loading
የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ዉጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናል፡፡

154 ሺ 10 ወንዶችና 127 ሺ 964 ሴቶች በድምሩ 281 ሺ 974 ተማሪዎች ፈተናዉን ወስደዋል፡፡ ተማሪዎች ዉጤታቸሁን ለማወቅ በኤጀንሲዉ ድረ ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት admission በሚለዉ ዉስጥ የመፈተኛ ቁጥር በመጻፍ go የሚለዉን አንዴ በመጫን ማየት ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡

በምህረት አዋጅ ሰበብ በማረሚያ ቤቶች ተከስቶ የነበረዉ አለመረጋጋት መስከኑን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ ፡፡

የምህረት አዋጁ ከወጣ በኋላ ምህረት ይገባናል በሚል በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ሁከት ተከስቶ እንደነበርና አሁን ግን በማረሚያ ቤቶች ዉስጥ መረጋጋት መፈጠሩን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ረዳት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አዲሱ ጴጥሮስ ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ አቶ አዲሱ በጠቅላይ አቃቤ ህግ የምህረት አዋጁ ዝርዝር አፈፃፀም መሰረት በምህረቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ እና ተጠቃሚ የማይሆኑ ታራሚዎች በግልፅ ይፋ ከሆነ በኋላ […]

በሰኔ 16ቱ የቦንብ ፍንዳታ በተጠረጠሩት ላይ የመጨረሻ የምርመራ የሶስት ቀን ተጨማሪ ጊዜ ተሰጠ::

የቀድሞው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ በሰኔ 16ቱ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ከተከሰተው የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ የስራ ክፍተት አሳይተዋል ተብለው በተጠረጠሩት ላይ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ተጠይቆ የመጨረሻ የሶስት ቀን ጊዜ ብቻ ተፈቅዷል።

የአንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ በ8 ሰአት አራት ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።

የአንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ በ8 ሰአት አራት ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል። ከጠዋቱ 4 ሰአት ጀምሮም ለበርካታ አመታት ባገለገለበት በብሄራዊ ቲያትር ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ እና የሙያ አጋሮቹ በተገኙበት አሸኛኘት እንደሚደረግለት ተነግሯል፡፡

በወታደራዊ ስነ ምግባር ጥሰትና ኩብለላ ወንጀሎች ለተከሰሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምህረት ማድረጉን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያጸደቀውን የምህረት አዋጅ መሰረት በማድረግ በወታደራዊ የስነ ምግባር ጥሰት ተከሰው በማረሚያ ቤት የሚገኙና ቀደም ሲል ከሃገር የኮበለሉ የሰራዊት አባላት ምህረት ተደርጎላቸዋል ብለዋል። የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ኪዱ አለሙ፥ ለኢዜአ እንደገለጹት መንግስት በሃገር አቀፍ ደረጃ የጀመራቸውን የለውጥ እንቅስቃሴዎች ለማስቀጠል መከላከያ ሰራዊት ለውጡን በመደገፍ እየሰራ ነው። የምህረት አዋጁ […]

በብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የአየር ወለድ አሰልጣኝ የነበረችው መ/አለቃ አይዳ አሌሮ ተፈታች፡፡

ወደ መከላከያ ሠራዊት የተቀላቀለችው በ1997 ዓ.ም የሥልጠና ቦታው ብር ሸለቆ የምልምል ወታደሮች ማሠልጠኛ ነው፡፡ አይዳ በውትድርና ስልጠና ከፍተኛ ውጤት ያመጣች ተመራቂ ናት፡፡ በፓራሹት 27 ጊዜ በመዝለል የምትታወቀው አይዳ በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በ2009ዓ.ም ስትሰለጥን ከ1800 ሰልጣኞች አንደኛ መሆኗ ልዩ ያደርጋታል፡፡ በቅርቡ ከሽብር ቡድን ጋር ተገኛኝተሻል ተብላ ክስ ቀርቦባት ነበር፡፡ በተጨማሪም ውስጥ ለውስጥ ሠራዊቱን በማነሳሳት አገር በማስከዳት […]

በሀዋሳ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ፡፡

የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት በሀዋሳ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ከ 1 ወር በላይ የቆዩ ተፈናቃዮች ከዛሬ ጀምሮ ወደ የቀያቸዉ ይመለሳሉ ብለዋል፡፡ አቶ ሚሊዩን ተፈናቃዮቹ የሚመለሱባቸዉ መንደሮች የቀድሞ ሰላማቸዉን ማግኘታቸዉን ተናግረዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ እስኪቋቋሙ ድረስ ቤተሰብ ላላቸው በወር 4 ሺ ብር ፤ቤተሰብ ለሌላቸው ደግሞ በወር 2 ሺ […]

የጀዋር መሐመድ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦ ኤም ኤን /OMN ) የአዲስ አበባ ቢሮ የፊታችን እሁድ በይፋ ይመረቃል፡፡

የጀዋር መሐመድ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦ ኤም ኤን /OMN ) የአዲስ አበባ ቢሮ የፊታችን እሁድ በይፋ ይመረቃል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች እንዳስታወቀዉ በሚሊኒየም አዳራሽ የኦ ኤም ኤን ሥራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የሀገር ሽማግለዎችና ቄሮዎች በተገኙበት የቢሮ ምረቃና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይካሄዳል ተብሏል፡፡