ከ1800 ሰልጣኞች አንደኛ መሆኗ ልዩ ያደርጋታል፡፡ በቅርቡ ከሽብር ቡድን ጋር ተገኛኝተሻል ተብላ ክስ ቀርቦባት ነበር፡፡ በተጨማሪም ውስጥ ለውስጥ ሠራዊቱን በማነሳሳት አገር በማስከዳት […]

የነልደቱ አያሌዉ ኢዴፓ ፈረሰ፡፡

የነልደቱ አያሌዉ ኢዴፓ ፈረሰ፡፡ ፓርቲዉ ከ1አመት ከ8 ወር በፊት በቀድሞ የኢዴፓ ፕሬዝደንት ዶክተር ጫኔ ከበደ በፓርቲዉ ላይ በከፈቱት ክስ ምክንያት ፤በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምስክርነት ፓርቲዉ በፍርድቤት እንዲፈርስ ተወስኖ እንደነበር አቶ ልደቱ አያሌዉ ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡: ሆኖም እንደ አቶ ልደቱ ገለጻ ፍርድቤቱ ያሳለፈዉን ዉሳኔ ለማስቀልበስ አስከ ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ድረስ አቤቱታ ብናቀርብም ምላሽ […]

በሀዋሳ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ፡፡

የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት በሀዋሳ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ከ 1 ወር በላይ የቆዩ ተፈናቃዮች ከዛሬ ጀምሮ ወደ የቀያቸዉ ይመለሳሉ ብለዋል፡፡ አቶ ሚሊዩን ተፈናቃዮቹ የሚመለሱባቸዉ መንደሮች የቀድሞ ሰላማቸዉን ማግኘታቸዉን ተናግረዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ እስኪቋቋሙ ድረስ ቤተሰብ ላላቸው በወር 4 ሺ ብር ፤ቤተሰብ ለሌላቸው ደግሞ በወር 2 ሺ […]

የጀዋር መሐመድ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦ ኤም ኤን /OMN ) የአዲስ አበባ ቢሮ የፊታችን እሁድ በይፋ ይመረቃል፡፡

የጀዋር መሐመድ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦ ኤም ኤን /OMN ) የአዲስ አበባ ቢሮ የፊታችን እሁድ በይፋ ይመረቃል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች እንዳስታወቀዉ በሚሊኒየም አዳራሽ የኦ ኤም ኤን ሥራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የሀገር ሽማግለዎችና ቄሮዎች በተገኙበት የቢሮ ምረቃና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይካሄዳል ተብሏል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ13 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ በተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ተመርምሮ፣ በየኮሌጆቹ አካዳሚክ ጉባኤዎች ተፈትሾና በዩኒቨርስቲው ሴኔት ታይቶ ይሁንታ ያገኘውን መረጃ ተመልክቶ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡ በዚህም መሠረት፡-ፕሮፌሰር ተሾመ ሶሮመሳ፣ፕሮፌሰር አሰፋ ወልደማርያም፣ፕሮፌሰር ወርቅነህ ቀልቤሳ፣ፕሮፌሰር በቀለ አበበ፣ፕሮፌሰር ዳንኤል አሥራት፣ፕሮፌሰር ንጉሴ መገርሳ፣ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ለማ፣ፕሮፌሰር ጥላሁን ተክለኃይማኖት፣ፕሮፌሰር አበበ በቀለ፣ፕሮፌሰር ኃይሉ ወርቁ፣ፕሮፌሰር ሽመልስ አድማሴ፣ፕሮፌሰር ላይከማርያም አስፋውና ፕሮፌሰር አባተ ባኔ የሙሉ […]

በሰኔ 16 የቦምብ ፍንዳታ ከተጠረጠሩት ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው::

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ድጋፍ ለመስጠት ሰኔ 16 ቀን 2010 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀ ሰልፍ ላይ ቦምብ በማፈንዳት ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው። መርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ያሰረከበባቸው ተጠርጣሪዎች አብዲሳ ቀነኔ፣ ደሳለኝ ተስፋዬ፣ ጌቱ ግርማ፣ ህይወት ገዳ እና ባህሩ ቶላ ናቸው። የፌደራል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች […]

ኢትዮጵያ ለሽምግልና ልትቀመጥ ነዉ፡፡

ኢትዮጵያ የምትሸመግለዉ ኤርትራንና ጅቡቲን ነዉ፡፡ የዉጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በሰጡት መግለጫ በሁለቱ ሀገራት መሀከል ያለዉ ችግር ተቀርፎ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲሰፍን ኢትዮጵያ ለጅቡቲዉ ፕሬዝዳንት መልክት ልካለች ብለዋል፡፡ ሁለቱ ሀገራትም ለሽምግለና ለመቀመጥ መልካም ፍላጎትን አሳይተዋል ተብሏል፡፡

ለህፃናት ሞት መቀነስ ዋና መፍትሄ ጡት ማጥባት ነው ተባለ ፡፡

ይህ የተባለው አለም አቀፍ ጡት የማጥባት ሳምንትን በተመለከተ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ላይ ነው፡፡ አለም አቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት በኢትዮጲያ ሲከበር ለ10ኛ ጊዜ ሲሆን “ጡት ማጥባት የሕይወት መሰረት ነው” በሚልመሪ ቃል እስከ ነሃሴ 1ቀን 2010 ዓ.ም ይከበራል ፡፡ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶች እና ህፃናት ዳይሪክቶሬት የስርአዓተ ምግብ አማካሪ ወ/ሮ በላይነሽ ይፍሩ ህፃናት ከወሊድ […]