loading
ግብፅ የሁለት ሽህ አስራ አንዱን አመፅ የሚዘክሩ ፖለቲከኞችን አሰረች፡፡

ግብፅ የሁለት ሽህ አስራ አንዱን አመፅ የሚዘክሩ ፖለቲከኞችን አሰረች፡፡ የፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ መንግስት በ2011 በግብፅ የነበረውን አብዮት ስምንተኛ ዓመት አክብረዋል ያላቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ጨምሮ አምስት ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ፖሊስ ዲግኒቲ የተባለው ፓርቲ አባላል የሆኑትን  አሊ አብደል አዚዝ ፋዳሊን በቢሯቸው እንዲሁም የግብፅ ሶሻሊስት ፓርቲ መሪውን ጀማል አብደል ፈታህን በቤታቸው ነው የያዛቸው፡፡ […]

በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ እና በአካባቢው ለብዙ ዓመታት በስደት ላይ የነበሩ 168 ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት  በራሳቸው ፍላጎት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ እና በአካባቢው ለብዙ ዓመታት በስደት ላይ የነበሩ 168 ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት  በራሳቸው ፍላጎት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

በኦነግና መንግስት መካከል የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት የተቋቋመው የዕርቅ ኮሚቴ ለእርቁ ስኬታማነት እየሰራ መሆኑን አሳወቀ

በኦነግና መንግስት መካከል የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት የተቋቋመው የዕርቅ ኮሚቴ ለእርቁ ስኬታማነት እየሰራ መሆኑን አሳወቀ። ከሁለቱም ወገን በኩል ለእርቁ ያለውን ተነሳሽነትም አድንቋል። የኮሚቴው ተወካዮች ትላንት በአዲስ አበባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት ከሆነ የዕርቁን ሂደት በአባ ገዳዎችና በተቋቋመው ኮሚቴ ለማስኬድ ስራዎች ተጀምረዋል፡፡ የቴክኒክ ኮሚቴውን በወከል ለሚዲያዎች ማብራሪያ የሰጡት ተወካዮች አቶ በቀለ ገርባና አቶ ጀዋር መሃመድ ሲሆኑ ሂደቱን […]

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢትዮጵያን አንድነት አደጋ ውስጥ የሚከትቱ ሃይሎችን አንታገስም አሉ

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የምክር ቤቱ አባላትም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ ከውጭ ሀገራት ጥሪ ተደርጓላቸው ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽም በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋቱን […]

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በአሁኑ ጊዜ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያዩ ይጋኛሉ።

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በአሁኑ ጊዜ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያዩ ይጋኛሉ። ይህ ታሪካዊና በኢትዮጲያ የፖለቲካ ታሪክና ትርክት አይነተኛ የውይይት መድረክ ከጥቂት ወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋባዥነት ከተደረገው መድረክ የቀጠለ ነው። የዛሬውን ውይይት አስተባባሪ ከሆኑት አንዱ የሺዋስ አሰፋ (ሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር) እንደተናገሩት የመድረኩ ዋና አላማ በዚህ የፖለቲካው ሽግግር ወቅት የፖለቲካ አመለካከትን በሰላማዊ መንንገድ የመለዋወጥ ልምድን ለማሰደግ […]

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ስብሰባው የኢትዮጵያን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት (AfCTA) አባልነት አፀደቀ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ስብሰባው የኢትዮጵያን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት (AfCTA) አባልነት አፀደቀ። ይህ ስምምነት የዓለም የንግድ ድርጅት ከተመሰረተ ትልቁ የንግድ ስምምነቶች አንዱ ሲሆን በአፍሪካ አንድ ገበያ ለመፍጠር ሙከራ ያደርጋል። ይህ ውሳኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሚያራምዱት አእምሮን ለሃሳብ መንሸራሸርና ገበያዎች ለትስስር በመክፈት በአፍሪካ ክልላዊ ውህደትንና ጥብቅ ጥምረት እንፍጠር ከሚለው ራዕይ ጋር ይጣጣማል። […]

የኮንጎው ፕሬዝዳንት የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን ሊያደርጉ ነው፡፡

የኮንጎው ፕሬዝዳንት የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን ሊያደርጉ ነው፡፡ በአወዛጋቢ የምርጫ ውጤት ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ሺሴኬዲ ቤተ መንግስት ከገቡ ሀያ ቀን ሳይሞላቸው ነው ዛሬ የውጭ ሀገር ጉዟቸውን የሚጀምሩት፡፡ ሺሴኬዲ የመጀመሪያ የጉዞ መዳረሸቸው ጎረቤት አንጎላ ናት፡፡ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ጎንጎ እና አንጎላ ሰፊ የድንበር ቦታ የሚጋሩ  ሲሆን የሁለቱ ሀገራት መሪዎች  በንድበር አካባቢ ስለሚኖሩ ዜጎች ይወያያሉ ተብሎ […]