loading
ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በማተም ለማዘዋወር ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በማተም ለማዘዋወር ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ የሲዳማ ክልል ፖሊስ  ኮሚሽነር አበራ አሬራ ለኢዜአ እንደገለጹት፤  ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት  እጅ ከፍንጅ ተይዘው ነው። ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተካሄደ አሰሳ በሃዋሳ ከተማ በጥቁር ገበያ ለማዘዋወር ታቅዶ የነበረና የህትመት ሂደቱ ያላለቀ ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ […]

አሸባሪው ቡድን ያደረሰው ውድመት በጦር ወንጀል የሚያስጠይቀው ነው -ጎንደር ዩኒቨርስቲ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014  አሸባሪ ቡድኑ በደቡብ ጎንደር ያደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት በጦር ወንጀል የሚያስጠይቀው ነው ሲሉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ኃላፊ አቶ ልጅ አለም ጋሻው ገለጹ፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ኃላፊና በደቡብ ጎንደር አሸባሪው ቡድን ያደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት የሚያጣራው የጥናት ግብረ ኃይል ሰብሳቢ አቶ ልጅ አለም ጋሻው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት […]

ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን- ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 የመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ የሕወሓት ሽብር ቡድንን እስከ መጨረሻው በመቅበር ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን አሉ። የልዩ ዘመቻዎች ኃይል፣ የሪፐብሊክ ጥበቃ ኃይል እና የአየር ወለድ አባላት በጭንቅ ላይ ያለች አገርን ችግር የፈቱ የጭንቅ ቀን ደራሾች መሆናቸውን አስታውቀዋል። ሌተናል ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት የመጀመሪያው […]

የታሪፍ ማሻሻያው ይፋ እስኪሆን በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ ይቀጥላል::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የታሪፍ መጠን እንደሚሻሻል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ ። የዓለም ዐቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በታኅሣሥ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን ቢሮው አስታውሷል፡፡ ይህንን ተከትሎ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናቱ እየተጠናቀቀ ነው ያለው ቢሮው፤ […]

የኢትዮጵያን ስም የሚያጠለሸው አዋጅ ውድቅ ተደረገ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 07፣ 2014 ኢትዮጵያን በዘር ተኮር ጭፍጨፋ ለመጠየቅ ታስቦ የነበረው ህግ መሰረዙ ይፋ ተደረገ፡፡ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ከከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ያደረገውን ስብሰባ መሰረት በማድረግ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ለምክር ቤቱ መረጃ መላኩ ታውቋል፡፡ በመረጃውም በኢትዮጵያ “የዘር ተኮር ጭፍጨፋ ተካሂዷል” በሚል ሀሰተኛ ውንጀላ ኢትዮጵያን ለመጠየቅ የሚረዳና በአሜሪካ ሴኔት ቢሮ የታሰበው ሕግ ማለትም […]

በአዲስ አበባ የሚገኙ ባለኮከብ ሆቴሎች ለዳያስፖራዎች እስከ 30 በመቶ ቅናሽ አደረጉ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 07፣ 2014 በአዲስ አበባ የሚገኙ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ለገናና ጥምቀት በዓላት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ አንድ ሚሊዮን ዲያስፖራዎች እስከ ሰላሳ በመቶ የሚደርስ ልዩ ቅናሽ ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ገለጸ። የአዲስ አበባ የሆቴል ባለቤቶች ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ አምሀ በቀለ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትእንደገለጹት፤ በመዲናዋ የሚገኙ ባለኮከብ ሆቴሎች ለገናና ለጥምቀት በዓላት ወደ ኢትዮጵያ […]

ኮልፌ አጠና ተራ ታይዋን ሰፈር አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 ኮልፌ አጠና ተራ ታይዋን ሰፈር አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጸ:: አደጋው የደረሰው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታዉ ኮልፌ አጠና ተራ ታይዋን ሰፈር አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ትላንት ምሽት በደረሰው በዚህ የእሳት አደጋ 7 ሚሊዮን […]

ሩሲያ ዩክሬን ላይ የኒውክሌር ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አስጠነቀቀች::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 ሩሲያ ዩክሬን ላይ የኒውክሌር ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አስጠነቀቀች:: ሞስኮ ባወጣችው መግለጫ ኔቶ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ በማቀበል የእጅ አዙር ጦርነት ከፍቶብኛል ስትል ወቀሳ ሰንዝራለች፡፡ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቨሮቭ ከአንድ የሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ መላው ዓለም ይህን ጉዳይ አቅልሎ መመልከት የለበትም ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ የላቭሮቭ ቃለ መጠይቅ የተሰራጨው […]