loading
የፖሊስ ልዩ የበዓል ዝግጅት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 የስቅለት እና የትንሳኤ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ወቅቱን ያገናዘበ የፀጥታ ዕቅድ አውጥቶ ወደ ተግባር መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡በበዓላት መዳረሻ ወቅቶች ከወትሮው በተለየ ጨምሮ የሚታየውን የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተከትሎ የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት እና በተለይም በግብይት፣ በመዝናኛ ሰፍራዎች እና በዕምነት ተቋማት አካባቢ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ከወትሮው የተለየ ዝግጅት በማድረግ የፀጥታ […]

ለህግ ታራሚዎች የተደረገ ይቅርታ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22 ፣ 2013የአማራ ክልል ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን ገለጸ የአማራ ክልላዊ መንግስት ለ2ሺህ 705 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል፡፡ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አለምሸት ምህረቴ ለኢዜአ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ለታራሚዎቹ ይቅርታ ያደረገው በይቅርታ ቦርዱ ተመርምሮ መስፈርቱን አሟልተው በመገኘታቸው ነው። የይቅርታው […]

የአሚሶም ሽልማት ለኢትዮጵያ ወታደሮች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 አሚሶም ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት አስተዋጽኦ ላበረከቱ የኢትዮጵያ ወታደሮች የክብር ሜዳልያ ሸለመ:: በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) ስር የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኑ፡፡ ሽልማቱ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች በሶማሊያ በነበራቸው የአንድ አመት ከስድስት ወር ቆይታ በሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በተደረገው ጥረት ላደረጉት […]

በኢትዮጵያ የሚከበረው የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን መረጃ ለህዝብ ጥቅም በሚል መሪ ሀሳብ ነው ለ30ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው። ከ 30 አመት በፊት በናሚቢያ መከበር የጀመረው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ መንግስታት የፕሬስ ነፃነትን እንዲያከብሩ መነሻ ሆኗል። በኢትዮጵያ የሚከበረውን አለምአቀፉ የፕሬስ ቀን በማስመልከት አዲስ አበባ ውስጥ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ በሀገራችን የፕሬ […]

ኢትዮጵያ የታገሰችው የሱዳንን ህዝብ ስለምታከብር እንጂ ፈርታ አይደለም!

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 ሱዳን ቤንሻንጉልን የራሷ ለማድረግ የምታደርገው እንቅስቃሴ እጅግ አሳፋሪ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሱዳን የኢጋድ ሊቀመንበር ሆና እያለ በዚህ መንገድ ለመፈፀም የምትሞክረው ህገወጥ ድርጊት በኢትዮጺያ በኩል ፍፅም ተቀባይነት እንደሌለው ነው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የገለፁት፡፡ ሱዳን የኢትዮያን መሬት የመያዟና ኢትዮጵያዊያን አርሶአደረች ማፈናቀሏ ሳያንሳት ቤንሻንጉልን የራስዋ […]

ማህበረሰቡ በሀሰተኛ መረጃ እንዳይታለል የጠቅላይ ሚሴቴር ፅህፈት ቤት አሳሰበ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 ማህበረሰቡ በሀሰተኛ መረጃ እንዳይታለል የጠቅላይ ሚሴቴር ፅህፈት ቤት አሳሰበ፡፡ ጽህፈት ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ የወንጀለኞች ቡድን የሀሰተኛ መረጃ እያሰራጨ መሆኑን ደርሰንበታል ብሏል፡፡ የወንጀለኞች ቡድን አባላቱ ከቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግል የኢሜይል አድራሻ የተላከ በማስመሰል መረጃ በመጠየቅ እና ሐሰተኛ ምላሽ በመስጠት ላይ መሆናቸውን አውቀናል ነወ ያለው። በመሆኑም ሁሉም ሰው […]

የኢትዮጵያ ሳምንት ከግንቦት 10 እስከ ግንቦት 16 በወዳጅነት ፓርክ ይከበራል::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 የኢትዮጵያ ሳምንት ከግንቦት 10 እስከ ግንቦት 16 በወዳጅነት ፓርክ ይከበራል:: ሀሳቡን ያመነቨጩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ሳምንት የሚለውን ዝግጅት እንዲያስተባብሩ ለሦስት ሴት ሚኒስትሮች የቤት ሥራ ሰጥተዋቸው እንደነበር ተገልጿል፡፡ በዚህም መሰረት ስራውን በሃላፈነት የተረከቡት የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሣው፣ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሐመድ […]

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ የምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ እንዲራዘም ወሰነ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ የምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ እንዲራዘም ወሰነ:: ቦርዱ ይህን ውሳኔ ያለፈው በአንደሰንድ የምጫ ክልሎች በተለያዩ ምክንያቶች መራዘሙን መነሻ በማድረግ መሆኑን ተናግሯል፡፡ በዚህም መሰረት በምእራብ፣ በምስራቅ ወለጋ እንዲሁም በቄለም ወለጋና በሆሮጉድሩ ዞኖች 31 ምርጫ ክልሎች መካከል በ24ቱ ምዝገባው ከሚያዝያ 29 – ግንቦት 13 ቀን 2013 ድረስ […]

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ለ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላፉ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27 ፣ 2013 በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ለ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላፉ::በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቨገንሲ ተርክሂን ኢትዮጵያውያን የዛሬ 80 ዓመት ለተቀዳጁት ድል የሚታሰብበት የአርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በዚህ ክስተት ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን ከፋሽስት ወረራ ነፃ ያወጡበት 80ኛ ዓመት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ ብለዋል። በአውሮፓውያኑ 1935 የፋሺዝም ጭቆናን በመጋፈጥ […]

የህክምና ኦክስጂን ማምረቻ እና ማከፋፈያ ማዕከል በጅግጅጋ ተመረቀ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27 ፣ 2013 የህክምና ኦክስጂን ማምረቻ እና ማከፋፈያ ማዕከል በጅግጅጋ ተመረቀ:: የሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ ያስገነባውን የህክምና ኦክስጂን ማምረቻ እና ማከፋፈያ ማዕከል የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በተገኙበት አስመርቋል። በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይ ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን እና የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዩሱፍ መሀመድ ተገኝተዋል። የማእከሉ መገንባት እንደ ክልል […]