loading
አርሷደሯ ጌሪ አሜሪካ ተብሎ ለሚጠራው የእህል ፈጅ ትል መድሀኒት አገኙ፡፡

አርሷደሯ ወ/ሮ ታቦቴ አባተ በቦኖ በደሌ ዞን አርሶ አደር ናቸው። ከችግራቸው በመነሳትም ጌሪ አሜሪካ ለተባለ ትል አዲስ የትል ማጥፊያ ፈጥረዋል። የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ሴንተር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ ጌሪ አሜሪካ በቆሎን በብዛት የሚያጠቃ ትል ነው።ትሉ ቁጥጥር ካልተደረገበት በበቆሎ ምርት ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል። በአንድ ሌሊት በ1500 እጥፍ ሊራባ ይችላል። ወ/ሮ ታቦቴ ታዲያ ይህን ትል የሚገድል መድሀኒት […]

በአዲስ አበባ ከአዲስ አመት በፊት በክፍለከተማና በወረዳ አመራሮች ላይ ለዉጥ ይደረጋል ተባለ፡፡ 

በዚህ ሳምንትም በክፍለከተማ ደረጃ ያሉ ዋና ዋና አመራሮች እንደ አዲስ እንደሚዋቀሩ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት በድህረ ገፁ አስታዉቋል፡፡ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በወቅታዊ የከተማዋ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ የተጀመረውን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ እና አሁን እየታየ ያለውን ሀገራዊ ተስፋ ለማደናቀፍ እንዲሁም የመዲናችንን ሰላም ለማደፍረስ ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ በመሆኑ ህብረተሰቡ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ደቡብ አፍሪካን ሊጎበኙ ነው፡፡

ኢ.ቢ.ሲ በድረገፁ እንዳስነበበው የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኤስ .ኤ.ቢ.ሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ዶክተር አብይ አህመድ ከቀጠናው ሀገራት ውጭ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት የመጀመሪያው በደቡብ አፍሪካ እንዲሆን ፍላጎት አላቸው፡፡ አቶ ኃይለማርያም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሰርል ራማ ፖሳ አድርሰዋል፡፡ በፀረ አፓርታይድም ይሁን በነጻነት ትግል ወቅት […]

በመሬት፣ በቀበሌ ቤቶች፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በህንፃዎች ላይ የኦዲት ሥራ በመስራት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት በከተማ አስተዳደሩ እስካሁን የነበሩ ተግባራትን ቆም ብሎ በማየት ሀገራዊ ለዉጡን ለማስቀጠል በመሬት፣ በቀበሌ ቤቶች፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በህንፃዎች ላይ የኦዲት ሥራ እየተሰራ ነዉ፡፡ ምክትል ከንቲባዋ ˝የአዲስ ተስፋ ቀመር˝ በሚል መሪ ቃል አዲሱን ዓመት ለማክበር ጥላቻን በመቀነስ (-)፣ ያለንን በማካፈል (÷)፣ […]

ከኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ከነሀሴ 14 እስከ 16/2010 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የጥልቅ ተሃድሶውን አፈፃፀምና ያስገኘውን ውጤት በተለመደው ድርጅታዊ ባህል፣ ዴሞክራሲያዊነትን በተላበሰ እና በሰከነ አግባብ በጥልቀት ገምግሟል፡፡ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የጥልቅ ተሃድሶውን ተከትሎ የተወሰዱ የለውጥ እርምጃዎች የአመራር ፈጠራ ታክሎባቸው የለውጡ ቱርፋት የሆኑ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን አረጋግጧል፡፡ ከአሁን በፊት ውሳኔዎች እየተወሰኑ እና አቅጣጫዎች እየተቀመጡ በአፈፃፀም ድክመት ይታይባቸው […]

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በኮየ ፈጬ ሳይት የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚገኙበትን ደረጃ ጎበኙ

በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተመራውና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልኡካን በ11ኛው ዙር የተላለፉ የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን አነጋግረዋል። ነዋሪዎች የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ባለማሟላቱ ቅሬታቸውን ገልጸውላቸዋል በተለይም የውሃ፣ የመብራት  እና የባለድርሻ አካላት በቅንጅት ተናበው አለመስራት በኑሮአቸው ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረ ነው የገለጹት፡፡ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለም የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች የህብረተሰቡን ቅሬታ ወስደው […]

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ ነው አለ፡፡

ተቋሙ ባለፉት አመታት ለፓርቲ የወገነ አሰራር መተግበሩና ከተሰጠው አገራዊ ተልእኮ ውጪ ዜጎችን የማፈን የማሰርና ኢሰብአዊ ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱ ተቋሙ እንዲፈራ አድርጎት ቆይቷል ተብሏል፡፡ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ጀነራል አደም መሀመድ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ከተቋሙ አሰራር ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትም ተቋሙ የተቋቋመበትን አዋጅ ማሻሻልን ጨምሮ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ ነው ፡፡ በተቋማዊ የሪፎርም ስራው […]

ባለፈው ሰኔ በአሶሳ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡

ያን ግዜ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ለድጋፍ አጽድቋል፡፡ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግስት በግጭቱ ምክንያት ህይወታቸው ላለፈ 16 ግለሰቦች ቤተሰብ ለእያንዳንዳቸው 30 ሺ ብር፣ በግጭቱ ምክንያት ከባድ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው 11 ግለሰቦች ለእያንዳንዳቸው 20ሺ ብር እንዲሁም በግጭቱ ምክንያት ቀላል ጉዳት ለደረሰባቸው 78 ግለሰቦች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 10 ሺ ብር […]