loading
ሐሰት: የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ርዕስቱ ይርዳው ፌዴራል መንግሥት ጫና ያደርግብናል አላሉም።

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ርዕስቱ ይርዳው ከወላይታ ህዝብ የክልልነት ጥያቄም ጋር ተያይዞ የፌዴራል መንግሥት ጫና ማድረጉን የሚገልጽ መግለጫ አልሰጡም። የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ርዕስቱ ይርዳው “የወላይታ ጥያቄ እጅግ በጣም እያሳሰበኝ ነው” ብለዋል የሚለው የፌስቡክ ልጥፍ ሐሰተኛ ነው። በአማርኛ የተጻፈው ልጥፍ  “#ሰበር #ዜና #የደቡብ #ክልል #ርዕስ #መስተዳድር #አቶ #ርዕስቱ #ስለ #ወላይታ #እውነታውን #ተናገሩ “ሆኖም የወላይታ ጥያቄ […]

የተጭበረበረ ፡ ይህ ምስል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በወታደሮች ተይዘው አያሳይም።

ትክክለኛው ምስል የህወሃት ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር ውለው አዲስ አበባ ሲገቡ ያሳያል። ልጥፉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በለበሱ ወታደሮች በቁጥጥር ስር የዋሉ አስመስሎ ለማቅረብ ሞክሯል። ልጥፉ “ዛሬ የደረሰን ሰበር መረጃ ሽመልስ አብዲሳ ታሰረ” ይላል። የጎግል የምስል ፍለጋ (Google reverse image search) ውጤት እንደሚያሳየው የልጥፉ […]

ሐሰት: ይህ ምስል MI-35 የተሰኘ የጦር ሄለኮፕተር በአፋር ክልል ሚሌ ተመቶ አያሳይም።

ምስሉ የተወሰደው ዘ ታይምስ ከተባለ በለንደን የሚገኝ የብሪቲሽ ዕለታዊ ብሔራዊ የጋዜጣ ድህረገስፅ ላይ ነው። ምስሉ የኢራቅ የጦር ሄሊኮፕተር በሰሜን ኢራቅ በሞሱል አቅራቢያ የሚገኙ የአይሲስ ቦታዎችን ሲደበድብ ያሳያል። ይህ የፌስቡክ ልጥፍ “#ሰበር #ዜና #ትግራይ #ትስዕር የትግራይ ሰራዊት አየር ሀይል ምድብ MI-35 የተሰኘ የጦር ሄለኮፕተር በአፋር ክልል ሚሌ መቶ መጣሉን የትግራይ ሰራዊት ሰንተራል ኮማንድ ቃላቀባይ ጌታቸው ረዳ […]

ሐሰት: ፕሬዚዳንት ሣህል ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የእርስበርስ ጦርነት ነው አላሉም።

ምስሉ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የ2014 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን መክፈቻ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ ነው።  በአማርኛ የተጻፈው ልጥፍ  “#ሰበር #ዜና ለመጀመሪያ ጊዜ የኢፌዴሪ  ፕሬዚዳንት ሣህል ወርቅ ዘውዴ እውነት ተናገሩ  ይሄ ጦርነት የእርስበርስ ጦርነት ነው በማለት ለፈረንሳይ መጽሔት ገልፃለች” ይላል። እ.ኤ.አ ህዳር 22-2021  War in Ethiopia: the disarray of President Sahle-Work […]

ሐሰት: ይህ ምስል የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግድብ በድሮን መመታቱን አያሳይም።

የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግድብ ላይ ምንም አይነት በከባድ የጦር መሳርያ የደረሰ ጉዳት የለም። በአማርኛ የተጻፈው ልጥፍ “#ሰበር #ዜና የተከዜ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በድሮን ተመታ በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው ቡድን የተከዜ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በሰዉ አልባ አዉሮፕላን (ድሮን) እንደመታ ተገለፀ። የህውሓት ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸዉ ረዳ በቲዊተር ገፃቸዉ እንደገለፁት ከሆነ ዛሬ ጣዋት አከባቢ ጥቃቱ በግድቡ […]

ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን- ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 የመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ የሕወሓት ሽብር ቡድንን እስከ መጨረሻው በመቅበር ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን አሉ። የልዩ ዘመቻዎች ኃይል፣ የሪፐብሊክ ጥበቃ ኃይል እና የአየር ወለድ አባላት በጭንቅ ላይ ያለች አገርን ችግር የፈቱ የጭንቅ ቀን ደራሾች መሆናቸውን አስታውቀዋል። ሌተናል ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት የመጀመሪያው […]

የሽብር ቡድኑ በጭና እና ቆቦ ንፁሃንን በጅምላ ጨፍጭፏል – ሂዩማን ራይትስ ዎች ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 ሂዩማን ራይት ዎች የህወሓት የሽብር ቡድን በወረራ ይዟቸው በነበረው የአማራ ክልል ጭና እና ቆቦ ከተሞች ንፁሃን ዜጎችን በጅምላ መጨፍጨፉን ገለፀ፡፡ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት እንዳለው፥ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ከፈረንጆቹ ነሐሴ 31 እስከ መስከረም 9 ቀን 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል በያዛቸው አካባቢዎች በርካታ ንፁሃን ዜጎችን በጅምላ ገድሏል፡፡ ከዚህም ውስጥ የጭና ቀበሌ […]

የታሪፍ ማሻሻያው ይፋ እስኪሆን በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ ይቀጥላል::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የታሪፍ መጠን እንደሚሻሻል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ ። የዓለም ዐቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በታኅሣሥ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን ቢሮው አስታውሷል፡፡ ይህንን ተከትሎ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናቱ እየተጠናቀቀ ነው ያለው ቢሮው፤ […]