loading
የ ኮድ 3 አጋዥ ታክሲ ባለቤቶች በሰልፍ አቤቱታ እያቀረቡ ነው ።

“ጥያቄአችን ካልተመለሰ ስራ እናቆማለን” ብለዋል ። በአዲስ አበባ ከተማ በአጋዥ ታክሲ ትራንስፖርት አግልግሎት ላይ የተሰማሩ ኮድ 3 ሚኒባስ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች 22 አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት ፊትለፊት አቤቱታ ለማቅረብ ስራ አቁመው ተሰልፈዋል። የተቃውሞው መነሻ “የተተመነው የታክሲ ታሪፍ ከተሰጠን ስምሪት ርቀት ጋር ባለመጣጣሙ ለኪሳራ እየዳረገን ስለሆነ ይሻሻልልን” የሚል ነው። በአሁኑ ሰአት በመቶዎች የሚቆጠሩ […]

ሱዳንና ኢትዮጵያ የድንበር ቁጥጥርን ለማስወገድ ተስማሙ::

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር የምታደርገውን ቁጥጥር ለማቆም ቁርጠኛ መሆንዋን አስታውቃለች፡፡ ሱዳን ከውሳኔ ላይ የደረሰችው የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሀፊዝ አብዱል ራህማን ከኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በካርቱም በገቡት ስምምነት መሰረት ነው፡፡ የሀገራቱን ግንኙነት እንደሚያጠናክር የተነገረለት ስምምቱ እውን የሚሆነውም በሁለቱ ሀገራት የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ ሹም ሽር ሊያካሄድ ነው ተባለ፡፡

ሪፖርተር እንደዘገበዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የካቢኔ አባላት ሹም ሽር ሊያካሂዱመሆኑ እና ከመጠን በላይ በመስፋታቸው ምክንያት ለአሠራር አላመቹም የተባሉ መሥሪያ ቤቶች እንደሚታጠፉ ተነገሯል፡፡ ከፌዴራል መንግሥትና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ አመራሮች፣ እስከ ቀጣዩ ምርጫ ድረስ የካቢኔ አባል ሆነው የሚሠሩ ተሿሚዎች እየመለመሉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈጸመውን ድርጊት አወገዘች።

ቤተክርስትያንዋ ሰባት አብያተ ክርስትያናት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው የካህናት ህይዎት ማለፉንም ተናግራለች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሶማሌ ክልል በተፈጸመው ድርጊት ሳቢያ የሰው ህይዎት በመጥፋቱ ማዘናቸዉን ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈም የሰላማዊ ሰዎች ህይዎት ማለፉንና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀላቸውን ጠቅሰው፥ በሁኔታው የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል። አሁን ላይ አብረው በኖሩ ወንድማማች ህዝቦች […]

በድሬዳዋ ከተማ ከትናንት ጠዋት ጀምሮ በተከሰተው ግጭት የአሥር ሰዎች ህይወት ማለፉን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን እና ንብረት መውደሙን ፖሊስስ ገለፀ፡፡

ግጭቱ በተከሰተበት ቀበሌ 09 እና አካባቢው በአሁኑ ሰዓት የተረጋጋ ሁኔታ መኖሩን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ለአርትስ ቲቪ አስታውቋል፡፡ የሰዎች ህይወት ያለፈው ከእሳት ቃጠሎ ጋር በተገናኘ እንደሆነ የገለፀው ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር እያዋልኩ ነው ብሏል፡፡ የሰላም ተምሳሌቷ ድሬ ወደቀድሞ ሰላሟ እንድትመለስ ወጣቶችና የአገር ሽማግሌዎች አሁንም እየሰሩ እንደሆነ የገለፁልን ዋና ሳጅን ባንታለም ግርማ […]

የሶማሌ ክልል አዲሱ ፕሬዚዳንት አህመድ አብዲ መሀመድ የቀድሞው ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሀመድ ኦማር ስልጣን እንዳስረከቡና ሽግግሩም በሰላም እንደተጠናቀቀ ለቢቢሲ ሶማልኛ ተናግረዋል።

የክልሉ አዲሱ ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ስልጣን ለመልቀቅ በመጠየቃቸው የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አዲሱን የክልሉ ፕሬዚዳንት እንደመረጠም ገልፀዋል። ሰሞኑን ከብዙ ሰዎች ሞት፣ አብያተ ክርስትያናት መቃጠልና ንብረት መውደም ጋር ተያይዞም በክልሉ የመከላከያ ሰራዊት የገባ ሲሆን በክልሉ ከነበረው አለመረጋጋትና ተቃውሞዎች ጋር ተያይዞም በማዕከላዊ መንግሥት ግፊት ምክንያት አብዲ ኢሌ ከስልጣን እንደወረዱ ብዙዎች አስተያታቸውን ቢሰጡም አዲሱ ፕሬዚዳንት ሲንከባለል […]

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ በተከሰተዉ ግጭት በደረሰዉ የሰዉ ህይወት መጥፋትና ንብረት መዉደም ማዘንዋን ገለጸች፡፡

ቤተክርስትያንዋ ሀዘንዋን የገለጸችዉ ዛሬ የተጀመረዉን የፍልሰታን ጾም አስመልክቶ ለአርትስ ቲቪ በላከችዉ መግለጫ ነዉ፡፡ በመግለጫዉ የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሊቀጳጳስ ካርዲናል ብርሃነየሱስ እንዳስታወቁት የፍልሰታ ጾም የተጀመረዉ ቤተክርስትያናችን 19ነኛዉን የአመሰያን ጉባኤ በስኬት ባስተናገደች ማግስት በመሆኑ ተደስተናል ብለዋል፡፡ ሆኖም በአንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተዉ ግጭት ምክንያት የሰዉ ህይወት በማለፉ ሀዘን ተሰምቶናል፡፡ቤተክርስትያንዋም ለሰላም ትጸልያለች ብለዋል፡፡ ካርዲናሉ በመግለጫቸዉ በአሁኑ ወቅት ምእመናንም በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉና […]

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት ለማ መገርሳ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ወደ አስመራ የተጓዙበት ጉዳይ በስኬት ተጠናቋል ተባለ፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ የሚመራውና የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ የሚገኙበት የልዑካን ቡድን፣ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ- መንበር ኣቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራውና አቶ ኢብሳ ነገዎ፣ ኣቶ አቶምሳ ኩምሳ፣ ኣቶ ቶሌራ አደባ እና ኣቶ ገመቹ ኣያና የሚገኙበት የልዑካን ቡድን ዛሬ በአስመራ ኤርትራ በመገናኘት ወንድማዊ መንፈስ በተንጸባረቀበትና በሙሉ መተማመን በተካሄደ የእርቅ ውይይት ያሉ ስምምነቶችና […]

ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሚሰማሩ 1 ሺህ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ገለጻ አድርገዋል

የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከዛሬ ነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2010 ዓ.ም የሚካሄድ ነው። ዛሬ ይፋ በተደረገው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ላይ ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 1 ሺ ተመራቂ ወጣቶች ተሳታፊዎች ናቸው። ወጣቶቹ ከሚኖሩበት ክልል ባለፈ ወደ ሌሎች ክልሎች በመሄድ በተለያዩ ተግባራት ላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሰጣሉ። ይህ ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ […]