loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አመሰገኑ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21፣ 2013 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰላማዊ ምርጫ እንዲሳካ አስተዋጽዖ ላደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምስጋና አቀረቡ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ አንድ ሳምንት በኋላ ዛሬ ጠዋት ከፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝቼ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና የወጣችበት ሰላማዊ ምርጫ እንዲሳካ ላደረጉት አስተዋጽዖ […]

ሱዳን የሽግግር መንግስትና በተቃዋሚ ሃይሎች የተጀመረው የሰላም ድርድር አሁንም እክል ገጥሞታል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21፣ 2013 በ እስካሁን በተደረጉ ውይይቶች በፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግባባቶች ቢኖሩም በማእከላዊ መንግስትና በክልሎች መካከል በሚኖረው የሥልጣን ውክልና መስማማት አልተቻላቸውም፡፡ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የሱዳን ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄን ወክለው የሚደራደሩት አማር አሞን ዋና ዋና ሀገራዊ ስምምነቶች ወደፊት በህዝበ ውሳኔ እንዲረጋገጡ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ በተለይ በሁለቱ ሃይሎች መካከል አለመግባባት እንዲካረር ያደረገው ዋነኛ […]

በጅማ ከተማ ለሸማቾች የተላለፈ ማሳሰቢያ!

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21፣ 2013  የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ እና የጥራት ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆነ ምግቦች በጅማ ከተማ መወገዳቸዉን ባለስልጣኑ አስታወቀ ግምታቸው 260 ሺህ ብር የሆነ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈና የጥራት ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆነ የምግብ ሸቀጦች መወገዳቸውን የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡ የባለስልጣኑ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጅማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የመድሃኒት ባለሙያ ኢንስፔክተር ሚፍታህ ዝናብ […]

አዲሱ የኮቪድ -19 ዝርያ ደቡብ አፍሪካን እያመሳት ነዉ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21፣ 2013 ዴልታ የተሰኘው አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ደቡብ አፍሪካን ክፉኛ እየጎዳት ነዉ ተባለ አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መጀመሪያ በህንድ የተገኘ ሲሆን፤ በደቡብ አፍሪካም የዚሁ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ አሳሳቢነት ከፍ እያለ በመምጣቱ አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣል ተገዳለች፡፡ ሀገሪቱንም በጥር ወር ወደነበረችበት አሳሳቢ ሁኔታ እየመለሳት የሚገኘው ይህ ቫይረስ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ […]

የመሪያቸው ሸንቃጣነት ያሳሰባቸው ሰሜን ኮሪያዊያን…

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22፣ 2013 ሰሜን ኮሪያዊያን የመሪያቸውን ክብደት መቀነስ ከጤናቸው ሁኔታ ጋር አያይዘው ሀሳብ ገብቷቸዋል ተባለ፡፡ ለወትሮው በሰፋፊ ልብሶቻቸው ፈርጠም ባለ ሰውነታቸው የሚታወቁት ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሸንቀጥ ብለው ታይተዋል ነው የተባለው፡፡ ይህ ደግሞ ለሰሜን ኮሪያዊያን እንደ መልካም ዜና እንደማይቆጠር መገናኛ ብዙሃን በስፋት እየዘገቡት ይገኛሉ፡፡ የሀገሪቱ ቴሌቭዥን ጣቢያ በሳምንቱ መጨረሻ […]

ቶጎ በምዕራብ አፍሪካ ግዙፍ የተባለውን የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22፣ 2013 ከዋና ከተማዋ ቶጎ በደቡባዊ አቅጣጫ 250 ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝው ይህን ፕሮጀክት የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ ፕሮጀክቱ 158 ሺህ የሚሆኑ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በቀጣይ ለማዳረስ ዕቅድ ተይዞለታል ነው የተባለው፡፡ በአቡዳቢው ልኡል ሼክ ሙሃመድ ቢን ዛይድ የተሰየመው ይህ ፕሮጀከት 64 ነጥብ 7 ሚሊዮን […]

ትግራይ ውስጥ ለሚከሰት ችግር መንግስት ተጠያቂ አይደለም አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23፣ 2013 ከዚህ በኋላ ትግራይ ለሚከሰት ችግር የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ አይሆንም ሲሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለፁ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና መከላከያ ሰራዊት በጋራ በሰጡት መግለጫ “ከዚህ በኋላ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለሚከሰት ችግር የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ” እንደማይሆን አስታውቀዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዴኤታው ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት መግለጫ የፌዴራል መንግስት ከዚህ በኋላ በትግራይ […]

ሶማሊያ በጥቅምት ወር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ አቅዳለች ተባለ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23፣ 2013 ሶማሊያ በጥቅምት ወር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ አቅዳለች ተባለ፡፡ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ የሶማሊያ የፖለቲካ መሪዎች የዘገየውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጥቅምት 10 ለማካሄድ መስማማታቸውን አስታውቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮቤል በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ የተካሄደውን የሁለት ቀናት ውይይት ተከትሎ ባለድርሻ አካላት በውክልና የሚካሄደውን የፓርላማ እና […]

በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ዉስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት ሞት አልተመዘገበም::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24፣ 2013  በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በኮቪድ -19 ምክንያት የሞት መጠን አልተመዘገበም ተባለ፡፡ የጤና ሚኒስቴር የ24 ሰዓትን ሪፖርት ባወጣዉ መረጃ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከረጅም ግዜ በኋላ በኮቪድ- 19 ምክንያት ሞት ያልተመዘገበበት ቀን ሆኗዋል፡፡ በ24 ሰዓቱ በተደረገ 4 ሺህ 974 የላብራቶሪ ምርመራ 137 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በጽኑ የታመሙ 145 ሰዎች ሲሆኑ ከበሽታዉ ያገገሙ […]

የአገዛዝ እንጂ የፖሊሲ ለዉጥ አንፈልግም -ሱዳናዊያን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24፣ 2013  በሱዳን የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመፅ መንግስት ይቀየር ወደሚል አጀንዳ መሸጋገሩ ተሰማ፡፡ ሱዳን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ምክረ ሀሳብን ተቀብላ ተግባራዊ ያደረገችው የኢኮኖሚ መሻሻያ የፈጠረው የዋጋ ንረት ነው በሀገሪቱ ህዝባዊ አመፅ የቀሰቀሰው ተብሏል በተለያዩ የሱዳን ከተሞች በርካታ ሰዎች ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስልጣኑን ይልቀቅ የሚል መፈክር ይዘው ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል ነው የተባለው፡፡ አጃንስ […]